>

ብሔርተኛ በራሱ መቆም የማይችል ጥገኛ ተዋሲያን ነው‼️ (ስዩም ተሾመ)

ብሔርተኛ በራሱ መቆም የማይችል ጥገኛ ተዋሲያን ነው‼️
ስዩም ተሾመ
አብዛኛው #የአብን አባልና ደጋፊ #አማራ የሚለውን ስም ሳይጠቅስ ከእኔ ፊት የመቅረብ አቅምና ድፍረት የለውም፡፡ የህወሓትና ኦነግ አባላትና ደጋፌዎች በየፊናቸው ትግራይ ወይም የኦሮሞን ህዝብ ስም ሳይጠሩ አንዳች ነገር ማድረግ ሆነ መናገር አይችሉም፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ብሔርተኞች ከሰው ተርታ ቆመው ማውራት የቻሉት ከራሳቸው ይልቅ “እንወክለዋለን” ያሉትን ህዝብ ስም በማስቀደም ነው፡፡
እነዚህ ሰዎች ከብሔራቸው ውጪ ምንድን ናቸው? ምንም! ዳንኤል ብርሃኔ “ትግራይ፥ ትግራይ” ባይል ኖሮ ማን ከሰው ይቆጥረው ነበር? ማንም አይቆጥረውም! ጃዋር መሃመድ “ኦሮሞ ኦሮሞ” ካላለ ማን ዞር ብሎ ያየዋል? ማንም አያየውም! አሁን አብኖች “አማራ፥ አማራ” ባይሉ ኖሮ ስለ መፈጠራቸው ራሱ ማን ያውቅ ኖሯል? ማንም አያውቃቸውም!!! የእነዚህ ሰዎች ዕውቅና የተመሠረተው “እንወክለዋለን” በሚሉት ህዝብ ስም ላይ ነው፡፡
በአጠቃላይ ብሔርተኛ የሚባሉት ሰዎች የራሳቸው የሆነ አቋምና አመለካከት የላቸውም፡፡ በራሳቸው ምን እንደሚያስቡ በይፋ ተናግረው አያውቁም! ተምረው በሰለጠኑበት ሙያ “ይህን አድርጌያለሁ፣ እንዲህ ሰርቼያለሁ” የሚሉት ነገር የላቸውም፡፡ የመጡበትን ህዝብ ስም ከመጥራት በዘለለ በራሳቸው ምንም ዓይነት ፋይዳ የሌላቸው ብኩኖች ናቸው፡፡ ጃዋር መሃመድ ኦሮሞ መሆኑ ያበቃ እለት ስለ ማንም ምንም ማለት አይችልም፡፡ ስለዚህ የእናቱን አማራነት አይኑን በጨው አጥቦ መካድ አለበት፡፡
የዳንኤል ብርሃኔ ደግሞ አይጣል ነው! ምክንያቱም ወላጅ አባቱ የደርግ ኢሰፓ አባል ከነበረ ህወሓት በትግራይ ህዝብ ላይ ተፈፀመ ለሚለው ጭፍጭፋ በቅድሚያ የዳንኤል አባት ተጠያቂ ይሆናል፡፡ ህወሓት ለዳንኤል አባት ይቃርታ ካደረገ ሃ/አለቃ ለገሰ አስፋው እና ኮ/ል መንግስቱ ሃ/ማሪያም ምን አጠፉ ቢባሉ መልስ የላቸውም፡፡ በራሱ አንድ ዓረፍተ-ነገር የመናገር አቅም ያለው ብቸኛው የአብን አመራር #በለጠ ከዚህ በፊት የአምስት ፓርቲዎች አባል የነበር መሆኑ ስታውቅ የብዙ ቡድኖች ልዋጭ እንደሆነ ይገባሃል፡፡
በአጠቃላይ ብሔርተኛ ሲባል በራሱ መቆም የማይችል እንኩሮ ነው!! “አንተ ማን ነህ?” የሚል ካለ እኔ ስዩም ተሾመ ነኝ! ከብሔር በፊት ሀገር የማስቀድም፣ ከዜግነት በፊት ሰው መሆኔ አብዝቶ የሚበልጥብኝ፣ ከጎጥና ሰፈር ብዙ ርቄ በየትኛውም የዓለም ከሚገኝ ሰው ጋር መነጋገርና መግባባት የሚችል፣ እንኳን የብሔር አምላኪ ደናቁርት መላ ሀገሩ ፊቱን ቢያዞርብኝ በደንቆሮዎች መሃል እውነትን እየለፈፍኩ በኩራት የምራመድ፣ ከማንም በላይ ህሊናዬን የምፈራ፣ ራሴን የማከብር ኩሩ ሰው ነኝ፡፡ የምወክለው ራሴን፣ የምናገረው በራሴ፣ ለማንም የማላሽቋልጥ፣ ማንንም የማይለማመጥ፣ በእንከፎች መሃል ብቻዬን በኩራት የምራመድ #ሰው ነኝ!!!
ወለ በል አቦ!!! ሰው ስትሆን ጥራኝ!!!!!!
Filed in: Amharic