>

" መንግስት በጸረ ሽብር አዋጁ ወደ ድሮው የአፈና ስልት ተመልሷል !!!"  (ሲ.ፒ.ጄ)

” መንግስት በጸረ ሽብር አዋጁ ወደ ድሮው የአፈና ስልት ተመልሷል !!!” 
ሲ.ፒ.ጄ
*  “መንግስት የጸረ ሽብር አዋጁን ጋዜጠኞችን ማጥቂያ ከማድረግ አቁሞ የመናገር እና የመጻፍ ነጻነትን በሚያረጋግጥ መልኩ ሪፎርም ማድረጉ ላይ ይስራ!” የሲፒጄ የአፍሪካ ተወካይ ሙቶኪ ሙሞ
በቅዱስ ማህሉ
በአራዳ ፍርድ ቤት ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉን ኢንተርቪው በማድረግ ላይ የነበረው የኢትዮጲስ ጋዜጣ ባልደረባ ጋዜጠኛ ምስጋናው ጌታቸው በጸረ ሽብር አዋጁ ሊከሰስ ይችላል ያለው ሲፒጄ የኢትዮጵያን መንግስት ክሱን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ውድቅ እንዲያደርግ ጠይቋል።
 የጋዜጠኛ ምስጋናው ጌታቸው ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ መንግስት ይወንጅለው እንጅ እስካሁን የቀረበበት ክስ እና መንግስትም ያቀረበው ማስረጃ የለም ብሏል።
ከጌታቸው ጋር የአዲስ አበባ ባልደራስ ምክር ቤት አባል የሆነው  አዳም ወጅራ እንደተያዘ የተናገረው እስክንድ ነጋ አዳም በተያዘበት ወቅት ቀረጻ ላይ እንደነበር ለሲፒጄ ተናግሯል።
የፌደራል አቃቤ ህግ ቃል አቀባይ አቶ ዝናቡ ቱኑ ለሲፒጄ ምስጋናው ጌታቸው እና አዳም ወጅራ ከጀነራል ሰዓረ ግድያ እና ከአማራ ክልል መንግስት ግልበጣ ሙከራ ጋር በተያያዘ መታሰራቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ ያሉ ሲሆን ተመሳሳይ መረጃ የተጠየቁት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ቃል አቀባይ አቶ ጄይላን አብዲ ደግሞ አቶ ምስጋናው ከፍቃድ ውጭ ካሜራ የተገጠመለት መነጸር አድርጎ ፍርድቤት በመገኘቱ እንደታሰረ ገልጸዋል።
ሁለቱም ባለስልጣናት ጋዜጠኛውን ፍጹም በሁለት የየራሳቸው ወንጀል እንዳሰሩት ከሰጡት የተለያየ አስተያየት መረዳት ከመቻሉም በላይ ባለስልጣናቱ ጋዜጠኛውን እስር ቤት ከመቆለፍ ውጭ ምርመራ እንዳላደረጉበትም ሆነ በጉዳዩ ላይ መረጃ እንደማይለዋወጡ ያሳያል።
 ከአማራ ክልል መፈንቅለ መንግስት ከተባለው ክስ ጋር በተያያዘ ከሁለት መቶ ሰዎች በላይ መታሰራቸውን ያወሳው ሲፒጄ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩም አንዱ መሆኑን ጠቅሷል። ሲፒጄ መንግስት በጸረ ሽብር አዋጁ ወደ ድሮው የአፈና ስልት ተመልሷል ብሏል። የሲፒጄ የአፍሪካ ተወካይ ሙቶኪ ሙሞ መንግስት የጸረ ሽብር አዋጁን ጋዜጠኞችን ማጥቂያ ከማድረግ አቁሞ የመናገር እና የመጻፍ ነጻነትን በሚያረጋግጥ መልኩ ሪፎርም ማድረጉ ላይ ይስራ በማለት ጋዜጠኛ ምስጋናው ጌታቸውን ያለቅድሚያ ሁኔታ ከእስር እንዲለቅ አሳስቧል።
Filed in: Amharic