>

የኮሎኔሉ አዲሷ የአቋም ቅያስ? (አሰፋ ሃይሉ)

የኮሎኔሉ አዲሷ የአቋም ቅያስ?
(The Colonel’s New Turn?)
አሰፋ ሃይሉ
         – አንዳንድ አበይት ጥያቄዎች
“ይሄ ህገመንግሥት በብዙ መከራ፣ በብዙ ስቃይ፣ በብዙ ደም የተገኘ ነው”፣ “ህገመንግሥቱን የማይቀበል ሰው ለምርጫ መዘጋጀት የለበትም”፣ ወዘተ፣ ወዘተ፣ ወዘተ የምትለዋ የኮ/ል፣ ዶ/ር፣ ጠ/ሚ አብይ አህመድ አሊ አዲሷ የፖለቲካ ቁማር “መቀሌ ላይ መሽጋለች” ካሏት ህወሃት ጋር ጠጋ ጠጋ የማለት የአሰላለፍ ለውጥ ማብሰሪያ አድርገን እንውሰዳት ይሆን?
ይህቺን የአሰላለፍ ለውጥ “ህገመንግሥት፣ ህገመንግሥት” ስትል የኖረችው ህወሀት እጇን ዘርግታ ትቀበለው ይሆን?
የኮሎኔሉ የጀርባ አጥንት ሻዕቢያስ አዲሲቷን የአሰላለፍ ቁማር ታፀድቀዋለች?
“ዳውን ዳውን ወያኔ” ሲል የኖረው የኮሎኔሉ ወካይ ህዝብስ (የፖለቲካ ቤዙ) ይህቺን አዲሲቷን አካሄድ ይሁንታ ይለግሳታል?
“ህገመንግሥቱ ላይ ተሣትፎ አልነበረኝም” የሚል አቋሙን ሲናገር የተደመጠውና ከሰሞኑ የማያወላዳ በትር ከወደ አናቱ ያረፈበት ገትጋታው ብአዴንስ ይህቺ አዲሲቷ ቁማር ትመቸው ይሆን?
ከኮሎኔሉ ጋር ለሀገራዊ ለውጥ በጋራ አሰላለፍ የተወዳጁ የተቃውሞ ፖለቲከኞች ጎራስ የዘር (የብሔር) ፖለቲካን የማዕዘኑ ራስ ያደረገውንና በኮሎኔል አብይ “በመከራ፣ በስቃይ፣ በደም” ተገኘ የተባለለትን ይሄን አዲሱን “አምልኮተ ዘ ኢፌዲሪ ህገመንግሥት” የፖለቲካ ቁማር ይዋጥላቸው ይሆን?
ይህቺን የኮሎኔል አብይ አህመድ አሊን አዲስ የቅያስ ጅማሮ “አዲሷ የጠቅላዩ ገፅ” ብለን እንውሰዳት? ወይስ “ጊዜ የገለጣት እውነተኛዋ የጠቅላዩ ገፅ” ተብላ ትወሰድ? ወይስ ሁሉንም “ሆድ ይፍጀው”? “ጊዜ ይፍታው”?
ጥያቄዎችን እንጂ መልሶችን ይዤ አልመጣሁም።
ጨርሼያለሁ።
ስድስት ነጥብ።
Filed in: Amharic