>

የኤጄቶ መሪ ታሪኩ ለማ ታሰረ!!! (ስዩም ተሾመ)

የኤጄቶ መሪ ታሪኩ ለማ (Tare_W_Lemma) ታሰረ!!!
ስዩም ተሾመ
ከታሪኩ ለማ ጋር ለመጀመሪያ ግዜ የተገናኘነው አዲስ አበባ በሚገኘው የOMN ስቱዲዮ በተካሄደ የውይይት ፕሮግራም ላይ ነበር። በውይይቱ ላይ የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ የሲዳማዎች ጉዳይ ብቻ አድርጎ መውሰድ እንደሌለበት በተደጋጋሚ ልነግረው ሞክሬ ነበር። ነገር ግን ጀማሪ ብሔርተኝነት እውነታን ከማየት፣ የተለየ ሃሳብን ከመስማት ይጋርዳል። በሌላ በኩል የፖለቲካ ጥያቄን በጉልበት እና ስሜት ለመመለስ መሞከር አደገኛ ነው። ታሪኩ ለማ ይህን አደገኛ መንገድ በመከተል ህዝባዊ ንቅናቄ ለመፍጠርና የሲዳማን ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ጥረት አድርጓል። ተጨባጭ ሁኔታን ከግምት ባላስገባ መልኩ በስሜትና ጉልበት ሲመራው የነበረው እንቅስቃሴ በንፁሃን ህይወትና ንብረት ላይ የከፋ ጉዳት አስከትሏል። ይህን ተከትሎ ከቀናት በፊት ታሪኩ ለማን ጨምሮ ሌሎች የኤጄቶ መሪዎች በሐዋሳ ከተማ መካነ እየሱስ ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ በድብቅ ስብሰባ በማካሄድ ላይ ሳሉ በፀጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለማወቅ ተችሏል።
Filed in: Amharic