>

ያንዳርጋቸው ፖለቲካዊ ሸፍጥ (መስፍን አረጋ)

ያንዳርጋቸው ፖለቲካዊ ሸፍጥ

መስፍን አረጋ

የኢዜማ አሽከርካሪ (brains behind) ነው የሚባለው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በጦቢያ ውስጥ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ሱማሌ ፣ አገው፣ ቅማንት ወዘተ. እንጅ አማራ የሚባል ብሔር የለም የሚባለውን እሱ ራሱ ከጻፈው መጽሐፍ ጋር ፍጹም የሚቃረነውን የፀራማሮች መሠረተቢስ እንቶ ፈንቶ እንደወረደ ፈንትቶታል፡፡ የዚህን መሠረተቢስ እንቶ ፈንቶ አመክንዮ (reasoning) እንከተል ብንል እንግሊዘኛ የአንግሎወች (Angles)፣ የሳክሶኖች (Saxons)፣ እና የሌሎች ቱቶኒክ ጎሳወች (teutonic tribes) ጭምቅ ውጤት ስለሆነ እንግሊዛዊ (English) የሚባል ዘር የለም ከሚል አስቂኝ ድምዳሜ ላይ እንምንደርስ የእንግሊዝ ዜግነት ያለው አንዳርጋቸው አይጠፋውም፡፡ ስለዚህም መሠረታዊው ጥያቄ እንቶ ፈንቶውን ያምንበታል አያምንበትም ሳይሆን፣ ባሁኑ ጊዜ ለምን ፈነተተው የሚለው ነው፡፡ ምክኒያቱ ምንድን ነው?

አንዳርጋቸውና ብርሃኑ የኢሕአፓ ሰወች (ኢሕአፔወች) ናቸው፡፡ ባበርካታ የኢሕፔወች ዘንድ ደግሞ ወደ ስልጣን የሚያመራ እስከሆነ ድረስ የማይኬድበት መንገድ የለም፡፡ ለስልጣን ሲባል የገዛ ቤተሰብን መግደል፣ ምሁራንን መረሸን፣ ወጣቶችን ማስጨፍጨፍ፣ ሕጻናትን መማገድ፣ ዓላማን የሚያሳካ የውሸት ትርክት መፍጠር፣ አገር ማስገንጠል፣ ካገር ጠላት ጋር መመሳጠርና መተባበር፣ በጀርባ መውጋት፣ በማጅራት ማረድ የተፈቀዱ ብቻ ሳይሆኑ ግዴታወችም ናቸው፡፡ የሂወታቸው አሌፍና ፓሌፍ (alpha and omega) ስልጣንና ስልጣን ብቻ ነው፡፡
• የአንዳርጋቸው ኢዜማ በትረ ስልጣን ለመጨበጥ ያቀደው በዜግነት ፖለቲካ ነው፣ ያለው አማራጭ ይሄውና ይሄው ብቻ ነውና፡፡
• ባብዛኛው ደረጃ ኦሮሞወችና ትግሬወች በብሔርተኝነት እንጅ በዜግነት ፖለቲካ የማያምኑ ኦነጋውያንና ወየንቲወች ናቸው፡፡ ከጦቢያ ትላልቅ ብሔረሰቦች (አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ሱማሌ) ውስጥ ከሞላ ጎደል ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በዜግነት ፖለቲካ የሚያምነው አማራ ብቻ ነው፡፡ ጦቢያዊነት ያለ አማራ፣ አማራ ያለ ጦቢያዊነት አይታሰቡም፡፡ ጦቢያዊነት የሚጠነክረው አማራ ሲጠነክር፣ አማራ የሚጠነክረው ጦቢያዊነት ሲጠነክር ነው፡፡
• ኦሮሞ ብዙሃን (majority) ነው የሚባለው ትርክት የኦነጋውያን ቅጥፈት እንደሆነና፣ ያማራ ሕዝብ የኦሮሞን ብቻ ሳይሆን የኦሮሞንና የትግሬን ሕዝብ ድምር እንደሚበልጥ አንዳርጋቸው አሳምሮ ያውቃል፡፡ ስለዚህም ኢዜማ ስልጣን ለመያዝ የሚያስፈልገው ያብዛኛውን አማራ ድምጽ ማግኘት ብቻ ነው፡፡
• አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እስከተቀናቀነው ድረስ ግን ኢዜማ ያማራን ድምጽ አብዛኛውን ቀርቶ ጥቂትም እንደማያገኝ ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህም ኢዜማ በምርጫ ያሸንፍ ዘንድ የአብን አማራዊ መሠረት የግድ መፈራረስ አለበት፡፡ አማራ የሚባል ሕዝብ ከሌለ ደግሞ አብን ሊኖር አይችልም፣ መኖርም የለበትም፡፡
• ስለዚህም ‹‹አማራ የሚባል ሕዝብ የለም›› የተሰኘው ያንዳርጋቸው ትርክት ሌላ ምንም ሳይሆን ከስልጣን ጥማት የመነጨ ፖለቲካዊ ሸፍጥ ነው፡፡ ለፖለቲካዊ ሸፍጥ ደግሞ ከኢሕአፔ ወዲያ ላሳር ነው፡፡ ኢህአባ አባ ደባ፡፡
• የኦነጉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኦቦ ዐብይ አህመድ የሚጓዝበትን ፍኖትካርታ (roadmap) ያዘጋጀው አንዳርጋቸው መሆኑን ራሱ አንዳርጋቸው በኩራት ስሜት ነግሮናል፡፡ ስለዚህም ዐብይ አህመድ በባልደራስና በአብን ባጠቃላይ ደግሞ ባማራ ሕዝብና አመራሮች ላይ ጦርነት ያወጀው በአንዳርጋቸው መመርያ መሠረት ነው ማለት ነው፡፡ በተለይም ደግሞ የሰኔ 15ቱ የባሕር ዳር ጭፍጨፋ አንዳርጋቸውን በቀጥታ ይመለከተዋል ማለት ነው፡፡ ከሰኔ 15 በኋላ ደግሞ የግንቦት ሰባቱ ውሻ አበረ አዳሙ አማራወችን የሚያሳድደው አለቃው አንዳርጋቸው ጃስ እያለው ነው ማለት ነው፡፡
• ኢዜማ (ማለትም ግንቦት ሰባት) አብንን ለማክሰም የሚሯሯጠው ብቸኛ የስልጣን መንገዱን ስለሚዘጋበት ነው፡፡
• የኦነጉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኦቦ ዐብይ አህመድ አብንን ለማጥፋት የሚጥረው በጦቢያ ፍርስራሽ ላይ የኦሮምያን አጸጌ (oromo empire) እንዳይገነባ የሚያሰናክለው የቀረው አንድ እንቅፋት አብን ብቻ በመሆኑ ነው፡፡
• ብአዴን አብንን የሚያዋከበው ደግሞ በውስጡ በተሰገሰጉ ግንቦት ሰባቶች፣ ኦነጎች፣ ወየንቲወችና ሆዳደሮች ነው፡፡
• ጎጠኞቹ ወያኔና ኦነግ፣ ስልጣን ጥመኛው ኢዜማ እንዲሁም የነሱ ሎሌ ብአዴን ባንድነት ተቀናብረው በጦቢያዊነት ላይ በተለያዩ አቅጣጫወች ጦሮቻቸውን መወርወራቸውን በቁርጠኝነት ተያይዘውታል፡፡ በፀረጦቢያ ኃይሎች የሚወረወሩበትን ጦሮች ጦቢያዊነት መቋቋም የሚችለው ደግሞ የጀርባ አጥንቱ የሆነው አማራነት ሲጠናከር ብቻ ነው፡፡ የግንቦት ሰባቱን ፊታውራሪ አቶ አንዳርጋቸውን እንደ ጦር የሚያስፈራው ደግሞ የአማራ በአማራነት መጠናከር ነው፡፡

Email: mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic