>

‹የሞት ፍርደኛው ማስታወሻ!!!›› የካምቦሎጆ ዝምታ!!! (ፀ/ትፂዮን ዘማርያም)

‹የሞት ፍርደኛው ማስታወሻ!!!›› የካምቦሎጆ ዝምታ!!!

ፀ/ትፂዮን ዘማርያም
‹‹ትውልድ አይደናገር እኛም እንናገር›› ቅፅ 1
(አዲስ አበባ፣ አንድ ቤተሰብ፣ አብዮቱ እና ኢህአፓ (1877- 1970)
አንዳርጋቸው ፅጌ)

የአንዳርጋቸው ትወና እንደ “Groundhog Day” የፀደይ ወቅት መምጣትን የሚያበስር አይጥ መታየት ያሳያል የሚል የቆየ ባህል በካናዳና፣ አሜሪካ ህዝቦች ጥንታዊ ባህል ነው፡፡ በ1993 እኤአ የተሠራ የኮሜዲ ፊልም ሲሆን በሃሮልድ ራሚስ ዳሬክተርነት እንዲሁም በራሚስና ዳኒ ሩቢን የተፃፈ ሲሆን ዋናው ተዋናይ ቢሊ ሙሪ እንደ ፊሊ ኮኖር የከባቢ አየር የቴሌቪዝን ዜና ዘጋቢ በመሆን አመታዊውን የግራውን ሆግ ዴይ በዓልን ሲዘግብ ያቀን ተቸክሎ ቀረበት፣ ሁሌ ያው ቀን ብቻ ይደጋገምበት ጀመር፡፡ አንድ ሰው የተለያየ ህይወት በአንድ ቀን ውስጥ አንዴ ንጉስና አንዴ ለማኝ፣ አንዴ አስተማሪና አንዴ ወታደር፣ አንዴ የፖሊት ቢሮ አባል አንዴ ሹፌር ሆኖ ማሳለፍ እንደሚችል በቡዲህዝም እምነት ተከታዬች ብዙ ህይወት መኖር ማለትም ‹‹ ፈጣሪ፣ የሰው ልጅ ህይወት ይፍታህ ፍርድ ተፈርዶበት በዚች ዓለም እንደሚኖር››ያምናሉ፡፡ በኢህአፓ ጎዶችም፣  ያ የአብዬት ቀን በየቀኑ ሲደጋገምበት ቀኑ ተቸክሎ የቀረበት ሁኔታ የሚገልፅ ፊልም ጋር ተመሳሳይ ይመስላል፡፡ በብዙ ጎዶች እይታ አምናና ዘንድሮን፣ ገነትንና ገሃነምን፣ ሞትና ህይወትን፣ እርጅናና ውልደትን በቀጭን ክር ሠፋተዋቸው በራሳቸውን ዛቢያ በአንድ ቀን በምናባቸው ዓመታትን በመዞር የፈጠሩት ዓለም ከልጅነት እስከ ሽምግልና ጊዜ እንደ ፎቶ አልበም፣ እንደ ልደት በዓል የተቀረፀ ቪዲዮ የሚያስተውሉት ይመስለኛል፡፡ ሻለቃ መንግስቱ ኃይለማርያም በዚንባዌ በስደት ብዙ ጊዜቸውን የሚያጠፋበት ሳስብ፣ ይዘውት የሄዱት የቪዲዬ ፊልም፣ የ17 ዓመታት በአብዬት አደባባይ ሠልፈኛው ከፉታቸው ሲተም፣ መጽሃፍ ገላጮች ገልጸው የእሳቸውን ፎቶግራፍ ሲያሳዬቸው፣ በእዝነ ህሊናቸው ተቀርጾ ቀን በእውኑ ዓለም ያዩት ለሊት በእንቅልፍ ልባቸው በህብረ ቀለማት አጊጦ ዳግም ያስተውሉታል፣ የእውኑና የህልም ዓለማት ተደበላልቆባቸው፡፡ የግልና የሃገር ታሪክ ድርና ማግ፣ነጠላና ጋቢ ወራጅና ማገር፣ አግድምና ቆሚ፣በህሊናችን የተዘበራረቀ የህመም ጊዜ፣ ቀንና ዓመት ልኪታቸው አንድ ይሆናል፡፡

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌና አቶ በረከት ስምዖን በ1991እኤአ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራንን ሰብስበው ስለ ‹‹ኢትዮጵያ የመቶ አመት ታሪክ›› ምሁራኑን ለማስተማር ተቅበዘበዙ፡፡ በትረካቸው ዲስኩር መኃል፣ ፕሮፌስር ባህሩ ዘውዴ ከመቀመጫው ተነስቶ ከስብሰባው አዳራሽ እንደወጣ፣ ጠቅላላ መምህራኖች ተከታትለው ወጡ፡፡ አንድአርጋቸውና በረከት ቢረሱትም በስብሰባው የነበሩ ምሁራን አይረሱትም፡፡ ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያ ታሪክ ፀሃፊዎችን እያወገዘ በእራሱ ሲመጻደቅ አንድ የሚለው ጠፍቶል፡፡ አንዳርጋቸው ፅጌ የኢትዮጵያን ታሪክ ከ1877 እስከ 1970 ዓ/ም ያለውን የ93 ዓመታት የታሪክ ዘመን የአንድ ቤተሰብ፣ አብዮቱና ኢህአፓ (Autobiography) ግለ ታሪክና (Biography) በሌላ ሰው የተፃፈ የህይወት ታሪክ በማጣቀስ ብሎም የኢትዮጵያ ታሪክ (Ethiopian History) አፃፃፍ፣ ዓለም አቀፋዊ የታሪክ አፃፃፍን ሳይንሳዊ ስልትና ትምህርት በማጣጣል ያደረገው እራስንና አንድ ቤተሰብን ታሪክ የማግዘፍ የሸፍጥ ትረካ እብደትና ንቀት እንደሆነ አስመስክሮል፡፡ የታሪክ ምሁራን ስለ መፅሃፉ ለህዝብ መልስ መስጠት ግን ይጠበቅባችኃል፡፡

መለስ ዜናዊና የትምህርት ሚኒስትሮ ገነት ዘውዴ (ጉዲት) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲት 40 መምህራንን የማባረራቸው ግፍ ዘሬ ተዘንግቶ፣ ሃገር የማፍረስ ተልእኮቸውን ግን ያለ አንዳች ፀፀት ቀጥለውበታል፡፡ የአንዳርጋቸው የ93 ዓመታት እንቶ ፈንቶ የቤተሰብ የግል ታሪክ እንጂ የኢትዮጵያ ታሪክ ሊሆን አይቻለውም፡፡ የአንዳርጋቸው መፅሓፍ የእምዬ ኢትዮጵያን ታሪክ በትንሹ እንኮን እንደወረደ በአንድ ገፅ ለማስቀመጥ ዳገት ሆኖበታል፡ በታሪክ የግለሰቦች ሚናን ለማጣጣልና በግራ ፖለቲካ ‹ታሪክ ሰሪው ሠፊው ህዝብ ነው›ተረካን አብሮ ማስኬድ ይቻለው ነበር እንላለን፡ የሃገሪቱ ወርካዎቹ አፄ ቴዋድሮስ፣ አፄ ዮሃንስ፣ ዳግማዊ ሚኒሊክ፣ እቴጌ ዘውዲቱ፣ ልጅ ኢያሱ፣ ቀ.ኃ.ሥ.፣መንግሥቱ ኃይለማርያም፣ መለስ ዜናዊ፣ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ዶክተር አብይ አህመድ ወዘተ እንደ ቅመም እንኮ ሳይጠቀሱ የቤተስብህን ገድለ ታሪክ እንደ አገር ታሪክ መፃፍህ ከዮኒቨርሲቲ በር ላይ የታሪክ 101 (History 101) እንኮ ያለፍክ አይመስለንም፡፡ ወደድክም ጠላህ ታሪካችን እንደወረደ እንዲህ ነው፡-

• ‹‹በ1855 እኤአ መይሳው ካሳ አፄ ቴዋድሮስ ሁለተኛው ነገሱ፡፡ በ1868 እኤአ በእንግሊዙ ጀነራል ናፔር ጦር አገራችን ተወረረች አፄ ቴዎድሮስ ራሳቸውን ገደሉ፡፡ አፄ ቴዋድሮስ የባርያ ንግድን ለማጥፋት ማከሩ፣ ሆኖም ቀይባህርን ተቆጣጠሩት እንግሊዞች የባርያ ንግድን በይፋ ያስኬዱ ነበርና!
• በ1872 እኤአ የትግራዮ አፄ ዮሃንስ አራተኛው ነገሱ፡፡ በ1889 እኤአ ዮሃንስ አራተኛው በማሃዲስቶች ጋር በተደረገ ጦርነት ተገደሉ፡፡ አፄ ዩሃንስ የባርያ ንግድን በአዋጅ በህግ ሠርዘው ነበር፣ሆኖም አገራችን በአውሮፓና አርብ የባርያ ፈንጋዬች ተከበ ስለነበረና ሀገር ውስጥ ዘውጌ ብሄርተኞች የባርያ ንግድን መደገፍ ምክንያት አዋጁን ማስከበር ተሳናቸው፡፡ብሎም አፄ ዳግማዊ ሚኒሊክ ነገሱ፡፡
• 1889 እኤአ ዳግማዊ ሚኒሊክ ከጣሊያን ጋር የውጫሌን ውል ተፈራረሙ፡፡ ጣሊያን በጫሌ ውል የኢትዮጵያ ሞግዚት ነኝ አለ፣ ውሉን ኢትዮጵያ ሰረዘችው፡፡
• 1889 እኤአ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና መዲና ሆና በእቴጌ ጣይቱ ተቆረቆረች፡፡
• በ1890 እኤአ የባርያ ንግድን እንቅስቃሴ ገታ፣ የባሪያ ገበያዎችን ከተሞች አወደመ፣ የባርያ ፈንጋዬችን ቀጣ፡፡ እንደ ክሪስ ፕሩቲ ሚኒሊክ የባርያ ንግድን ለማጥፋት ቢጥርም የህዝቡን ህሊና መለውጥ ባለመቻሉና የአውሮፓና የአረብ የባርያ ፈንጋች ዓለም አቀፍ ንግድ የተነሳ ተግባራዊ ሊሆን አልቻለም፡፡
• 1895 እኤአ ጣልያን ኢትዮጵያን ወረረች፡፡
• 1896 እኤአ ኢትዮጵያ የጣልያን ወራሪዎችን በአድዋ ጦርነት አሸነፈች፡፡ ዳግማዊ ሚኒሊክ በድል አድራጊነት የውጫሌ ውልን ሰረዙ፣ ጣልያን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ተቀበለች፡፡
• 1913 እኤአ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሞቱ‹‹ ልጅ እያሱ ተተኩ፡፡ በ1916 እኤአ ልጅ ኢያሱ ተሸሩ፡፡ የሚኒሊክ ሴት ልጅ እቴጌ ዘውዲቱ ነገሱ፡፡ ራስ ተፈሪ መኮንን አልጋ ወራሽ ተባሉ፡፡
• በ1919 እኤአ ቀ.ኃ.ሥ. የሊግ ኦፍ ኔሽን አባል ለመሆን አመለከቱ፡፡ ጣሊያንና ታላቆ እንግሊዝ ሃሳቡን በመቃወም ኢትዮጵያ ነጻ ሃገር ብትሆንም ቅሉ፣ የሰለጠነች ሃገር አይደለችም፣ ብሎም የባርያ ንግድ አላጠፋችም ስለዚህ ከዚህ ዓለም አቀፍ ድርጅት ዘንድ አባል መሆን አይቻላትም በማለት ተቃወሙ፡፡ በ1923 እኤአ የባርያ ንግድ ለማጥፋት የሴንት ጀርሚን ስምምነት ተደረገ፡፡ በ1924 እኤአ የሊግ ኦፍ ኔሽን ጊዜያዊ የባርያ ኮሚሽን በመሾም ባርነትን ከዓለም ለማጥፋት ወሰነ፡፡ በ1926 ኢትዮጵያ የባርያ ንግድን ለማጥፋት ስምምነት ፈረመች፣ በአዋጅ በአንድ ጊዜ ባርነትን ማጥፋት ግን አስቸጋሪ ነበር፡፡
• በ1930 እኤአ ዘውዲቱ ሞቱ፡፡ ራስ ተፈሪ መኮንን ቀ.ኃ.ሥ ተብለው ነገሱ፡፡
• በ1935 እኤአ ጣልያን ዳግም ኢትዮጵያን ወረረች፡፡ በ1936 እኤአ ጣልያን አዲስ አበባን ተቆጣጠረች፡፡ ጣልያን ምስራቅ አፍሪካ በማለት ኢትዮጵያን ኤርትራንና የጣልያን ሶማሌ ላንድን ቀላቅላ ተቆጣጠረች፡፡ ጣሊያን ኢትዮጵያን የወረረችበት ምክንያት በኢትጵያ ውስጥ ያለውን የባርያ ንግድ ለማጥፋት ነው በሚል በ1935 አና 1936 እኤአ የባሪያ ንግድን ለማጥፋት አዋጅ አወጀች፡፡ 420000 ሽህ ሰዎችን ከባርነት አላቀቅሁ በማለት የዓለምን ቀልብ ለወረራዋ ምክንያት ፈጠረች፡፡ ቀ.ኃ.ሥ ተሰደዱ በሊግ ኦፍ ኔሽን ታሪካዊ ንግግር አደረጉ፡፡ የኢትዮጵያ አርበኞች በድር በገደሉ ሽምቅ ውጊያ ገጠሙ፡፡ የመጀመሪያው ሽምቅ ውጊያ (Gurreala warfer) በዓለም ታሪክ ተመዘገበ፡፡ በ1941 እኤአ የኢትዮጵያ አርበኞች ለአምስት ዓመታት በድር በገደሉ ሽምቅ ውጊያ በመግጠም ጣልያንን አሸነፉ፡፡ ቀ.ኃ.ሥ. በእንግሊዝና የኮመን ዌልዝ ሠራዊት ታጅበው በኢትዮጵያ አርበኞች መሪነት ወደ ዙፋናቸው ዳግም ተመለሱ፡፡ ቀኃሥ የባርያ ንግድን አጠፉ፡፡ አንደርጋቸው ኢትዮጵያ ጣልያንን ያሸነፈችው በእንግሊዝና የአላይድ ኃይል እንደሆነ አስረግጦ ፅፎል፣ ለእሱ የአምስቱ ዓመት ተጋድሎና የሽምቅ ውጊያ ቁብም ባይሰጠው በብዙ ታሪክ ፀሃፊዎች ዘንድ በአርበኞቹ ተጋድሎ ጣሊያን ተሸንፎ እንደወጣ ተፅፎል፡፡ መፅሃፉ ‹‹አትፍረድ ይፈረድብሃል›› ተብሎልና!!! ኤርትራ አደሩ፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት ሕወሓት/ኢህአዴግን ድል አድርገን ከአስር አመታት የአርበኝነት ትግል በኃላ አሽንፈን ገባን ሲሉን በቆረጣ ነው ፣ በደፈጣ፣ አልያስ በጨበጣ፣ ብለን ብንጠይቅ ተገቢ አይሆንምን!!! ግንቦት 7፣ ኦነግ፣ ኦብነግ ወዘተርፈ በሪሞት ኮንትሮል ከኤርትራ በርሃ ሆነው በመዋጋት ‹‹ነፃነትን የማያውቅ ነፃ አውጭ›› ነታቸውን አበሰሩ ይሄነው ታሪኬ ባጭሩ ሰኞ ተረገዝሁ….ማክሰኞ …..እሮብ……ሐሙስ…. ተረት ተረት!!!
• 1952 እኤአ የተባበሩት መንግስታት ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን ቀላቀሎት፡፡ በ1960 እኤአ ሃያ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ነፃ ወጡ፡፡ በ1962 እኤአ ቀ.ኃ.ሥ. ኤርትራን ወደ እናት ሃገሮ አዋሃዶት፡፡
• 1963 እኤአ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በአዲስ አበባ ተቆቆመ፡፡
• 1974 እኤአ ቀ.ኃ.ሥ. ከስልጣን ወረዱ፣ወታደራዊ ደርግ ስልጣን ያዘ፡፡ 1975 እኤአ ቀኃሥ ተገደሉ፡፡
• በ1977 እኤአ ሱማሊያ ኢትዮጵያን ወረረች፡፡ በ1978 ኢትዮጵያ ጦር ሱማሊያ አሸነፈች፡፡
• ከ1977 እስከ 1979 እኤአ በመንግስቱ ኃይለማርያም ወታደራዊ አገዛዝ ዘመን ‹‹በቀይ ሽብር›› አንድ ትውልድ አለቀ፡፡ በ1984 እስከ 1985 እኤአ በኢትዮጵያ ድርቅና ርሃብ ብዙ ሰዎች አለቁ፡፡
• በ1991 ሻብያና ወያኔ/ኢህአዴግ አዲስ አበባን ተቆጣጠረ፡፡ መንግስቱ ኃ/ማርያም ዝንባዌ ተሰደደ፡፡ ህወሓት/ ኢህአዴግ በ1993 እኤአ ኤርትራ ከኢትዮጵያ አስገነጠለ፡፡
• በ1994 በኢትዮጵያ አዲስ የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ፌዴራላዊ የዘውጌ መንግስት ተመሠረተ፡፡››1
አንዳርጋቸው በገፅ 154 ‹‹በኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው የባሪያ ፍንገላ ታሪክ ይህ ገበሬ የሚለውንም ከዕምነት ጋር የተያያዘ ገጽታም ነበረው፡፡ ዕምነት አለን ይሉ የነበሩት ክርስቲያኖች እና እስላሞች በአብዛኛው በባርነት የሚፈነግሉትና የሚሸጡት የኛ አይነት ዕምነት የለውም ብለው የፈረጁትን የራሱ ተውፊታዊ ዕምነት የነበረውን የደቡብና የደቡብ ምእራብ ህዝብ ነበር፡፡ እምነታችንም ይፈቅድልናል የሚል ክርክር ያቀርቡ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ክርስቲያኖች ሙስሊሞቹን ሙስሊሞቹ ክርስቲያኖቹን እየወረሩና እያፈኑ በባርነት ይሸጡ እንደነበር (The social history of Ethiopia) በሚለው መጽሃፍ ሪቻርድ ፓንክረስት ከነ ማስረጃው በአሃዝ አስደግፈው ጽፎታል፡፡ ‹‹ግንባራቸው ላይ መስቀል ያለባቸው ህፃናት ተሸጠው በመርከብ ሲጎዙ ይታዩ ነበር›› ይላል፡፡ እንዲህ አይነት ነገር ነበር ብንልም የባርነት ጠባሳና ቁስል ግን በሁሉም ማህበረሰብ ውስጥ በእኩልነት የሚታይና የሚሰማ እንዳልሆነ ማወቅ ይኖርብናል፡፡ አንዳንድ ማህበረሰቦች ዘራቸው እስከመጥፋት ደረጃ እስከሚደርስ የባርነት ሰለባ ሆነዋል፡፡ ‹‹ሁሉም ባሪያ ሆኖል፤ ሁሉም ባሪያ አድርጎል፤ ምን የሚያስጮህ ነገር አለ?›› በሚል ክርክር በእያንዳንዱ ህዝብ ላይ በተለየ የደረሰበትን የከፋ ስቃይ አሳንሰንና አድበስብሰን ማለፍ አንችልም፡፡) ይለናል፡፡ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ የነበረውን የባርያ ንግድ ‹አንዳንድ ማህበረሰቦች ዘራቸው እስከመጥፋት ደረጃ እስከሚደርስ የባርነት ሰለባ ሆነዋል፡፡›ብሎ ማስረጃ ግን አያቀርብም፣ የነጭ ውሸት በመሆኑ!!! በሃገራችን የነበረውን የባርያ ንግድ እኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳላድበሰብስ ፃፍኩት ይላል፡፡ በ1990ዓ/ም በሪፖርተር መፅሄት ገጣሚ ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው በኢትዮጰያ ስለ ባሪያዎች የእለት ተዕለት ኑሮ ፅፈዋል፡፡ በ1992 ዓ/ም ኢትኦጵ መፅሔት ‹‹በባርነት የተሸጡ አፍሪካውያን እና እየገዘፈ የመጣው የካሳ (መቆቆሚያ) ጥያቄ›› በፍቅር ነጋ ወዘተርፈ ብዙ ፀሃፊዎች ዘመኑን እያጣቀሱ ለህዝብ አሳውቀዋል፡፡ አንዳርጋቸው በመጽሃፉ የሚኒልክ እናት እጅጋየሁ ለማ አዲያሞ ባርያ እንደነበሩ፣ ልጃቻው ንጉሥ ሚኒሊክ የኢትዮጵያ ንጉስ እንደሆኑ፣ ኃብተጊዬርጊስ ዲነግዴ ባርያ ሆነው የጦር ሚኒስትርና የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር እንደነበሩ፣ ባልቻ አባነፍሶ ባርያ ሆነው ባለ ከፍተኛ የጦር ማዕረግ ሰው እንደነበሩ ይተርካል፡፡ መንግስቱ ኃይለማርያም የባርያ ልጅ ሆኖ ለ17 ዓመታት የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት እንደነበረ ተርኮል፡፡ መለስ ዜናዊ የባንዳ ልጅ ሆኖ ለ20 ዓመታት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር የሆነባት ሃገር እንደሆነ ተፅፎል፡፡ በዓለም አቀፍ ታሪክ፣ ይሄ አገር በእውነት ለባሮችና ለባንዶች ፍትህ የሰጠ፣ የሃገር መሪ ያደረገ በመሆኑ በታሪክ ወርቅ መዝገብ ሊመዘገብ ይገባዋል እንላለን፡፡

ኢትዮጵያ 82 የተለያዩ ብሄር ብሄረሰብ/ ዘውጌዎች ያለት ሀገር፣ ናይጀሪያ 300 ዘውጌዎች ያላት ሃገር እንዲሁም ጋና 100 ዘውጌዎች (Ethnic groups) ያላቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡ በባርያ ንግድ የተነሳ ዘራቸው የጠፋ በኢትዮጵያ ታሪክ አልተፃፈም፣ አንዳርጋቸው አለ ካለ ምንጭ ጠቅሶ መፃፍ ይጠበቅበታል ካለዛ ውሸት ነው፡፡ አቶ አንዳርጋቻው በኢትዮጵያ የባርያ ንግድ በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍህን ለኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ኢንስቲቲውሽን አዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ማቅረብ ትችላለህ፡፡ የባርነት ታሪክ ተድበስብሶል ወዘተርፈ ሳያጣሩ ማለት የአካዳሚሽያን/ የልሂቃን ምግባር አይደለም፡፡ ችሎታ ካለህ ተጋብዘሃል!!!

SLAVERY AND THE SLAVE TRADE IN ETHIOPIA AND BEYOND / 07/12/2018 MARIE BRIDONNE AU LAISSER UN COMMENTAIRE/  SLAFNET Summer School,15-18 April 2019/ Institute of Ethiopian Studies, Addis Ababa University
Slavery and the slave trade have been an important historical feature of the Horn of Africa region. Consecutive regional polities executed slave raids into their respective hinterland well into the 20th century. The internal Ethiopian slave trade connected the political centers of Ethiopia with its peripheries, and the trade in slaves connected Ethiopia with the Red Sea  and the Indian Ocean world as well as with the Ottoman world. Various polities in the Horn of Africa were depended on, and were commercial centers for, slave labor. The regional contours of slavery are relatively well established. Despite the diversity of various forms of human bondage, slavery and serfdom, as well as the trade in slaves, and its relatively rich documentation, slavery has received little attention in the field of Eastern Africa’s social, cultural and economic history. Moreover, one feature of Ethiopia is the public silence and the absence of commemorative discourses among the descendants of owner groups, slave descendants as well as within the public sphere. This summer school is part of a program by a scholarly network focusing on slavery in the East African region providing evidence of the diverse patterns of human bondage, in order to come to a more holistic understanding of what actually constituted slavery in East Africa, and what its legacies are today.The summer school is organized by the Institute of Ethiopian Studies of Addis Ababa University, with the Hiob Ludolf Centre for Ethiopian Studies and the Department for History and Culture of the Middle East (University of Hamburg, Germany), and the Institute of Research for Development (IRD, France), under the framework of SLAFNET (Slavery in Africa: a Dialogue between Africa and Europe). We invite papers that look at the relation between slavery, labor and intergenerational stratification; as well as papers that focus on the emergence of subaltern identities as a result of slavery and the slave trade, both in Ethiopia, in the Horn of Africa, in Africa and the Middle East.
In particular, we envisage addressing some or all of the following issues: (1) Sources for the study of slavery in Ethiopia and beyond;
(2) Legal and normative approaches toward slavery by different groups in Ethiopia; (3) Statuses related to slavery and practices akin to slavery;
(4) Abolitionist approaches and the trajectories of emancipation of different categories of  enslaved persons; (5) Transformations of social relations rooted in historical slavery: post-slavery and  citizenship; (6) Gender and economic dimensions of slavery and the slave trade;
(7) Cultural, artistic, and performative dimensions of slavery, including art forms produced  by, or on, enslaved persons; (8) Connections between slavery, kinship, inheritance and succession. The summer school is open to scholars with an interest in any of the themes above. We especially encourage early career scholars and PhD students to participate. The summer school will include visit to archives, a graduate workshop, academic presentations and discussions. An exhibition on slavery will be held in the Institute of Ethiopian Studies during the summer school.
Submission guidelines The organizers welcome submissions of abstracts on the themes and questions above. We regret that we cannot provide funding for participants external to the SLAFNET Project. Limited funding is available to scholars from the region thanks to the French IFRE network in East Africa (CEDEJ & CFEE). Please send your submission before January 15th, 2019 by email to: Dr. Serena Tolino (serena.tolino@uni-hamburg.de). Submissions should include: title, abstract of 300-500 words, presenter’s name, institutional affiliation, and contact information. The selection committee will make a decision on the retained abstracts by early February 2019. All presenters will be asked to hand in a preliminary draft of the proposed paper (of no more than 2000 words) one month prior to the summer school.

የዓለም የባሪያ ንግድ ታሪክ ለመጥቀስ ያህል “የትራንስ አትላንቲክ የባሪያ ንግድ 12.5 ሚሊዮን አፍሪካዊያን በባርነት በመፈንገል ሸጠዋል፡፡ የባሪያ ንግድ ከ17ኛው እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ የተከናወነ ዓለም ዓቀፍ የባርያ ንግድ ነበር፡፡ ከ12.5 ሚሊዮኑ ባሮች አስፈሪውን የአትላንቲክ የባህር ጉዞ ሲያቆርጡ 10.6 ሚሊዮን በደህና ደርሰዋል፡፡ በዛን ዘመን የመርከቦች ጉዞ በተነሳ የባህር ወጀብና ልዩ ልዩ የተሰቦ በሽታ የተነሳ 1.9 ሚሊዮን ባሮች በጉዞው ላይ እንደሞቱ ታሪክ ይዘክራል፡፡ የትራንስ አትላንቲክ የባሪያ ንግድ 350 ዓመታት ታሪክ ያለው ነው፡፡ ዛሬ ከዚህ የባርያ ንግድ የተሸጡት ቀጣይ ትውልዶች በአሜሪካ፣ ብራዚል፣ በብዙ ካሪቪያን ደሴቶች ጃማይካ፣ ሃይቲ ወዘተ ውስጥ ይኖራሉ፡፡
• በሃገረ አሜሪካ ባሪያ ፈንጋዬች ከአፍሪካ 388,000 ሽህ ባሪያዎች 3.6 ከመቶ ያካተተ ሲሆን ባሪያዎቹ ከሴኒጋል፣ ጋምቢያ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ማሊ፣ አንጎላ፣ ኮንጎ፣ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኦፍ ኮንጎ፣ ጋቦን፣ ጋና፣ አይቮሪ ኮስት፣ ናይጀሪያ፣ ካሜሩን እንደመጡ በዲኤንኤ (የህብለ በርሄ) የሰው ዘር አመጣጥ ሳይንስ ተረጋግጦል፡፡
• በምድረ ጃማይካ ለስኮር ፋብሪካ ግብዓት፣ የሸንኮራ አገዳ ተከላ ስራ ከአፍሪካ የተፈነገሉ ባሮች ቁጥር 1.2 ሚሊዮን ነበር፡፡
• ከምድረ ብራዚል ለግብርና ስራ ከአፍሪካ የተፈነገሉ ባሮች ቁጥር 4.8 ሚሊዮን ነበር፡፡ ምንጭ (What part of Africa did most slaves come from? By Sarah Pruitt)
“በ1494 እኤአ ሰፔን ጃማይካን በቅኝ ግዛት አደረገች፡፡ ቀጥሎም በ1655 እኤአ እንግሊዝ ጃማይካንና ካሪቪያን ደሴቶችን ቅኝ ግዛቶ አደረገች፡፡ የእንግሊዝ ቅኝ ገዥዎች ከካሪቪያን ደሴቶች ከባርባዶስ ቀጥሎ ወደ ጃማይካ ተዘዋውሮ ነበር፡፡ ከአፍሪካ አህጉር ወደ ጃማይካ ለስኮር ፋብሪካ ልማት ግብአት ለሸንኮር አገዳ እርሻ ልማት ሠራተኝነት 600,000 ሽህ ባሮች ተወስደዋል፡፡ በብሪቲሽ አሜሪካን ባርያ ፈንጋዬች ጃማይካን ቅኝ ተገዥ በማድረግ ስኮር ምርት ወደ ውጪ ንግድ በመላክና በገቢ ንግድ ወደ ጃማይካ ባሪያ በማስገባት የዓለም ዓቀፍ ንግድ ሥርዓት ይከናወን ነበር፡፡ ከአፍሪካ አህጉር ወደ ጃማይካ በባርነት የተፈነገሉ አገሮች ውስጥ ከጋና፣ አይቬሪኮስት፣ ቤኒን፣ ቶጎ፣ ናይጀሪያ፣ ካሜሩን፣ኮንጎ፣ሴኒጋል እና ጋምቢያ የተጋዙ መሆናቸውን በዲኤንኤ (የህብለ በርሄ) የሰው ዘር አመጣጥ ሳይንስ ተረጋግጦል፡፡ በመቀጠልም ከ1845 እስከ 1917 እኤአ እንግሊዝ በትራንስ አትላንቲክ አፍሪካን የባርያ ንግድ ሲቆረጥ ለስኮር ፋብሪካ ሥራ ከህንድ በጉልበት ሠራተኞች ስም አምጥታ ነበር፡፡ ዛሬ 180 ሽህ የህንድ ተወላጆች በጃማይካ ይገኛሉ፡፡ ከ1854 ጀምሮ በ1980 እስከ 1990 እኤአ ከምድረ ቻይና በሠራተኞች ስም ወደ ጃማይካ ገብተዋል፡፡ ዛሬ 30 ሽህ ቻይና ተወላጆች በጃማይካ ይገኛሉ፡፡ በሃገረ ጃማይካ 2,671,000 ሚሊዮን ከአፍሪካ የመጡ ልዩ ልዩ ህብረ ብሄር ዘውጌዎች ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ በጃማይካ 90 በመቶ ከአፍሪካ የመጡ ዘውጌዎች ሲሆኑ በሃይቲ ደግሞ 95 በመቶ አፍሪካዊያን ዘርያዎች መሆናቸው ተረጋግጦል፡፡” ታዲያ አንዳርጋቸው ነጮቹን ባርያ ፈንጋዬች ሳያወግዝ፣ በጥቁር ባርያ ፈንጋዬች ማላዘን ምን ይሉታል፡፡ ምንጭ “The English slave trade to Jamaica, 1782-1808 by Herbert S. Klein
ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሆኑ ጃማይካኖች እንዳሉ የታሪክ ድርሳናትና አጥኝዎች በማስረጃ ይገልፃሉ፡፡ ከብዙ ክፍለ ዘመናት ጀምሮ በአውሮፓውያንና በአረብ የባርያ ፈንጋይ ነጋዴዎች፣ 100 ሚሊዮን አፍሪካዉያን ከመኖሪያ ቀያቸው ታፍሰው በባርነት ተፈንግለው ተወስደዋል፡፡ ለጃማይካ ልዕካን ቡድን አቡነ ባስሊዎስ ከአንድ ምዕተ ዓመት በፊት ከኢትዮጵያ ወደ ጃማይካና ምዕራብ ዓለም ኢትዮጵያዊያን በባርነት እንደተወሰዱ ገልጸውላቸዋል፡፡ በ1966 እኤአ ቀ.ኃ.ሥ. ጃማይካን በጎበኙ ወቅት እንተተናገሩት ‹‹ኢትዮጵያና ጃማይካኖች ግንኙነት ከብዙ ዘመናት ያስቆጠረ ነው፡፡›› በዚህም ጃማይካኖችና ኢትዮጵያን ወንድማማቾች ናቸው በደም፡፡ በተመሳሳይ በጀርመን ድምፅ ዶችቤሌ ሬዲዬ ራስ ተፈሪያኖች ጥንታዊ ዝርያቸው ከኢትዮጵያ ከወደ መንዝ እንደሆነ በጥናት አረጋግጠዋል፡፡ የሚል የዜና ዘገባ አቅርበው ነበር ስለዚህ ጉዳይ ጋዜጠኞቹ ዘገባውን ቢፈልጉትና መረጃውን ለህዝብ ቢያካፍሉሳ!
“Centuries ago over 100 million Africans were kidnapped from their native home and enslaved by European and Arab slave traders. Although most of these Africans were stolen or sold from West Africa, it is important to note that slaves were taken from as far as Mt.Kenya in East Africa. In 1961 (Western calendar) when a delegation of Jamaicans visited Ethiopia, they were told by the late Abuna Basillos that the people were taken from Ethiopia and brought to the Western world centuries ago. When His Imperial Majesty Emperor Haaile Selassie I visited Jamaica in 1966, he told us that “Ethiopias and Jamaicas have a relationship going back for a very long time,” and that Jamaicans and Ethiopians were brothers by blood.” https:// www. Africaresource.com> rasta ምንጭ (Jamaicans of Ethiopian origin By P.Napti, April 7, 2012)

አንዳርጋቸው በገፅ 156 ‹‹ ሻምበል ፍቅረስላሴ የተጠቀሰው የአቶ ገበያው ዓይነት አነጋገር እዛ ቤተመንግሥት ውስጥ ብቻ የተጀመረ እንደማይሆን እርግጠኛ ነኝ፡፡ በመንግሥቱ ኃይለማርያም ከህጻንነት ጀምሮ በነበረ አስተዳደግ ላይ የመቶ አለቃ ገበያው አይነቱ ሰው አነጋገር ምን ተጻእኖ ነበረው ሰውን ባሪያ እያሉ የሚንቁና በሚያዋርዱ በመልካቸው ቅላት፣ በከንፈራቸው መሳሳት፣ በጽጉራቸው መለስለስ፣ በሃብታቸው ትልቅነት መኮፈስ በሚያሳዩ ሰዎች ላይ ጥላቻ ይዞ ወጣቱ መንግስቱ የማያድግበት ምክንያት አይታየኝም፡፡ እኔም ብሆን የማደርገው ነው፡፡›› ይላል፡፡ አንዳርጋቸው አስተሳሰብ ከመንግሥቱ ኃይለማርያም በምን ተሸለ!!! ታሪክን በዚህ መልክ ለልጆችህ ለማስተማር መፈለግህ ያሳዝናል፡፡ የቂም በቀል የታሪክ ዘመቻ አይሆንም መቼ ይሆን ለልጆችህ ደጉን ነገር የምታወርሰው፡፡

ዘመቻ አንድአርጋቸው !!! ዳግማዊ ቢሊሱማ ውልቂጤማ!!!

የመፅሃፉ ተልእኮ የሴራ ፖለቲካውን ከእስር ቤት ከወጣህ በኃላ በመጨማመር 1ኛ አዲስ አበባ የኦሮሞ መሬት ነበረች አዲስ አበባ የአያቶቼ ጥጃ ማሰሪያ ከገፅ 56 እስከ 70፣ አዲስ አበባ የወታደሮች፣ የባሪያዎች እና የሴተኛ አዳሪዎች ከተማ ከ71 እስከ 140 ገፅ የታሪክ መፅሃፍት መረጃ ሳያጣቅስ፣ የሃገራችንን ታሪክ ፀሃፊዎች በማጥላላትና በማናናቅ የእራሱን የበታችነት ስሜት ለመበቀል፣ እንደ መንግስቱ ኃይለማርያም (የባሪያ ልጅ እያሉ ይሰድቡት ነበር!) የልጅነት የሥነልባና የባርነት ጠባሳ፣ እንደ መለስ ዜናዊ (የመለስ አባት የጣልያን ሹንባሽ ስለነበሩ፣ የባንዳ ልጅ እያሉ ይሰድቡት ነበር!)፣የልጅነት የሥነልባና የባንዳነት ጠባሳ፣በህሊናው አምቆና ደብቆ ማህበረሰቡን ለመበቀል የተነሳው አንድአርጋቸው፣ሃገሩን የማይወድ፣ የክህደት ታሪኩ ከመኢሶን ወደ ኢህአፓ፣ ከኢህአፓ ኢህአን፣ ከኢህአን ወደ ኢህዴን፣ ከኢህዴን ወደ ቅንጅት፣ ከቅንጅት ወደ ግንቦት ሰባት፣ ከግንቦት ሰባት ወደ አዜማ የፖለቲካ ዥዋዤዌ ሲጫወት፣ በእድሜው ቁማር ሲቆምር ያሳለፈ፣ በሎንዶን በፈረስ ውድድር ቁማር ጥርሱን የነቀለ (The Gambler of London)፣ ከኢህአፓ/ኢህአሠ እስከ አርበኞች ግንቦት ሰባት በሴራ ፖለቲካ ለስልጣን ለግል ጥቅም በህይወቱ ጥብጢብ የተጫወተ ትላንት ከህወኃት/ኢህአዴግ ዛሬ ደግሞ ከኦህዴድ/ ኦዴፓ/ኢህአዴግ ጋር በማሴር ከኤርትራ ምድር ሚሳኤል አስወንጭፈን ወያኔን አይኑን አጠፋንው፣ ህወሓትን በጦር ሜዳ ዉጊያ በቆረጣና በደፈጣ አስወገድንው ይሉናል፡፡ አርበኞች ግንቦት ሰባት በአንድ ጀንበር ትጥቅ በመፍታት በዓለም ነፃ አውጪ ታሪክ በጊኒስ መፅሃፍ ግን ሳታስመዘግቡት ቀራችሁ!!!፡፡ የዴሞክራሲ አብሪ ጥይቶች አጠፉት፣ የኢሳትን ትንታግ ሞተር ጋዜጠኞች ጎደኞቻቸውን አባረሩ፣ አድርባይ ተጎታች ጋዜጠኞች ኢዜማ ጋር ወደፊት!!! ከኦህዴድ/ኦዴድ/ኢህአዴግ ጋር ወደፊት እያሉ ድቤ ይደበድቡ ጀመር፡፡ ጁሃር ትንኮሳ እስክንድር እንደአንበሳ አገሳ ይለና፣ እስክንድር የራሱ የእውቀት ልዕልና ያለው ልሂቅ ነው፣ እናንተ ፖለቲከኞቹ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ የባልደራስ የአዲስ አበባ ጥያቄን በፀረ ዴሞክራሲያዊነት ሊያጣጥለው ሞከረ፣ከንቲባው እንኮ እንዴት አልገባ አለው ብዬ በጊዜው አዘንኩኝ፡፡ የከንቲባው ፀሃፊም አቶ አንዳርጋቸውም የእስክንድር ጉዳይ፣ የነብር ጭራ ከያዙ ሆነባቸው፣ የእኛ ፖለቲከኞች የሰውን ጭንቅላት ማንበብ ቻሉ እንዴ፣የካምቦሎጆ ዝምታ!!!

ዘመቻ አንድአርጋቸው !!! ዳግማዊ ቢሊሱማ ውልቂጤማ!!!

ኤርትራ አደሮች!!! አርበኞች ግንቦት ሰባት፣ ኦነግ፣ ሲአን፣ ኦብነግ ወዘተርፈ ሁላ፣ ህወኃት/ኢህአዴግ በየትኛው የጦር ሜዳ እንዳሸነፉ ሊነግሩን ይገባል!!! እንዲያውም የወያኔ ሹማምንቶች በኤች አር 128 ስብዓዊ መብት ጥሰት ለዓለም ፍርድ ቤት ለማቅረብና በየትኛውም ዓለም እንዳይንቀሳቀሱ በተባሉበት፣በዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት የመቅረባቸው ጉዳይን ያዳፈኑ ግንቦት ሰባት፣ ኦነግ፣ ሲአን ወዘተርፈዎች መሆናቸውን በሃገሪቱ ተቀጣጥሎ የነበረውን ስር ነቀል ለውጥና የዴሞክራሲ አብሪ ጥይቶች አጠፉት፣ አንድ ቀን ታሪክ ያወጣዋል፡፡ እነዚህ ድርጅቶች ወያኔ ሹማምንት ለፍርድ እንዳይቀርብ፣ የወያኔ ወንጀለኞች መቀሌ እንዲመሽጉ ያደረጉ፣ በትግራይ የሃገሪቱ የጦር መሳሪያ የታንክ፣ የጦር ተዋጊ አይሮፕላን እንዲሁም የሃገራችን የጦር መሳሪያ ግምጃ ቤት በኤርትራ ጦርነት ጊዜ ተወስዶ በትግራይ እልቆ መሳፍርት ክምችትን እንዳለ አይተው እንዳላዩ የሆኑ፣የኢንሳ የፀጥታ መሳሪያዎች ተነቅለው መቐለ ሲወሰዱ ዝም ያሉ፣ ወያኔ ከሃገራችን የዘረፈውን ሃብትና ንብረት እንዳይመለስ ያደረጉ የፖለቲካ ባንዳዎች የቀረውን ሃብትና ስልጣን ለመቆደስ የኦህዴድ/ኢህአዴግን የኮነሬል አብይ አህመድን መንግሥት በመደገፍ ጎዛቸውን ሸክፈው የገቡ ምሁራን ስብስብ ናቸው፡፡ ኢዜማና መስርተው አማራ የለም!፣ የአማራ ብሄርተኝነት የለም!! አማራ በኢዜማ ሥር መደራጀት አለበት፡፡ ህዝባዊ ድጋፍ ያገኙ የአማራ ድርጅቶች ማበብ አብን፣ መአህድ፣ ወዘተ የእራስ ምታት የሆነባቸው የኦህዴድ ተረኛ ገዥዎች በኢዜማ እየተደገፈ በኢሳት አጫፋሪነት ፍርፋሪ ለቀማ፣ የቴሌቪዝን ጣቢያዎች በመቆጣጠር (ኢሳት አድርባዬች)፣የድረገፅ (ሳተናው፣ ዘሃበሻ፣ ሹምባሾች) በፀረ ዴሞክራሲነት የኦዴድ/ኢህአዴግ መንግሥት ጭፍራ በመሆን የአብይ መንግስት ከወደቀ በኢትዮጵያ የምፅዓት ቀን ይመጣል (Doomsday)፣ ይለናል፣ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በዋሽንግተን ዲሲ የመፅሃፍ ምርቃት ላይ የዶክተር አብይ መንግሥት ከሌለ ኢትዮጵያ ለመፍረስ 80 በመቶ አደጋ ውስጥ ትገኛለች በማለት የኒውክለር ቦንቡ ቁልፍ በአብይ እጅ እንደሆነ ይተርካል፡፡

ዘመናዊ ባርነት ትርጉም (Modern slavery meaning) በምድረ እንግሊዝ በሎንዶን ከተማ በ2016 እኤአ ብቻ 11700 ሰዎች በዘመናዊ ባርነት ውስጥ እንዳሉ ቢቢሲ ዘግቦል፡፡ በሀገረ እንግዚዝ ተቀምጠህ የሚፈፀመውን ዘመናዊ ባርነት ብተርክልህ የአገርህ የቅምቅም እና አያትህ ዘመን የተፈፀመ ባርነት ለማነፃፀር ይጠቅምህ ይሆናል በሚል ነው፡፡ በሃገረ እንግሊዝ ዘመናዊው ባርያዎች ፓስፖርታቸው፣ መታወቂያ ካርዳቸው እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ስልካቸው በዘመናዊ የባርያ ፈንጋዩቹ ተነጥቀው ከመኖሪያ ቤት ውስጥ ባርያ የሆኑ ግለሰቦች ናቸው፡፡ የባሮቹ እንቅስቃሴ የተገደበ ሆኖል፣ከባድ የጉልበት ስራ ያለክፍያ ይሰራሉ፣ የአካል ጥቃትና የተመጣጠነ ምግብ የማግኘት ስቃይ ይደርስባቸዋል፣የወሲብ ጥቃት፣ ያለፍቃድ ጋብቻ፣ የህጻናት የጉልበት ብዝበዛ ወዘተ ይፈፀምባቸዋል፣ ዘመናዊ ባርነት ትርጉም {Modern slavery includes – forcedlabor, bonded labor, domestic servitude, sex trafficking, forced marriage and child labor} ምንጭ (modernslavery.co.uk)
የአንዳርጋቸውን መፅሃፍ ገንቢ ሂስ ለማጠቃለል እውቁ የአሜሪካ ፀሃፊ ሱሳን ሶንታንግ በሚለው እንደምድም ‹‹እውነቱ እንዲህ ነው ሞዛርት፣ ፓስካል፣ ቡሊን አልጀብራ፣ ሸክስፒር፣ ፓርላሜንታዊ መንግስት፣ ሥልጣን ያላቸው ቤተክርስቲያኖች፣ ኒውተን፣ የሴቶች ነፃነት ተሞጋጮች፣ ካንት፣ ማርክስ፣ እና ብላንቺን ባሌት፣ በዚህ የሰው ልጆች ስልጣኔ ለዓለም ያበረከተውን ስልጣኔ፣ መታደግ አሊያም ቤዛ መሆን አይቻላቸውም፡፡ በሰው ልጆች ታሪክ የነጭ ዘር የካንሰር በሽታ ነው፡፡›› “The truth is that Mozart, Pascal,Boolean algebra, Shakespeare, parliamentary government,baroque churches, Newton, the emancipation of women,Kant, Marx, & Blanchine ballets don’t redeem what this particular civilization has wrought upon the world. The white race is the cancer of human history.” Susan Sontag- American essayist”

 ምንጭ
• A chronology of key events in Ethiopia history/ Ethiopian foreign policy
• Ethiopian time line chronological timetable of events- worldatlas.com
• Ethiopian profile- Timeline- BBC News
• History of Ethiopia- Wikipedia
• History of Ethioipia- HistoryWorld
• ሪፖርተር መጽሔት/ ሰኔ 1990ቅጽ ፻ ቁጥር 10 ገ

Filed in: Amharic