>

ሐዋሳ በቶክስ እሩምታ እየተናጠች ነው...!  (አባይ ሚድያ)

ሐዋሳ በቶክስ እሩምታ እየተናጠች ነው…!
 አባይ ሚድያ
 
በሀዋሳ መትረየስ ከጫኑ ተሽከርካሪዎች በስተቀር ዋና ዋና መንገዶች ጭር ብለዋል!!!
በሀዋሳ ከተማ በተለምዶ ጉዱማሌ በመባል በሚታወቀውና በከተማዋ የሀይቅ ዳር ክፍለ ከተማ 05 ቀበሌ በሚገኘው የሲዳማ መሰብሰቢያ ሜዳ የተሰበሰቡ በከተማዋ ዙራያ ካሉ የሲዳማ ዞን ወረዳዎች የመጡ ወጣቶች ከመከላያከያ ጋር በፈጠሩት ግጭት መከላከያ ሰራዊት ላይ ጉዳት በመድረሱ መከላከያም አፀፋዊ እርምጃዎች እየወሰደ ይገኛል::
 
 ሎቄ ተብሎ ከሚጠራው የከተማዋ ጥግ አንስቶ ግጭቱ የተፈጠረበት ጉዱማሌ የተባለውና አሞራ ገደል አካባቢ እስካለው መንደር ድረስ ከፍተኛ የተኩስ እሩምታና ግርግር እየተስተዋለ ነው::
መትረየስ የሚባለው መሳሪያ የተጠመደባቸው የደቡብ ክልል ፣ የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ ሰራዊት ተሽከርካሪዎች በከተማዋ የተለያዩ ክፈሎች ቅኝት ሲያድረጉ ይታያሉ።
 የኢቲዮ እና የሀበሻ ባስ የአክሲዮን ማሀበር የሀዋሳ ቅርንጫፍ አስተባባሪዎች ምክንያቱ ከጸጥታ ስጋት ጋር የተያያዘ መሆኑን ባያረጋግጡም ዛሬ ከሀዋሳ ከተማ የሚነሱም ሆነ ወደ ከተማው የሚገቡ መደበኛ የህዝብ ማመላለሽ አገልግሎት ስምሪት አንደሌላቸው አረጋግጠዋል። በከተማው የሚገኙ የንግድ አግልግሎት መስጫዎች ተቋማት በከፊል ተዘግተው የሚታዩ ሲሆኑ ባንኮች ግን እንደወትውሮው ተግልጋዮቹ ባይታይባቸውም ክፈት ሆነው ተስተውለዋል።
  የሲዳማ ህዝብ በክልል ለመደራጀት የዞኑ ምክር ቤት ውሳኔ ከሳለፍ ዛሬ ሀሙስ ሀምሌ 11 አንደኛ ዓመቱን አስቆጥሯል ። ጥያቄው በቂ ምላሽ እልተሰጠውም ብለው የሚያምኑ አካላት ክልሉን በራሳቸው ለማወጅ የሚያድርጉት እንቅስቃሴ ወደ ግጭት ሊያመራ ይችላል በሚል በከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ ስጋትን አሳድሮ ይገኛል።
 
ምንጭ:- (የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች
Filed in: Amharic