>
12:41 pm - Thursday December 8, 2022

ተመራጮች ከሌሉ፣"ምርጫ!" የክህደት ወጥመድ ነው የሚሆነው። (ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ፤)

ተመራጮች ከሌሉ፣”ምርጫ!” የክህደት ወጥመድ ነው የሚሆነው።
ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ፤

ከታሪክ ትምህርት እንደተገነዘብነው “ምርጫ” በዕውነት ጥበቃ ክንድ ውስጥ ለመሆኑ ዋና ዋስትናው የሕግ የበላይነት መኖሩን ማረጋገጥ ነው።ይህንን ለማረጋገጥ ደግሞ ትክክለኛ በሕዝብ የፀደቀ ሕዝብ ግ( ሕገሕዝ)ወሳኝ ነው።ፓርላማው ከሕገ ሕዝቡ ሕገ መንግሥትንና ህግጋትን ለመቅረፅ፣ፖሊሲዎችን ለመንደፍና ዝርዝር ደንቦችን ያለ-ሕገ ሕዝብ የአንቀፅ ተቃርኖ ለማውጣት አያስቸግረውም ሕገ-ሕዝብ ሳይኖር ምርጫን ማሰብየህግ የበላይነት ሳይኖር ያለዋስትና ያለሕግ ከለላየሕዝብን ሥልጣን ለመንግሥት ወይም ግለሰቦች እንደመስጠት ነው፤ያለደረሰኝ ዕቃ እንደመሸጥ፤ኣሊያም ያለውል ወይም  ያለስምምነት እና  ያለፊርማ የሥራ ኮንትራትን በወጥመድ ውስጥ እንደመጀመር ነው፤ሕዝባዊ ሐቁ።ምርጫ፣(ያለ ስሌት…ወይስ…) የሚመረጠውን ነገር ለይቶ መምረጥ ማለት  ቢሆም ምርጫውም ሆነ ተመራጮች ከሌሉ ግን፣“ምርጫ”  የክህደት ወጥመድ ይሆናል። 

          እነሆ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሕግን የበላይነት ለማስፈን ለዘመናት እየታገለ በነፍስ ወከፍ የተወራረሰውን ነብስ፣ ሽልንግ በማትሞላ የተባረከችም ሆነ ያልተባረከች፤ ዕድሜው የሚተካለትን ትውልድ ለመዝራት፣በሰላምና በደስታ እየኖረ ሕይወቱን ሊጠቀምባትና ሊኖርባት ይታገላል።ይህ የህልውና ትግል ከግለሰብ አልፎ፤ቤተሰብን ተሻግሮ እና ሕብረተሰብ ውስጥ አድጎ አገርን እያስጠራ ይኖራል፤ጥሪውም  የሰብዓዊነታችንን ማንነት ወደ ዓለም አቀፋዊ የዕውቅና ደረጃ በከፍታ ያደርሰዋል።
      ከዚህ የታሪክ ሐቅ አንፃር ነው የኢትዮጵያ ሕዝቦች በሰብዓዊነታቸው ያሳለፉት የኑሮ ደረጃ ከፍታ በደስታ እና በመከራ የነበር። ተብሎ ለማጠቃለል ካልሆነ በቀር፣መከራን መርጠው ለመኖር የፈለጉ እንዳልነበሩ ሁሉ፣ሐቁን ለማረጋገጥ የታሪክ መረጃዎችን ማሰባሰብ አያስፈልገንም፤እናም ሰው መሆናቸው ብቻ ለኢትዮጵያዊነታቸው ይበቃቸዋል።
     እናማ ማነውሳ ከደስታ እና ከመከራ:-የቱ ነው መከራን የሚመርጥ?ጤናማ ያልሆነ ሰው ብቻ ነው መምረጥ  ስለሚሳነው። ያለበለዚያ ጤነኛ የሆነ ሰው ሁሉ ተሳስቶ ከደስታ ይልቅ መከራን እንዲመርጥ፤የ”መከራን ቅርፅ” በተለያዩ ገፅታዎች አሽሞንሙኖ በመሸፋፈን ወይም አባብሎ በማጉረስ፣አሊያም በጉልበት በማጋት የግድ እንዲመርጡ ይደረግ ይሆን እንጂ ፍላጎቱ አይ-ገታም። ለምን ቢባል የሰው ልጅ ሀሳቡ አይቆምምና”ሰው”ን ሰው ያደረገው አዕምሮው ስለሆነ፣ ፍላጎቱ ያድጋል፤ይህ በቋንቋ የሚነገረው አስተሳሰቡ ደግሞ ሁሌም የሚቀርቡለትን ሁሉ አማርጦ ያደርጋል፤እናም ምርጫን አይተወውም፤የዕለት ተዕለት ፍላጎቱም ያለምርጫ አይኖርም።
     “አንድን ነገር ለመምረጥ ደግሞ”ሀ” መንገዶች ቢኖሩ እና ሌላ ክዚህ ጋር የማይገናኝ ነገር ለመምረጥ “ለ” መንገዶች ቢኖሩ፣ሁለቱን አንድ ላይ መምረጥ ባይቻል፣ ከሁለቱ አንዱን ለመምረጥ[ሀ + ለ]መንገዶች አሉ ማለት ነው፤”ይህን የመደመር ቀመር የማያውቅ መ+ደ+መ+ር ገብቶኛል ብሎ”እኔ አሻግራችኋለው i”ስለተባለ በለበጣ ከተናገረው ጋር እንደቀልድ ጉዞ መጀመሩ ያጠያይቃል፤እናም ክፉነት ባይሆንም ላንዳፍታ ቆምብሎ ማሰቡ በጎ ማስተዋል ነው የሚያሰኘው።
      ለበጎ ማስተዋል ሠለጠኑ የምንላቸውን ሀገሮች ከማንሳታችን በፊት ግለሰቦችን በጥንቃቄ ብንመረምራቸው በአብዛኛው አንዱ ከሌላው ስህተት የተማረው፣አሊያም የገለበጠው ዕውቀት መሆኑን እንገነዘባለን፤እንጂ በተፈጥሮ የሚገኝ ፀጋ ወይ በልጅነት ይታያል አሊያም በስተእርጅና ይጀምራል፤ከእነዚህ የተፈጥሮ ሕግጋት ውጭ አይሆኑም፣ቤትሆቭን እና ሞዛርትን ይመለከቷል፤አንዱ ተምሮ፣ሌላው በተፈጥሮ የነበራቸው የሙዚቃ ዕውቀት ነው።
 ወደ ተነሳንበት ርዕሰ-ጉዳይ ስንመጣ የአገርን ጉድይ አስመልክቶ ኢትዮጵያ”ሕዝባዊ መንግሥት”ለማቋቋም በመዘጋጀት ላይ ትገኛለች፤ በቀላል አቀራረብ ኖሮ የማያውቀውን የሕዝብ መንግሥት ለመመሥረት ደፋቀና ትላለች።ለዚህ መልካም ተግባር ሰዎች በአንድ ልብ ሆነው ሲነሱ ርኩሳን መናፍስት ደግሞ ዝም ብለው አይመለከቱም፤በሰዎች ልብ ሰርፀው ክፉውን እንዲደረግ ያደርጋሉ።ዜጎች ግን ይሰበሰቡና እነዚያ እና እነዚህን.. ሰዎች በሰውነታቸውና በኢትዮጵያዊነታቸው ካላቸው ዕውቀትና የዕድሜ ተመክሮ አንፃር በመንግሥትነት ያገለግሉኛል ብሎ በኮንትራት ቀጥሮ ለተወሰኑ ዓመታት ያሰራቸው ዘንድ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ይመርጣቸዋል፤ይህ ነው ቀላሉ ዕውነታ፣ዳሩ ግን እየተደራረቡ በሚሄዱት ሌሎች ተቀጥላዎች በላይ በላዩ ላይ ሲደማመሩ ነው የሚወሳሰበው።[ሀ + ለ ]ሀ + መ+ ለ…ተራ ጨዋታ…የሚሆነው…
     በቀላል የአገላለፅ ምሳሌ ሳስቀምጠው፤ጫማ ሊገዛ የፈለገ ግለሰብ የጫማው ዋጋ ሃያ አምስት ብር ብቻ መሆኑን አውቆ በእጁ ገብቶ እስከተጫመው ድረስ የአርባ አምስት ብር ድምር ዋጋ ካወጣ፤ዋጋው ስንት ነው ብሎ መናገር ይቻላል?እናም ድብቅ የለም።እኛ ሰዎችን ስንመርጥ በጣም በጥንቃቄ መምረጥ አለብን፤ቀስ በቀስ የሚጨመር ዋጋ እንደማያስከፍሉን ቢያንስ እርግ ጠኞች መሆን ስለሚኖርብን ነው፤ለዚህም ከሁሉም ችግር መፍቻዎች ይበልጥ ለመፍትሄነት የሚረዳን የበሰለ-ግልፅነት ብቻ ነው።
        የተንኮለኞች የመጀመሪያ ማፈሪያ  ርምጃቸው ግልፅነት ብቻ ነው፤የሚነገረውና የሚባለው የፈለገውንም ያህል መስዋዕትነት  ቢያስከፍሉንም፣ግልፅ ከመሆናቸውም በፊት ሆነ በኋላ እንዲታወቁ ከተደረገ ስለዕውነተኛነታቸው ምስክርነትም አያስፈልጋቸውም።ዛሪ ስንት ጉዳዮችን ማወቅ ሲገባን የዜግነት መብታችን መሆኑ እየታወቀ ተከልክለናል፤ሕዝብ በግልፅ ጨረታ በኅላፊነት ለመቀጠር”እኛ ሕዝብን ሌት ተቀን በመንግሥትነት እናገለግላለን” ብለው ችሎታቸውን፣ ዕውቀታቸውን፣የአስተዳደር ልምዳቸውን፣ታማኝነታቸውን እና ዓላማቸውን አቅርበው  እና የሕዝብ ታዛዥ ለመሆን አሁን  የሚያመለክቱትንም  ሲቆጣር   “ምርጫውን!”በስሌት ቅርፅ ይሰጡትና  ለማጭበርበር ሥልጣኑን ይቆጣጠሩታል።ለነገሩ “ምርጫ”ትርጉሙ የሚመረጠውን ነገር ለይቶ መምረጥ ማለት ነው፤ካለበለዚያ ምርጫውም ሆነ ተመራጮች ከሌሉ ግን፣ምርጫ የክህደት ወጥመድ ይሆናል።
Filed in: Amharic