>

ኤርሚያስ፣ ሃብታሙና ብሩክታዊት ላይ የግድያ ሙከራ ተፈፀመባቸው!!! (ናትናኤል መኮንን)

ኤርሚያስ፣ ሃብታሙና ብሩክታዊት ላይ የግድያ ሙከራ ተፈፀመባቸው!!!

(ናትናኤል መኮንን)
በግድያ ሙከራው ላይ ሀብታሙ አያሌውና ብርታዊት ተጎድተው ወደ ሆስፒታል እንደሄዱ የታወቀ ሲሆን ፖሊስ ጉዳዩን እየተከታተለ እንደሆነ ከደቂቃዎች በፊት ኤርሚያስ ነግሮኛል። ከኤርምያስ እንደተረዳሁት ሁኔታው አስፈሪ ነበር በፈጣሪ ሀይል ተርፈናል። ፖሊስ ጉዳዩን እየመረመረው ነው በማለትም ኤርሚያስ አሳውቆኛል።
ተጨማሪ መረጃ፡
ጥቃቱን ያደረሰው አፍሪካን አሜሪካን (ጥቁር ኢትዮጵያዊ ያልሆነ) ሲሆን በመኪና ሁለት ጊዜ ከዞራቸው በኋላ በፍጥነት ከመኪናው በመውጣት መሳሪያ አውጥቶ ሃብታሙ ደረት ላይ ሲደቅን ለመሮጥ ሲሞክሩ ተደነቃቅፈው ሲወድቁ ሀብታሙ እጁ ላይ መጠነኛ ጉዳት ሲደርስበት ብርታዊ  እጇ ተሰብሯል።
ኤርሚያስ በድንጋጤ የወደቀ ሲሆን ጥቃት አድራሹ ወደላይ በመተኮስ የሀብታሙን እና የኤርሚያስን ዋሌት በመዝረፍ ተሰውሯል። ፖሊሲ ክትትል እያደረገ ሲሆን ክሬዲት ካርዳቸውን መጠቀሙ ታውቋል ሁሉም በሙሉ ጤንነት ወደቤታቸው ሄደዋል።
ጉዳዩን ፖሊስ እየመረመረ ሲሆን ስለሁኔታው ተጨባጭ መረጃ እና ማስረጃ ሳይኖራቸው ሆነ ብለው በአሉባልታ የተዛባ መረጃ ከሚያሰራጩ ሸፍጠኞች ተጠበቁ።
ፈጣሪ እንኳን ከክፉ አደጋ ጠበቃቹ!!
Filed in: Amharic