>
5:13 pm - Friday April 19, 1985

በአማራ ሕዝብ ላይ የተከፈተው ዘመቻ በአስቸኳይ ይቁም!!! (ሐይለገብርኤል አያሌው)

በአማራ ሕዝብ ላይ የተከፈተው ዘመቻ በአስቸኳይ ይቁም!!!
ሐይለገብርኤል አያሌው
ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ በነጻነት እንዳበራች ዛሬ ላይ እንድትደርስ የአማራው ሕዝብ መስፈሪያ የለሽ ዋጋ መክፈሉ ታሪክ ምስክር ነው:: ሃገራችን ተስፋፊና ወራሪ ሃይሎችን መክታ ሉዐላዊነቷ አስጠብቃ እንድትኖር የመላው ዜጎቿ ተጋድሎ ውጤት ቢሆንም አማራው ግንባር ቀደም በመሆኑ ለውጪና ለውስጥ ጠላቶች ኢላማ እንዲሆን አድርጎታል:: በዚህም ባለፉት 50 አመታት ግልጽ ጥቃት ተከፍቶበት ብዙ መከራን ሊያስተናግድ ተገዶ ቆይቷል::
በተለይ ባለፉት 28 አመታት አማራው በግልጽ ማንነቱን መሰረት  ያደረገ የጥቃት ዘመቻ ተከፍቶበት ዋጋ ሲከፍል ቢቆይም ከኢትዮጵያዊ ማንነቱ ወርዶ በብሄር ላለመደራጀት በትግዕስት ለመቆየት ሞክሯል:: የመከራው መርግ መክበድ የግፍ መበራከትና የስቃዩ ብዛት ሳይወድ በግድ በብሄር ማንነቱ ተሰባስቦ እንዲመክት ተገዷል::
ሕወሃት ኦነግና ግብረአበሮቻቸው አማራውን ገለን ቀብረነዋል :: አከርካሪው ተሰብሮ እንዳይነሳ አርገን ጥለንዋል:: ቢሉም በማንነቱ መሰባሰብ በጀመረ ማግስት ያሳየው መነሳሳት ጠላቶቹን ከፍተኛ ድንጋጤ ላይ ጥሏቸዋል:: የአማራው መነቃቃትና መደራጀት ለአማራው ብቻ ሳይሆን ጥላቻና የግንጠላ አጀንዳ ያላቸውን የጽንፈኛ ሃይሎችን ሕልም አምክኖ ለመላው ኢትዮጵያዉያን ብሄሮች ሕልውና ጭምር ተስፉ በመሆኑ አደረጃጀቱ እንዲመክን አንድነቱ እንዲበተን በግልጽና በስውር ሰፊ ዘመቻ ተከፍቶበት ቆይቷል::
ይህንንም ተቋቁሞ እራሱን ከማንኛውም ጥቃት ለመከላከል የሚያደርገውን ዝግጅት ለመቀልበስ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በተቀናበረ ሴራና የፖለቲካ አሻጥር መፈንቅለ መንግስት በሚል ሰበብ በአንድ ቡድን የበላይነት በሚመራ የፌዴራል ጣልቃ ገብ ወታደራዊ ወረራ ስር እንዲውል ተደርጏል:: ይህንን በዓለም ታሪክ ተሠምቶ የማያውቅና ፍጹም ግልጽነት የጎደለው ድርጊት በጽኑ እናወግዛለን:: ለሃገር የማይበጅና ሁሉንም ወገን ዋጋ የሚያስከፍልና መሪውን የሚያስጠይቅ እርምጃ ባስቸኳይ እንዲቆም የሕዝቡን መብትና ነጻነት እንዲያከብሩ በጥብቅ እናሳስባለን::
ጠቅላይ ሚንስትሩ ድርጅታቸውና የፌዴራል ካቢኔያቸው ሃገር ሊያፈርስ ሕዝብን ለአመጽ ከሚጋብዝ ድርጊት ተቆጥበው ዘለቄታዊ አብሮነታችን እንዲቀጥልና ሰላማችን እንዲከበር ግልጽና አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ እንጠይቃለን:: የአማራው ሕዝብ የጀመረውን መብቱን የማስጠበቅና ሕልውናውን የመከላከል
ትግል ሳይከፋፈል አንድነቱን አጥብቆና አጠንክሮ እንዲቀጥል ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን::
እንዲሁም :-
1, መፈንቅለ መንግስት በሚል ተራ የቅጥፈት ፖለቲካ ሃገሪቷ ብሄራዊ አደጋ ላይ የወደቀች አስመስሎ በዶር አብይና በመንግስታቸው የቀረበው ዘገባና ፍረጃ  አስቸኳይ የሆነ ማብራሪይ እንዲሰጥበት::
2, ከአማራ ክልል ፍቃድና እውቅና ውጪ በጠቅላይ ሚንስትሩ አዝማችንት በፌዴራል ወታደሮች  የተደረገው ጣልቃ ገብነት ሕጋዊ አግባብነት የሌለው በመሆኑ ውሳኔውን የሰጠው አካል እንዲጠየቅ የፈጸሙትም ድርጊት በነጻና ገለልተኛ አካል እንዲጣራ
3, በአንድ ቡድንና ብሄር የበላይነት የሚመራው ወታደራዊ ካውንስል የሚወስዳቸው እርምጃዎች ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ ባስቸኳይ ከአማራ ክልል ለቆ እንዲወጣ ጸጥታ የማስከበሩን ሃላፊነት ለክልሉ ፀጥታ ሃይል እንዲያስረክብ
4, ከሕግ አግባብና ግልጽ ባልሆነ ምክንያት የታሰሩ የክልሉ አመራሮችና የአማራ ወጣቶች በአስቸኳይ እንዲፈታ ጥፉት አደረሱ የተባሉም ካሉ በግልጽ እንዲዳኙ እንዲደረግ
5, ምንም ባልተጣራ ምክንያት በፌዴራል መንግስት በአማራ ሕዝብና መሪዎች ላይ የተወሰደው እርምጃ : በሃገሪቱ የኢታማጆር ሹምና በጡረተኛው ጀነራል ላይ ምንነቱ ያልታወቀው  ግድያ ገለልተኛና እለም ዓቀፍ አጣሪ ኮሚሽን ተቋቁሞ ሂደቱ እንዲጣራ
6,  ከሕግ አግባብ ውጪ የአማራውን ሕዝብ ትጥቅ የማስፈታት እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲቆም: ሰላም ለማስፈን በሚል ሰበብ በሕዝቡ ላይ የሚደረገው ግድያ በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን::
7, ኢሳት የተባለው ሚድያ ሕዝባዊ ወገንተኛነቱን ትቶ ለገዥዎች ልሳን በመሆን ያልተጣራ ዘገባና ውንጀላን በስፋት በማናፈስ እውነትን ለማድበስበስ ከሚያደርገው እርካሽ ተግባር እንዲቆጠብ ሕዝባችንም የሚዲያ ተቋሙን ቅጥረኛ ተግባር ተረድቶ እንዳይታለል በጥብቅ እናሳስባለን!

ድል ለሕዝባችን!

አቶ ሐይለገብርኤል አያሌው 
ሻለቃ ዳዊት ወልደጎርጊስ
ዶር ዳንኤል ክንዴ
ዶር ሰማህኝ ጋሹ
አቶ ቴዋድሮስ ፀጋዬ
ወ/ሮ ፀሃይ መዝገቡ
አቶ ዳንዔል ሐይሌ
ወ/ሮ ሜሮን አጎናፍር
አቶ ንጉሴ አዳሙ 
አቶ ሚካኤል ሳህሌ
አቶ ይፍሩ ረታ
አቶ ይፍሩ ሀይሉ
ዶር ግርማ ብሩ 
አቶ በላይ ሀይሉ
Filed in: Amharic