>

የአማርኛ ጥላቻው ዜጎችን እስከመስቀል ትምህርት ቤቶችን እስከማፍረስ ደርሷል! (ታምራት ገመዳ)

የአማርኛ ጥላቻው ዜጎችን እስከመስቀል ትምህርት ቤቶችን እስከማፍረስ ደርሷል!!!
ታምራት ገመዳ
ኦሮሚያ ክልል አማርኛ የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች ላይ “ዘላለማዊ እርምጃ ውሰዱባቸው” ትምህርት ቤቶቹ እንዲፈርሱ እና መምህራኑም “ዘላለማዊ እርምጃ” እንዲወሰድባቸው (ማለትም ራቁታቸውን ተዘቅዝቀው ተሰቅለው ሬሳቸው መሬት ላይ እንዲጎተት) ተወስኖባቸዋል::
የቁቤ አክቲቪስቶች በላቲን ፊደል ለደጋፊዎቻቸው በስፋት  እያስተላለፉት እና እየተተገበረ ያለ ፋሽስታዊ መልእክት
የጃዋርን ጥሪ ተከትሎ በኦነግ/ኦህዴድ አመራር ሰጭነት በኦሮሚያ ክልል የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ኦሮሚኛ ውጭ የሆኑ ዜጎች የሚማሩባቸው ትምህርት ቤቶች እየተዘጉና እየፈረሱ  ነው።
ቋንቋን ተከትሎ የመጣው ጥላቻ መሰረቱ ትላንት የኖረው አንድ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ የሀስት ትርክት ውጤት ነው ።ምርጫው የኦዴፓ(ኦህዴድ) ነው። እስካሁን ሁለት ቦታ እየረገጠ አንዴ በእነ ጃዋር አንዴ በእነ ዳውድ አንዴ በእነ ጃል ማር አንዴ በእነ ለማ መንገድ እንደፈለገ ስልቱን እየቀያየረ ሊሄድበት ያሰበው ሁሉን አማራጭ የፖለቲካ መንገድ ብዙ ርቀት አልወሰደውም። ነገም የትም አያደርሰውም።
ሕገ መንግሥቱ አይነካብን እያለ የሚሟገተው አካል ጃዋርን ጨምሮ የህጻናቱን ህገ መንግስታዊ መብት ጥሶ በአደባባይ የጠራው የጥላቻ ዘመቻ በክልሉ መንግሥት ተግባራዊ ሆኗል። ወላጆች አቤት የሚሉበት አጥተዋል ። ይህን ድርጊት የፌደራሉ መንግሥት አላየሁም ሊል አይችልም። ጭንብሉን አውልቁ እና አጀንዳችሁን ወይ ፊት ለፊት አምጡት።ትላንት ከስልጣን ዋዜማ በለንደን ጉባዔ ሲባል እንደነበረው ኢትዮጵያ ካልፈረሰች የኦሮሚያ ጥቅም አይከበርም የሚለው አካሄድ አያዋጣም።መምረጥ እና አንዱን መንገድ መከተል ያስፈልጋል። ከዚህ ውጭ ዜጎችን በገዛ አገራቸው መድረሻ ማሳጣት መዘዙ ብዙ ነው። ሰላምን የሚያደፈርስ እርምጃ እየወሰዱ፣ዘራፊዎችን እና የዘር ጥላቻ ያነገቡ ወገኖችን እርምጃ እየፈጸሙ ስለ መደመር ሆነ መሻገር ማውራት ትርጉም የለውም።
4800 ህጻናት ከሳምንት በሁዋላ የሚገቡበት ትምህርት ቤት  የለም
ለምን በአገሪቱ የሥራ ቋንቋ በአፍ መፍቻቸው እና አፍ መፍቻቸውም ባይሆንም እንኳን  በምርጫው የመማር መብታቸው አልተከበረም። አይሻሻልብን የሚባለው ህገ መንግሥት ጭምር የሰጠው ዋስትና እየተሻረ  ነው። ይህ አካሄድ እንደ ቀልድ የሚታይ አይደለም ።የዚህ የጥላቻ ዘመቻ የጠያቂው አያቶላን ብቻ አድርጎ መቁጠርም ሞኝነት ነው።መፍትሄው አንድ ብቻ ነው።ጭንብልን አውልቆ አገር አፍርሶ አገር የመመስረት አጀንዳን በግልጽ አቅርቦ ለማስፈጸም መንቀሳቀስ ወይም እጅ የገባን ሀላፊነት በአግባቡ መወጣት።
መንግሥት በአፋጣኝ ለዜጎች ጥያቄ ዝም ታውን ትቶ አወጣሁት ባለው የትምህርት ፍኖተ ካርታ እና በተቃውሞው ላይ  አቁዋሙን ግልጽ ያድርግ።ለዜጎች ጩኸት ምላሽ ይስጥ።
ምስል አንድና ሁለት ፦ ልጆቻችንን የት እናስተምር? ያሉ ወላጆች ለተቃውሞ ተሰባስበው
ምስል ሶስት ፦ የምታዩት ትምህርት ቤት ቡራዩ ላይ አማርኛ በማስተማሩ ብቻ እንዲፈርስ ተወስኖበታል:: ወደ ማፍረሱም ተገብቷል።
Filed in: Amharic