>
12:51 pm - Sunday December 4, 2022

ሃዋሳ – ወላይታ – ሚኒሶታ – አስመራ – ዋሽንግተን ዲሲ (ዘመድኩን በቀለ)

 አጫጭር መረጃዎች!!!
 ዘመድኩን በቀለ

 ~ ሃዋሳ – ወላይታ – ሚኒሶታ –አስመራ – ዋሽንግተን ዲሲ።

•••
የ11/11/11 ትራጄዲ ፊልም ደራሲዎች ዛሬ በፊልሙ ምርቃት ቀን በሀገር ውስጥ የሉም። ከእሳቱ ወላፈንም ሸሽተው ወደ አስመራና ወደ ሚኒሶታም አቅንተዋል ተብሏል።
•••
ጃ-War ወደ ሚኒሶታ የሄደው አንድም ፈርቶና ደንግጦ ሲሆን በሌላም የናፈቃቸውን ሚስቱንና ልጁን ህጻን ኦሮሞ ጃዋርን ለመጎብኘት ነው የሄደው የሚሉም አሉ።
•••
ዛሬ ጠዋት አራት ኪሎ ከሚገኘው የሚኒሊክ ቤተ መንግሥት በማለዳ ተነስተው ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮጵላን ጣቢያ ያቀኑት ጠሚዶኮ ዐቢይ አህመድ ብዙዎች ወደ ሃዋሳ ሄደው ውጥረቱን ሊያረገግቡ ይሆናል በማለት የገመቱ ሲሆን አቢቹ የተሳፈረባት አውሮጵላን ግን ፊቷን ወደ ሰሜን አቅጣጫ አዙራ ወደ ኤርትራ ወስዳ ሳያስቡት አስመራ ጥላቸዋለች ተብሏል።
•••
ብልጡ የአስመራው ተጓዥ አቢቹዋችን እንደተለመደውና ሁልጊዜ እንደሚያደርገው “ በደቡብ ክልል ዛሬ ለመጥበጥ ቀጠሮ የያዘውን ህዝብ ሲዝቱበት በመክረማቸው አለቃቸው ጃዋር ግን በጉልበትም ቢሆን ሲዳማን ክልል እናደርጋታለን የሚለውን ዛቻና በዚህ የተነሳ በሃዋሳ የሚፈጠረውን ችግር ባላየ ባልሰማ ልክ እንደ ለገጣፎና ቡራዩው “ አልሰማሁም አላየሁም፣ አልነበርኩም” ለማለት ነው የተሸበለሉት ተብሏል።
•••
ለኤርትራ የነፃነት ቀን አስመራ ሳይሄድ ደብዳቤ የላከው ሰውዬ ካልጠፋ ቀን 11/11/11 ን መርጦ ዛሬ ሐምሌ 11 ራሱ በአካል መሄዱም ብዙ ጥያቄዎችን አጭሯል። ይሄ ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ተብሎ ወደ አስመራ የተደረገው ጉዞ ከአዋሳው ውጥረት ለማምለጥ ብቻ ሳይሆን እንደኔ እንደእኔ ጥርጣሬ ደግሞ ኤርትራ ወደ ትግራይ ድንበር ያስጠጋችውን ጦር በፍጥነት እንድትገፋበት ከአለቃው ከኢሱ ጋር ለመመካከር ነውም በልበል ያሰኘኛል። ምክንያቱም ትግራይንና ዐማራን በጄነራል አሳምነው ጽጌ በኩል ጦርነት እንዲፈጥሩ እናደርጋለን ብለው ያስቡ የነበሩት አባቶርቤዎች እንዳሰቡት ዐማራና ትግራይ ወደ ጦርነት አልገባ ስላሉዋቸው እነ ዶር አምባቸውንና ጄነራል አሳምነው ጽጌን አስወግደው አሁን በሻአቢያ በኩል ትግሬን ለማንበርከክ፣ ዐማራንም ለመጥበጥ ሊሞክሩ ይመስለኛል።
“ ጎበዝ አሁን የገጠመን ፈተና ከዛሬ 500 ዓመት በፊት ከገጠመን ፈተና በእጅጉ የከፋ ነው” ይህቺ ቃል ናት ጄነራል አሳምነው ጽጌን ሳይዘጋጅበት ያስገደለችው።
“ አሳምነው ጽጌ በኢትዮ ኤርትራው ጦርነት ጊዜ በባድመ ግንባር ተሰልፎ ጦሩን በመምራት ኢትዮጵያንም ትግሬንም ነፃ ያወጣ፣ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማንም በባድመ ያውለበለበ ጀግና ነበር። ወደፊት በጀነራል አሳምነው ሞት የሳቁ ትግሬዎችና ዐማሮች መቃብሩ ድረስ ሄደው ማረን ይቅር በለን የሚሉበት ዘመን ይመጣል የሚሉም አሉ።
•••
ምስኪኖቹ ተዋንያንና ራሳቸውን ኤጄቶ ብለው የሰየሙት የሲዳማ ወጣቶች ግን በተመልካች ታዛቢዎች ፊት ዛሬ በሃዋሳ ከተማ በሃዋሳ ፖሊስ ድጋፍ ሰጪነት የንፁሐን ዜጎችን ድርጅቶችና ቤቶች በማቃጠል እሳቱንም በመሞቅ ምስኪኖችን ደም እንባ ሲያስለቅሱ መዋላቸው እየተነገረ ነው።
•••
የሃዋሳው ፖሊስ የኦሮሞው ቄሮ በእነ ኦቦለማና ዐቢይ አህመድ ድጋፍ ሰጪነት ወደ ሥልጣን እንደመጣ ስለሚያውቅ የሲዳማው የአቶ ሚልዮን አስተዳደርም በቄሮ ስታይል ህዝብና መንግሥትን በኤጄቶ አስደንግጦ ሽብር በመፍጠር ሲዳማን በመገንጠል የአዲሲቷ ክልል የሲዳማ መሪ ለመሆን ይፈልጋል እየተባለም ነው። ለዚህ ነው የሲዳማ ፖሊስ ለእሳት አንዳጁ ኤጄቶ በሃላል ድጋፍ ሲሰጥ የሚታየው። ደቡብ ዛሬ ዘረፋ የተጧጧፈ ሲሆን ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በተፈጠረ ግጭት 1 ሰው ሞቶ ብዙዎች ቆስለው ሆስፒታል መግባታቸው ተነግሯል።
•••
 ዛሬ በሲዳማ ዞን በተለይ በለኩ በአለታ ወንዶ፣ በጩኮ፣
ብዙ የንግድ ድረጅቶችና መኖሪያ ቤቶች ተዘርፈዋል፣ ተቃጥለዋልም ተብሏል። በተለይ ቀደም ብለው መጤ ተብለው በተመረጡ የዐማራውና የጉራጌ ነገድ የንግድ ድርጅቶች ትኩረት ተደርጎባቸው ውለዋል። ከዘረፋው እና ከማውደሙም በተጨማሪ ብዙዎች በድብደባም ብዙ ጉዳት እንደደረሰባቸው የመገናኛ ብዙሃን እየገለጡ ይገኛሉ። ነገሩ በጊዜ ካልቆመ ነገና ተነገ ወዲያም በከፋ ሁኔታ እንዳይቀጥል ብዙዎች ስጋታቸውን ሲገልጡ ተስተውሏል።
•••
ኤጄቶን ጃስ ያሉት ቄሮዎችም በቁጥር ጥቂት ሆነው የኦነግን ባንዲራ ይዘው ሃዋሳ ገብተው በከተማው እየበጠበጡ ለኤጄቶ ድጋፍ ሲሰጡ የታዩ ሲሆን መቐለ የመሸገችው ህወሓት ለጊዜው በምን ዓይነት መልኩ ኤጄቶዎችን እየረዳቻቻው እንደሆነ እስከአሁን አልታወቀም። በአጠቃላይ ህወሓቶች እንደ ኦነጎች እስከ አሁን ኤጀቶን ለመርዳት በግልጽ ሲንቀሳቀሱ አልታዩም። “ ካስፈለገ በኃይልና በጉልበት ” ብሎ ጃስ ያላቸው ጃ -War ግን ወደ ሚኒሶታ አቅጥኖታል።
•••
ከዚህ በፊት በህወሓት አግአዚ ጦር የተጨፈጨፈው የሲዳማ ህዝብ አሁን ደግሞ ያቺው ጨፍጫፊ መቀለ ተቀምጣ አዛኝ ቅቤ አንጓች ሆና ሲዳማ ክልል መሆን አለበት ስትል ሲዳማ የዋሁ እውነት መስሎት ባይታለል ይመከራል። የሲዳማ ህዝብ ግን ሁለቴ በእሳት ሊማገድ ነው ማለት እኮ ነው። በቀድሞው ሥርዓት በመለስ ዜናዊ ጦር አሁን ደግሞ በኦቦ ለማ መገርሳ የኦህዴድኦነግ ጦር ደሙ ደመ ከልብ ሆኖ በከንቱ ይፈስ ዘንድ የተፈረደበትም ይመስላል። ቢረጋጉ ይሻላቸው አይመስላችሁም። እኔ ቢረጋጉ መልካም ይመስለኛል።
•••
በሌላ ዜና ከዚያው ከደቡብ ሳንወጣ በወላይታ ሶዶ ከተማ የዐቢቹ መንግሥት ለራሱ ሲል ሲዳማን በመገንጠል ደቡብን ካፈረሰ አይቀር እኛስ ከማን እንሰን ነው ክልል የማንሆነው በማለት በዛሬው ዕለት የቀድሞውን የደበቡብ ክልል ባንዲራ እንደ አስከሬን ተሸክመው ከተማውን ሲያዞሩት ውለው በመጨረሻም ቤንዚን አርከፍክፈው ሲያቃጥሉት ታይተዋል። ወላይታ ግልገል ነፍጠኛ ተብሎ በፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች መደቡን ከጉራጌና ከዐማራ ነገድ ጋር መድበው የሚወቅጡት ኢትዮጵያዊ ነገድ ነው። ለዚህ ደግሞ ታዲዮስ ታንቱ ምስክር ነው።
•••
እዚያው ደቡብ በመሎ ለሃ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሚካኤል ደብር አገልጋይ ካህናትና ምእመናንን የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ በሆኑት አስተዳዳሪዎች መሪነት የቤተክርስቲያኗ ካህናትና ምእመናን እየተደበደቡ መሆናቸውም እየተነገረ፤ በአካባቢውም የተኩስ ድምጽ እየተሰማ መሆኑ ተነግሯል። እስከአሁን ስለደረሰ የሞት ጉዳት የተሰማ ነገር የለም።
•••
በመጨረሻም የዳያስፖራው የጫጉላ ሽርሽርና ያደረ ስካር በርዶለት ለመጀመሪያ ጊዜ የዐቢቹን መንግሥት በመቃወም በዋሽንግተን በኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ሲያካሂዱ ውለዋል። ይሄ ለአቢቹ መንግሥት ጥሩ ሚልኪ አይመስልም። አንድ ዓመት ሙሉ በነፃነት በአሜሪካ ምድር ሽር ብትን ሲሉ የከረሙት የኢትዮጵያ መንግሥት ባለ ሥልጣናት እንደፈረደባቸው መደበቅ ሊጀምሩ ይመስላል። ምክንያቱ ደግሞ የዲሲ ግብረ ኃይል የሚባለው ስብስብ በዛሬው ስብሰባ ላይ መገኘቱ የዳያስፖራውን ትእግስት ማለቅ አመልካች ነው ተብሏል። በእዚህ ሰልፍ ላይ ታማኝ በየነ ይገኝ አይገኝ የታወቀ ነገር የለም። አይ ማኖ መንካት።
•••
እዚያው በአሜሪካ የኦነግን ባንዲራ የያዙ የኦሮሚያ ሀገር ዜጎችም ኢትዮጵያውያኑን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ታይቷል። በመፈክራቸውም እስክንድር ነጋ አሸባሪ ነው። ተመስገን ዳሳለኝ አሸባሪ ነው ሲሉ መዋላቸው ታይቷል። አይ ተረኝነት። ድሮ ህወሓት ነፍሴ ነበረች እንዲህ መከራዋን የምትበላው። አሁን ኦነግ ሆኗል እዬዬ ባዩ።
•••
ይሄ በእንዲህ እያለ ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናት አባቶች ዝምታን መርጠዋል። የሌለ ለሽ ብለው ተኝተዋል። ጮጋ ነው ያሉት። ገሚሱ ጳጳስ ባላየ ባልሰማ ችግኝ ተከላ ዜና ይሠራል። ገሚሱ ማኅበር ሀገር ቀውጢ ሆኖ ሲምፖዚየም ኤግዚቢሽን ያዘጋጃል።
•••
ሰላም ለኢትዮጵያ! ሰላም ለሃገራችን ! 
•••
ሻሎም !  ሰላም !
ሐምሌ 11/11/11 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።
Filed in: Amharic