>
5:18 pm - Sunday June 16, 6391

ለዶ/ር አሰፋ ከበደ መልስ (ችሎት ዘ ጊንር)

በእውነት ዶ/ር ነህ ? የጠቅላይ ሚ/ሩን ንግግር እኛም ሰምተነዋል ምን አይነት ጆሮ ቢገጠምልህ ነው ወይም ማን ተርጉሞልህ ነው እንደዚህ እንዳሉ እየነገርከን ያለኸው ::እኔ ¨ከሜንት¨ በፍፁም ማድረግ የማልፈልግ ቢሆንም ይህን
ማለፍ አልቻልኩም፡፡ ይሔን የፃፈው እዛ ስብሰባ ውስጥ ያልነበረና ሐሰተኛ ፥ፈፅሞ ሰላም እንዳይሆን የሚፈልግ የውጭ ሰው ነው ብል ይቀለኛል፡፡

ለምሳሌ

1-  “ሐኪምም እንደዚህ በሬ ነው መሆን ያለበት” ጉባኤው ላይ ብትሆን ኖሮ ወይም የመጠቀ አስተሳሰብ ቢኖርህ ኖሮ ፣ ያሉት-> “በሬ ሁሉ ነገሩ ጠቃሚ ነው ፥የሚጣል ነገር የለውም ፥ጅማቱ እንኳን ዜማ ያወጣል የብዙዎችን ልብ
ያጽናናል ይፈውሳል… ሐኪም እንደዚህ ነዉ ፥የሚሰጠውን ጥቅም በዋጋ ልንተምነው አንችልም ማለታቸው መሆኑን ትረዳ ነበር::ምናልባት አንተ የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ብትሆን ፥ታላቁ ሰባኪ ቅዱስ ጳውሎስ አገልጋዮችን ” በሬ” ብሏቸዋል ስለዚህ በቅዱስ ቃል በሬ የክብር ምሳሌ እንጂ የውርደት አይደለም።

2-ስለ መኪና ላነሳኸው፧ እውነት እንደዛ ነው ያሉት ? እንደው ፈጣሪን ባትፈራ ህሊና የሚባል ነገር የለህም?ወይም ሌሎች ፥እኛ በ TV ያሉትን ያልሰማን ይመስልሃል? አገሪቱ መኪና ለያንዳንዱ ትግዛለት ማለት ነው ? ህጻን ልጄን መሰልከኝ ፥ ከሱፐር ማርኬት ብዙ ዕቃ ገዝቼ ስሰጣትና (አይኗ የፈለገውን ሁሉ ማለት ይቻላል)  ፣ ደስ አለሽ? ብዬ ስጠይቃት” አላለኝም ደስ
እንዲለኝ ከፈለክ ሱፐር ማርኬቱን ግዛልኝ”አለችኝ ፤ ወንድሜ- ኢኮኖሚስቶችንም ትንሽ አነጋግራቸው፥ ባጭሩ ደሞዝ መጨመር ማለት ብዙ ጣጣ ያለውና ከባድ መሆኑን ይነግሩሃል፡፡ እናንተ በጥ ቂቱ 10,ዐዐዐ ብትሆኑ 500 ቢጨመርላችሁ በወር 5000000 ይሆናል በአመት 60 ሚሊዮን ይሆናል ለናንተ ሲጨመር-መምህር (የዕውቀት አባት) ይቀጥላል፥ ፖሊስ ፥ ወታደር ይቀጥላል ለወታደር 500 ቢጨመር በግምት ለወታደር ብቻ በአመት (ቁጥሩ 200,000 ብቻ እንኳን ቢሆን)  1ቢሊዮን ሁለት መቶ ሚሊዮን ይሆናል ከዚያ መንግስት ይህን ብር ለማግኘት ግብርና ቀረጥ ይጨምራል፥ አንተ 5 መቶ ሲጨመርልህ ነጋዴው መላው ኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ደሞዝ ተጨመረ ብሎ በያንዳንዱ ዕቃ ላይ በወር ብትደምረው 2ሺ ይጨምራል ፥ይቀጥልና ቤት አከራይህ በትንሹ 5 መቶ ይጨምራል ፦’ዶlር’ እባክህን የኢትዮጵያን ህዝብ ሚሳይል አታስተኩስበት፣ አታስጨርሰን!! ‘የዋጋ ግሽበት’ የሚባል የሆነ አንተ የማታክመው በሽታ በአገሩ ላይ ይመጣል።ለዚህ ነው እሳቸው “አይዞህ
ይጨመራል” ብለው ያልዋሹህና ግለፁን የነገሩህ ” ጣጣውን”እሳቸው በደምብ ያውቁታላ!ቢጠየቅስ አሁን እውነት ጊዜዉ ነዉ? ሰው እየተፈናቀለ የያዝነው ከእጃችን ይበተናል ብሎ ህዝብ ሱባኤ ማን በገባልን እያለ  ሲያማትር አንተ መኪና
ለሦስት ንዱ ተባልን ፥9ሺ ይበቃችኋል ተባልን ትላለህ ?

3-“አባቴ ለነሱ የሚገባቸው ምርቃት ነው” አሉ ብለዋል? እኔ አንተን ፈራሁህ : ልታከም አንተ ጋ ብመጣ እንዴት ላምንህ እችላለሁ ?አባትየው ለታከምኩበት ገንዘብ አልከፈልኩም ወይም አልከፍልም ፥ ገንዘብ ሳይሆን ምርቃት ነው የሚገባህ ያሉ አስመሰልከው ፥ ያሉትን ልንገርህ እኔ ልተርጉመውና ” ሥራችሁ ከገንዘብ በላይ ነው ፥ አሳረፋችሁኝ፥ጤና ሰጣችሁኝ ….
ስለዚህ መርቅልኝ ማለታቸው ነው፥ኢትዮጵያዊ ሥራህን በገንዘብ የማይተካ፥ የበለጠ ሆኖ ሲያገኘው በነፍሱ ፥ በውስጡ፥ በሚያመልከው አምላኩ ስም… ሊከፍልህ ይፈልጋል፥በምርቃት እናም ይሔ የመጨረሻ ታላቅ ስጦታዉ ነዉ፡፡አባቱ ያንን ነው ያደረጉት ፣ጠ/ሚሩም ያንን ነው ያስተላለፉት _፤

በነገራችን ላይ ብዙዎችን  ያስለቀሰውና ልባቸውን የነካው በዚህ ውይይት የጠ/ሚሩ አባት ጉዳይ ነው፡፡ ይሔንን ውብ የነፍስ ምግብ በገንዘብ ፍላጐት አፈር ላይ ልትጥለው ስትፈልግ ፥እዉነትም መጽሐፉ “ገንዘብ የክፋት ሁሉ ሥር ነው” የሚለውን የበለጠ እንዳምን አደረገኝ፣ ምነው እሳቸው እኔን በመረቁኝ ትልቅ “አሜን” እል ነበር::ደግነቱ እድሜዬ እንዲረዝም አባትና
እናቴን እንዳከበር ባልታዘዝ ኖሮ፥  ሃኪም ብቻ ቢሆን እድሜ የሚያረዝመው  ምን ይውጠኝ ነበር። መልካሞቹ ሃኪሞች ግን ጠ/ሚሩ እንዳሉት ሥራችሁ ከምንከፍለው ገንዘብ በላይ ነውና ከልባችን እናከብራችኋለን እናመሰግናችኋለን::

የአገሪቱ የኢኮኖሚ ሁኔታ ሲለወጥ ለበዛ ስቃያችሁና ለምትከፍሉት ዋጋ የሚመጥናችሁ ክፍያ አገሪቱ እንደምተሰጣኝሁ አልጠራጠርም።

Filed in: Amharic