>

ዛሬም መባነን ለማይፈልጉቱ እንቅልፋሞች!!! (ዮናስ አበራ)

ዛሬም መባነን ለማይፈልጉቱ እንቅልፋሞች!!!
ዮናስ አበራ
ከእውነት የተጣላ ማህበረሰብ እንደቆመ ውሃ እንቁረሪትና አልጌ ብቻ ነው የሚያፈራው ቀልደኛ !!!
 
በበረከት ስምኦን ፥ በክንፈ ዳኘው እና በአብዲ ኤሌ መታሰር ብቻ ተንገራግጮ የቆመው የአብይ አህመድ የታይታ ለውጥ ሩጫውን ጨርሷል።
ከዚህ በኋላ እንኳን ለውጥ ሊመጣ “ኢህአዴግ ለሚቀጥለው ምርጫ ወደ አንድ ፓርቲነት ተዋህዶ ነው የሚወዳደረው” እያለልህ ነው ያንተ አሻጋሪ፤ የድሮዎቹ ቲያትረኞች በአብይ አዝማችነት በ season – 2 ሊመጡብህ ነው ወገኔ። አሁንም የኦዴፓ/የኦነግ/የጃዋር/የዳውድ ኢብሳ/የታከለ ኡማና የአብይ አህመድ ምንም አልገባህም! ስነግርህ አትሰማኝም እኮ፥ ወሬ ታያለህ።
አንድ ትንሽ ምሳሌ ለስጥህ እስቲ ዛሬ እንኳን ከገባህ:>
አብይና የትምህርት ሚኒስትር ይወያዩና የሰሞኑን የትምህርት ቤቶች የቋንቋ ካሪኩለም ምን መምሰል እንዳለበት በቅጡ ያልታሸ አሻሚ የሆነ “ፍኖተ ካርታ” እያሉ የሚጠሩትን ነገር አውቀው ለቀቁ፤ ህዝቤ አጀንዳ አገኘና እሱ ላይ ተረባረበ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃዋር ከኦሮምኛ ቋንቋ ሌላ ኦሮሚያ ላይ ይሰጥና ጉድ ይፈላል ሲል አስጠነቀቀ፤ የኦሮሚያ ምክትል ፕሬዚዳንት (ማንትሴ ሽመልስ) ይነሳና የጃዋርን ዛቻ መንግስታዊ/ህጋዊ አደረገና አስተጋባ፤ አሁንም እኛ ተጨማሪ አጀንዳ አገኘንና እሱ ላይ እንደ ግሪሳ መስፈር፤ አብይ አሁንም ባላየ ማለፍ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች እሱ ላይ አጥንት እንዳገኘ ጉንዳን ሲረባረቡ ሌላ አርዕስት እያሰናዱልህ ነው ….. ኦነግ/ኦዴፓ/አብይ/ታከለ/ታዬ ደንደአ/ዳውድ ኢብሳ ሁሉም እየተናበቡ ነው እየሰሩ ያሉት !! They have outsmarted everyone of us!! ይሄ እውነት ነው !! ሃቅ ነው !!
ባለፈው እሬቻን አ.አ ላይ ነው የምናከብረው ሲሉ ከወዲያ ጃዋር፥ ከወዲህ ታከለ ኡማ፥ ከወዲያ ፀጋዬ አራርሳ ፥ ከወዲህ ታዬ ደንደአ፥ ….. እየሆኑ ይቀባበሉሃል ፥ ፊንታ ይሰሩሃል !! አብይም ሁሉንም ባላየ ማለፍ ነው ስራው !! አጀንዳዎቹ ሲጠነሰሱ ያለእርሱ እውቅና እንዲመስልህ ተደርጎ ይቀርብልሃል – አይገባህም !!
አንተም ጎማ ሲያኝክ እንደሚውል አይምሮ ዘገምተኛ “አብይ ብቻ ነው የኢትዮጵያ አዳኝ” ብለህ ማምለክህን ትቀጥላለህ !! ሃገርና ነብስህን አስይዘህ መቆመርህን ዛሬም ቀጥለሃል…ጅል ነህና !!!
Filed in: Amharic