>
5:13 pm - Friday April 19, 2791

በኦሮሙማ  አስተሳሰብ ኢትዮጵያን ማፍረስ እንጂ ማስተዳደር አይቻልም! (አቻምየለህ ታምሩ)

በኦሮሙማ  አስተሳሰብ ኢትዮጵያን ማፍረስ እንጂ ማስተዳደር አይቻልም!
አቻምየለህ ታምሩ
ለሁሉ ነገር እርሾ ያስፈልገዋል። አገር ለምራትም እንደዚያው። ለልጅ መፈጠር የእናት ማሕጸንና የእንቁላል አስኳል እንደሚያስፈልገው ሁሉ ለማንኛውም አካል ለመፈጠርና ለማደግ የተመቻቸ መነሻ ያስፈልገዋል። እነዚህ እርሾዎች ሳይመቻቹ አዲስ፣ ተተኪ ወይም የተሻለ ፍጥረት ሊመጣ አይችልም። አገሮች የሚፈጠሩበት፣ ቀድመው ከነበሩበት ሁኔታ ለማሻሻል ወይም በተሻለ ለመተካትም ቢሆን የሚሳካው ያንን የሚያመቻች አስኳል ነገር አልያም እርሾ  ሲኖር ብቻ ነው።
አንድ የጦር መሪ አገሮችን ወግቶ በቁጥጥሩ ውስጥ ስላደረገ ብቻ አገር አይመሰረትም፣ መምራትም አይቻለውም። ይህ ባገራችም፣ በውጪም አገሮችም የታየ ታሪክ ነው። የግሪኮችን፣ የሮማን፣ የእንግሊዝን፣ የአሜሪካንን፣ የሩሲያን፣ የጃፓንን ታሪክ ብንመለከት አገሮቹ የተፈጠሩት አስኳል የሚሆን ምቹ ሁኔታ ስለነበራቸው፤ ካልነበራቸው ከሌላ አገር እንደ እርሾ በመዋስ ነው። ድሮ የንጉሣዊ ቤተሰብ ያልነበራቸው አገሮች አገር ለመመስረት ሰማያዊ ደም ያለውን ከሌላ አገር አንዳንዴም ከባላንጣ አገር ይዋሱ ነበር። የዛሬው የኖርዌይ ንጉሣዊ ቤተሰቦች የመጡት ከድሮ ገዢዎቻቸው ከዴንማርክና እንግሊዝ ነው። ካናዳ እንደ አገር የቆመችው ከእንግሊዝ አገር ዘውድ ተውሰው የአገራቸው ምልክት በማድረግ ነው።
ሕገ መንግሥቶችንና የሕግ ስርዓቶችን የወሰድን እንደሆነም ታሪኩ ተወራራሽ ናቸው። ሌሎች ባሕሎች የራሳቸውን ተጽዕኖ ወይም አስተዋጽዖ ቢያደርጉም የመጀመሪያው እርሾ ለምን ኖረ የሚል ጥያቄ ግን አያስነሳም። ያለፉት አንድ ሺሕ ዓመታትና እስከ ዛሬም ያለውን የኢትዮጵያን ታሪክ መለስ ብለን ካየነው የሚነግረን ይህንኑ ነው።
ዮዲት ባካሄደችው አብዮት የኔ ያለቻቸውን ጎሳዎች ወደ ስልጣን ቢያወጣም ወደ ስልጣን የመጡት ግን አገር በመምራት ኢትዮጵያን ማስተዳደር አልቻሉም፤ ስለዚህ ራሳቸውን ስልጣኑን ለሚመራ ማስተላለፍ ብቻ ሳይሆን በመጨረሻ ያለጦርነት ዘውዱን አሳልፈው ሰጥተው ሄዱ። ግራኝ አሕመድ ጦሩን ይዞ የኢትዮጵያን ግዛት መቆጣጠር ቢችልም፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ መያዝ የሚችል ባሕላዊም ሆነ ስነልቦናዊ ዝግጅት ስላልነበረው ሌላውን ማጥፋት እንደ አማራጭ ወስዶ መጨረሻ ሳይሳካለት ቀርቷል።
ከግራኝ በኋላ በመላው ኢትዮጵያ እንደዋርካ የተስፋፉት አባገዳዎችም ከሶስት መቶ አመታት በላይ እየተስፋፉ የአገሪቱን ለም መሬት በቁጥጥራቸው ስር ሲያደርጉ ከሌላው ጋር አብሮ፣ አክብሮ ለመኖር ምንም ፍላጎት አልነበራቸው። ስለዚህ የነበረውን ዘር ሁሉ ማጥፋት እንደአማራጭ ወሰዱት እንጂ ሁሉንም እንዳባቱ የሚኖርበት አገር አልገነቡም። ባለፉት ሀያ ስምንት አመታት ስልጣን ላይ  የነበሩት ወያኔዎችም በዘር ተደራጅተው በመንግሥትነት ቢሰየሙም በሀያ ሰባት አመታት ውስጥ ያደረጉት ነገር ቢኖር  የዐፄ ይኩኖ አምላክ መንግሥት ወደ ስልጣን ተመልሶ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 1966 ዓ.ም. ድረስ ለ 750 አመት ያልተካሄደ መዝረፍና ማፈናቀል በ27 ዓመት  ውስጥ መዝረፍና ማፈናቀል ነው። እነዚህ ዘራፊዎች ሀብታችንን ጨርሰው ኩላሊታችን ወደ መዝረፍ ገቡ እንጂ አገር ለመገንባትና ማስተዳደር  ችሎታምም  ፍላጎት ፍላጎት እንዲሁም የሥነ መንግሥት አስተሳሰብ  አልነበራቸውም።
ብሔርተኛነት እንደ እሳቤ የያዙ ሁሉ አላማው የሌላውን ነጥቆና ተቀራምቶ  የራስ ብቻ የማድረግ የቅሚያ፣ የወረራና የመውረስ እንቅስቃሴ እንጂ ከእኩልነትና መብት ትግል ጋር የሚያገናኘው አንዳች ግብ የለውም። ኦሮሙማን ታጥቀው በመንግሥትነት የተሰየሙት እነ ዐቢይም  አላማቸው እንደዚያው ነው። ለዚህም ነው የእነ ዐቢይ የአፓርታይድ አገዛዝ ፋሽስት ወያኔ 27 ዓመታት የፈጀበትን የቅድሚያ፣ ወረራና የመውረስ ክብረ ወሰን በአስር ወራት ውስጥ የሰበረው።
ሲጀመር እነ ዐቢይ መንግሥታዊ ያደረጉት የኦነጋውያን ኦሮሞማ ፖለቲካ ሳይሆኑ ዘረፋን፣ ወረራንና ቅርምትን የትግል ዓላማው የሚያደርግ የወንጀል ተግባር ነው። የኦሮሙማው ፈጣሪዎች ኦነጋውያን ራሳቸው ፖለቲከኞች ሳይሆኑ ዘረፋን፣ ወረራንና ቅርምትን የትግላቸው ዓላማ ያደረጉ፣ ሕጻናትና ሴቶችን ሲሰልቡና ሲዘርፉ የኖሩ፣ አቅመ ደካሞችን ሲያፈናቅሉ የኖሩ ተራ ማጅራት መቺዎች ናቸው። ኦነጋውያን ሁሉ የሥነ መንግሥት አስተሳሰብ የሌላቸው  ወሮበሎች ናቸው። ኦሮሙማን መርሁ ያደረገው ዐቢይ አሕመድና ድርጅቱ በመላው ኢትዮጵያ ላይ በመንግሥትነት ተሰይመው አገር ከዳር እስከ ዳር እየገዙ «አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት» የሚሉን የሁሉ መንግሥት ሆነው እንኳን የዘረፋ፣ የወረራና የቅርምት ፖለቲካቸው አባዜ አልለቃቸው ብሎ ነው።
የኦነጋውያን ኦሮሙማ ማዕከሉ ዘረፋ፣ ወረራና ቅሚያ ስለሆነ አዲስ አበባን ዳግማዊ ምኒልክ ከመምስረታቸው በፊት የነበሩት ኦሮሞዎች አይደሉም የሚለው የታሪክ እውነት ደንታ አይሰጣቸውም። በዚያ ላይ በአዲስ አበባ ዙሪያና በመላው አገሪቱ የሚገኘው ኦሮምኛ ተናጋሪ ሁሉ ኦሮሞ አለመሆኑን የራሳቸው ሰዎች እንኳ ያጠኑትን ታሪክ ለመቀበል ዝግጁ ያልሆኑ ሕመምተኞች ናቸው። በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ኦሮሞዎቹ ወራሪዎቹ አባገዳዎቹና የነሱ ዘመዶች ብቻ ናቸው። ነባሩ ሕዝብ ኦሮምኛ እንዲናገር የተደረገው  ተገዶ ኦሮምኛ  ስለተናገረ  ኦሮሞ ነው ማለት አይደለም።
ኦሮምኛ የሚናገረው ሁሉ ኦሮምኛ እንዳልሆነ እውነተኞቹ ኦሮሞዎቹ ራሳቸው  ምስክር ናቸው። በእውነተኞቹ ኦሮሞዎች  ትውፊት ውስጥ  «Salgan Borana, sagaltamman gabra» የሚል አባባል አለ። ይህ ወደ አማርኛ ሲተረጎም «ዘጠኙ ኦሮሞ ነው፤ ዘጠናው ገርበ ነው» ማለት ነው። ገርበ  ኦሮሞ ሲስፋፋ ያስገበራቸውንና ባርያ ያደረጋቸውን ነገዶች የሚጠራበት ስያሜ ነው። በኦሮሞ በራሱ  ትውፊት መሰረት  ዛሬ ኦሮምያ በሚባለው ክልል ውስጥ ከሚኖረው  ኦሮምኛ ተናጋሪው  ሕዝበ መካከል ትክክለኛው  ኦሮሞ ከአስሩ አንዱ ብቻ ነው ማለት ነው። ከአስሩ  ዘጠኙ ገርበ ወይም በአባገዳዎች በወረራ የተያዘና በኃይል ኦሮሞ የተደረገ ሕዝብ ነው።
ይህንን እውነት ከኦሮሞዎች ትውፊት በተጨማሪ ዛሬ በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል። የሰላሌና አምቦ ሕዝብ የDNA ውጤት እንደሚያሳየው  ዝምድናው ከምንጃርና ወይም ጅሩ ሕዝብ ጋር እንጂ ከቦረና (እወነተኛው ኦሮሞዎች) ጋር አይደለም።  ከዚህ በተጨማሪ ፖል ሶሊሌት የተባለው የፈረንሳይ ጎብኝ እ.ኤ.አ. በ1884 ዓ.ም. ሸዋን ጎብኝቶ በጻፈው የጉዞ ማስታወሻው በሰላሌና ጃርሶ ውስጥ ኦሮሞ ገርበ ያደረጋቸው የአካባቢው ቀደምት ባለይዞታዎች አማሮች እንደሆኑ ጽፏል።
የአርሲ ሕዝብ ዝምድናው ከሐዲያ ጋር እንጂ ከቦረና ጋር አይደለም። ጀርመናዊው የታሪክ ምሁር በርካምበር እንዳጠናው ከአርሲ ሕዝብ ሁለት ሶስተኛው ሐድያ ነው። የጅማ ሕዝብ ከየምና ከከፋ ሕዝብ እንጂ ከኦሮሞ ጋር ምንም ዝምድና የለውም። አባጅፋር ራሱ አረብ እንጂ ኦሮሞ አይደለም። ወለጋ እውነተኛ ኦሮሞዎች ከመቶ አስርም አይሞሉም። እውነተኛ ኦሮሞዎቹ ለባሪያ ፍንገላና ውሀና ሳር ፍለጋ መጥተው ሌላውን ገርበ አድርገው የቀሩት አባገዳዎችና ልጆቻቸው ብቻ ናቸው።
የትኛውም ብሔርተኛ ቢሆን አገር ማፍረስ እንጂ አገር ማስተዳደር አይቻለውም። በየትኛውም አለም ብሔርተኛ ሆኖ በመንግሥትነት ተሰይሞ አገር ሲያፈርስን እንጂ አገር ሲያረጋጋና ሲያስተዳድር ታይቶ ተሰምቶ አይታወቅም። በኢትዮጵያም ሆነ በአለም ታሪክ በብሔርተኛነት እሳቤ በመንግሥትነት ተሰይሞ አገር የማስተዳደር እርሾና የሥነ መንግሥት እሳቤ ያለው አገዛዝ የለም። የኦሮሞ ብሔረተኞም ዓላማቸው ወንድምን በወንድም ላይ እኅትን በእኅት ላይ በማስነሳት የኦርሞ ኤምፓየር ቅዠታቸውን ማሳካት እንጂ ኢትዮጵያ የምትባልን  አገር የማስተዳደር ፍላጎት፣ እርሾና የሥነ መንግሥት እሳቤ የላቸውም።
ከነገዳቸው ውጭ ያለውን የተቀረውን ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ይዞ ለመቆየት የሚያስችል ባሕላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ እሴት እንዲሁም የሥነ መንግሥት አስተሳሰብ የሌላውን ዘረፋን፣ ወረራንና መውረስን ፖለቲካቸው ያደረጉ ያበዱ ብሔርተኞች መንግሥት ይሆኑናል ብሎ ማሰብ ውሻ ነከሰኝ ብሎ ለጅብ አቤት እንደማለት አይነት የዋህነት ነው። ብሔርተኛ ሁሉ አገር ማፍረስ እንጂ አገር ማስተዳደር እንደማይችል ያለፉት አርባ አራት አመታት የኢትዮጵያ የቁልቁለት መንገድ ምስክር ነው። ልክ በቅሎ እንደማትወልድ ሁሉ የነገዱ ሳይሆን የኢትዮጵያ ስነ መንግሥት እሳቤ የሌለው፣ ከነገዱ  ውጭ ያለውን የተቀረውን ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ይዞ ለመቆየት የሚያስችል ባሕላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ እሴት ያልያዘ ማናቸውም አይነት  የሁሉም መንግሥት የመሆን ችሎታ የለውም። ያለው ችሎታ ቢኖር እንደ ወያኔና ኦነግ  የሌላውን መዝረፍ፣ መቀማት፣ መቀራመትና መውረስ ብቻ ነው። ይኼው ነው።
Filed in: Amharic