>

ቄሮን የማደንቆር እኩይ አላማ!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

ቄሮን የማደንቆር እኩይ አላማ!!!
አቻምየለህ ታምሩ
«ከማኅበራዊ ሜዲያና ከብዙሐን መገናኛዎች  እየራቅሁ ነው» ያለን ጃዋር የአማራ ጉዳይ የተነሳ ሲመስለው ግን ርቆ መራቅ የማይሆንለትም! 
—-
አንድ ወዳጄ ከወራት በፊት በውስጥ መስመር በኩል «ጃዋር መሐመድ ከማኅበራዊ ሜዲያና ከብዙሐን መገናኛዎች መራቅ እፈልጋለሁ ያለውን እንዴት ታየዋለህ?» የሚል ጥያቄ አቅርቦልኝ  ነበር። እኔም በመልሴ «ሐጂ ጀዋር የኦነግ ልጅ ነኝ ብሏል፤ የኦነግ ልጅ እንደመሆኑ መጠን ከማኅበራዊ ሜዲያና ከብዙሐን መገናኛ መራቅ እፈልጋለሁ ቢሉም ስለ ኦሮሞ ሳይሆን  የአማራ ጉዳይ የተነሳ ሲመስለው ግን «ለመተንተን» ተመልሶ ይመጣል» ብዬው ነበር።
እንዳልሁትም ወለጋ ግፉዓን በኦነግ ሸኔ ሲዘረፉ፣ሲረሸፉና አስከሬናቸው ሲቃጠል፣ ከሀያ በላይ ባንክ በኦነግ ሲዘረፍ፣ቡራዩ የዘር ፍጅት ሲካሄድ፣ ሻሸመኔ ሰው ዘቅዝቀው ሰቅለው ግዳይ ሲጥሉለት፣ከአርሲ ወደ ወለጋ ይጓዝ የነበረው ተሿሚ በኦነግ ዐይኑ እንደ ሙጀሌ ተነቅሎ ሲወጣ፣ሐረር ባንክ ሲዘረፍና ንጹሐን ሲገደሉ፣ወዘተ  አንድም ሳይተነፍስ  ከማኅበራዊ ሜዲያና ከብዙሐን መገናኛዎች የራቀ የመሰለው ጃዋር መሐመድ ከአማራ ጋር የሚያገናኝ  አንዳች ነገር  የተከሰተ ሲመስለው ግን «በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ»  እየተባለ «ትንተናና አስተያየት» ሊሰጥ በቴሌቭዥኑ  መስኮት እንዲሁም በፌስቡኩ ዱቅ ይላል።
ከአማራ ጋር ይያያዛሉ በተባሉቱ የአጣዬውን  የኦነግ ጭፍጨፋ፣ የከሚሴውን  የኦነግ ወረራ፣ የአዲስ አበባ የባለቤትነት ጉዳይ፣ የሰኔ 15ቱን  የባሕር ዳር ግድያ፣ የአማራ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዳመጡ ተደርጎ በማኅበራዊ ሜዲያ ውጤታቸው የመታየቱን  ጉዳይ ተከትሎ ከሁሉ አስቀድሞ በፌስቡኩ  አስተያየት የሚሰጠውና በቴሌቭዥኑ  ቀርቦ የሚተነትነው ከማኅበራዊ ሜዲያና ከብዙሐን መገናኛዎች  እየራቅሁ ነው ያለውን ጃዋር መሐመድ ነው።
ከማኅበራዊ ሜዲያና ከብዙሐን መገናኛዎች እየራቅሁ ነው ያለውን ጃዋር መሐመድ ከአማራ ጋር የሚገናኝ  ጉዳይ  የተነሳ ሲመስለው ከራቀበት የማኅበራዊ ሜዲያና ከብዙሐን መገናኛዎች ከሁሉም በፊት ቀርቦ በመገኘት አስተያየትና ትንተና የሚሰጠው የአባቱ  ቤት ማለትም የኦነግ ቤት ፖለቲካ
 የሆነው አማራ ይጠላዋል ብለው የሚያስቡትን መጥላት፤ይወደዋል ብለው  የሚያስቡትን ደግሞ መውደድ ፖለቲካው ስለሆነ ነው። ስለኦነጋውያን ፖለቲካ  የበለጠ ለመረዳት «የኦነጋውያን ፖለቲካ የጥንብ አንሳ ፖለቲካ» በሚል የጻፍሁትን ያነቧል።
በእስካሁኑ ትዝብቴ  ከማኅበራዊ ሜዲያና ከብዙሐን መገናኛዎች  እየራቅሁ ነው ያለውን ጃዋር በኦሮምኛም ይሁን በአማርኛ  በፌስቡክና በቴሌቭዥኑ አስተያየትና ትንተና ያለፈበትን ወቅት አላስታውስም።
እነሆ ዛሬ ከማኅበራዊ ሜዲያና ከብዙሐን መገናኛዎች የራቀው ጃዋር «ሕፃናትን ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ አማርኛ ቋንቋን ይማራሉ ማለት ጦርነት ማወጅ ነው» የሚል ነገር ይዞ መጥቷል። ጃዋር ይህ የአማርኛ ጥላቻ ጅራፉን ይዞ ብቅ ያለው ትምህርት ሚኒስቴር ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ አማርኛና እንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲሰጥ ወስኗል ያሉትን በመቃወም ነው። ልብ በሉ አዲሱ ፖሊሲ ሕጻናት ከአንደኛ ክፍል ጀምረው የባዕድ ቋንቋ የሆነውን እንግሊዝኛ ቋንቋን እንዲማሩ ይደነግጋል። ለነጃዋር ጦርነት የሚሆነው ኢትዮጵያዊውን ቋንቋ አማርኛን  ከአንደኛ ክፍል ጀምረው  የኢትዮጵያ ሕጻናት መማራቸው እንጂ  የባዕዱን ቋንቋ እንግሊዝኛን  ከአንደኛ  ክፍል ጀምሮ መማራቸው አይደለም።
ጃዋር ልጁን በሚያስተምርበት አገር ሕጻናት ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እስከ ሶስት  ቋንቋ ድረስ ይማራሉ።  ምንም እንኳ አማርኛ የአማራ ቋንቋ ብቻ ባይሆንም ፖለቲካው ግን  የአማራ ጥላቻ ስለሆነ ልጁን በሚያስተምርበት አገር ሕጻናት የሚያገኙትን  እድል የኢትዮጵያ የድኃ ገበሬ ልጆች እንዳይጠቀሙበት ሳይመረምሩ የሚከተሉትን የጥላቻ ፖለቲካ ሰለባዎች  ተቃውመው ይቀሰቅሳቸዋል።  ምርምር ከማድረግ ባልተናነሰ ከአፍ መፍቻ በተጨማሪ  ሌላ ቋንቋ መማር ተጨማሪ የእውቀር በርን ይከፍታል።  በአገዛዙ በሪፑብሊካን ጋርድ የሚጠበቁት የድንቁርና መምሮቹ እነ ጃዋር ግን የእውቀት በር የሚከፍተውን ተጨማሪ ቋንቋ መማርን ጦርነት እንደማወጅ ይቆጥሩታል። አገዛዙ
ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ከአንደኛ ክፍል ጀምረው አፋቸውን ከፈቱበት ቋንቋ  በተጨማሪ  ምርጫቸው የሆኑ ተጨማሪ የአገራችንን ቋንቋዎች ቢማሩ የእውቀር በር ይከተትላቸዋል እንጂ ጃዋር እንዳለው ጦር ሜዳ እንደመግባት አይነት ጉዳት አይደለም። የአገራችን ታላላቅ ሰዎች ሁሉ ከአንድ በላይ ቋንቋ የሚናገሩ ናቸው። ታላላቆቹ እነ  እነ  ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም፣ ከንቲባ ገብሩ ደስታ፣ ዶክተር ሎሬንሶ ታዕዛዝ፣ ፀሐፌ ትዕዛዝ  አክሊሉ ሃብተ ወልድ፣ ብላታ ደሬሳ አመንቴ፣ አናሲሞስ ነሲብ፣ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ አቶ ሐዲስ አለማየሁ፣ ዶክተር ገብረ ሕይዎት ባይከዳኝ፣ አቶ አሰፋ ጫቦ፣ በአሉ ግርማ፣ ወዘተ… ጳውሎስ ኞኞ፣ ኢላላ ኢብሳ፣ ወዘተ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ከሆኑት ከአማርኛ፣ ከኦሮምኛ፣ ከትግርኛ፣ ወዘተ. . .  ወዘተ በተጨማሪ  ከውጭ አገር ቋንቋዎችም እንግሊዝኛን፣ ፈረንሳይኛን፣ አረብኛን፣ ሞስኮብኛን፣ ጀርመንኛንን፣ ወዘተ በልጅነታቸው የተማሩ ናቸው። ለእነዚህ የኢትዮጵያ ታላላቅ ሰዎች  ሰፊ የእውቀት በር የተከፈተላቸውና ታላቅ ሰው ለመሆን የቻሉት ብልሆቹና አሳቢዎቹ ወላጆቻቸውና ቤተሰቦቻቸው  ከአንደኛ ክፍል፣ ከልጅነታቸው ጀምሮ ከአንድ በላይ ቋንቋ እንዲማሩ ስላደረጓቸው ነው። የድንቁርና መምሕሮቹ ግን የኢትዮጵያ  የድኃ ገበሬ ልጆች የእውቀት በር እንዳይከፈትላቸው ከአንድ በላይ የኢትዮጵያ ቋንቋ መማርን ጦርነት እንደማወጅ አድርገው ይዘምቱበታል።
አንድ ሰው አማርኛ የሚማረው ለአማራ ሲልም ይመስላቸዋል። እንዲህ የሚያስቡ ሰዎች እስከ ሶስተኛ ዲግሪ ድረስ እንግሊዝኛ ሲማሩ ግን ለእንግሊዞች ነው ብለው አያስቡም። እያንዳንዱ አማርኛም ሆነ ሌላ ቋንቋ የሚማረው የእውቀር በር እንዲከፈትለት ለራሱ ሲል እንጂ ለማንም አይደለም። ትግርኛ በማወቄ ተጨማሪ የእውቀት በር ተከፍቶልኛል።
እኔ ትግርኛ ያወቅሁት ለራሴ እንጂ ለትግሬ ብዬ አይደለም። እንዴም ትግርኛ በማወቄ  የተጎዳው ትግርኛ ተናጋሪው ሕወሓት ነው። ትግርኛ በማወቄ ተደብቀው በትግርኛ የሚጽፉትን ብዙ ሚስጥራቸው እንዳውቅና እየተረጎምሁ  በፌስቡክ በመልቀቅ እንዲጋለጡ አድርጌያለሁ። እነዚህ አማራን የጎዱ እየመሰላቸው ሕጻናት ተጨማሪ ቋንቋ እንዳይማሩ የሚያደርጉ ጥንብ አንሳዎች ግን  የሕጻናቱን የእውቀት በር ከመዝጋታቸው በስተቀር በአማራ ላይ የሚያስከትሉት አንዳች ጉዳት እንደሌለ ያወቁ አይመስሉም።
ቄሮን የማደንቆር እኩይ አላማ
ሓጂ ጃዋር(አባ ሜንጫ) መንጋዎቹን ይዞ ለቅሶ ተቀምጧል። ምክኒያቱ ደግሞ አማርኛ ቋንቋ ለምን ከ፩ኛ ደረጃ ትምህርት ጀምሮ ይሰጣል ነው።
ጉዳዩን ስንመረምረው የጃዋር ለቅሶ ዋና ምክኒያት ህወሓት አደንቁሮ ያስረከበውን መናኛ መንጋ ከእንቅልፉ እንዳይነቃበት ነው። የጃዋር ተፅዕኖ ፈጣሪነት አንዱ ምክኒያት የአማርኛ ቋንቋ ችሎታው ከቄሮ የተሻለ በመሆኑ ነው።
እናም ቀጣዩ የቄሮ ትውልድ አማርኛ የሚችል ከሆነ ሓጂ ጃዋር በጅራፍ ሊነዳው አይችልም። ምክኒያቱም አማርኛን የሚችል ቄሮ ከተፈጠረ በራሱ የሚተማመን ስለሚሆን የጃዋር ጉዳይ ያከትማል። ስለዚህ ሓጂ ጃዋር ወጥሮ የሚያለቅስበት አብይ ምክኒያት ይሄ ነው።
በኢትዮጵያ ውስጥ ለመንጋ ፖለቲካ መፈጠር ዋና ምክኒያት በቋንቋ የታጠረው ፌደራሊዝም ትውልዱን እንደዝንጀሮ በተወሰነ የቦታ ክልል ውስጥ ብቻ እንዲቆራኝ ስላደረገው የስነልቦና ትስስሩም እንዲሁ በአንድ ክልል የተገደበ በመሆኑ በራስ የመተማመን መንፈሱ ደካማ ስለሆነ በቀላሉ በሌሎች ተፅዕኖ ስር ስለሚወድቅ ነው።
የህወሓት ጉዳይ ከመለስ ሞት ጋር ያከተመበት አንዱ ምክኒያት ህወሓት እንደመለስ አማርኛን እንዳሻው እየሰነጠቀና እየፈተለ ሲለውም ወደፈለገው አቅጣጫ እያጣመመ የሚችል ሰው አለማግኘቱ ነው።
ስለዚህ የሓጅ ጃዋር ጩኸት አሁን በስራ ላይ ያለው የትምህርት ፖሊሲ ያደነዘዘለትን ትውልድ ከእንቅልፉ እንዳይነቃበት ያለመ እኩይ እንቅስቃሴ ነው።
ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ!
Filed in: Amharic