>

አሉላ በቀጣይ የትግራይ ኦርቶዶክስ?  እየመጣች ነው እያለን ነው!!! ( ዘመድኩን በቀለ)

አሉላ በቀጣይ የትግራይ ኦርቶዶክስ? 
    እየመጣች ነው እያለን ነው!!!
        ዘመድኩን በቀለ
★  መናበብ ይሉሃል እንዲህ ነው! ኦያኔና ኦነጌ!!!  
 
★ ህወሓትና ኦነግ ሊያፈራርሷት የሚፈልጓትን ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ የያዛትን ገመድ ለይተው ተራ በተራ መዘገቡ። 
• ዐማራ
• አማርኛ ቋንቋ 
• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ 
እነዚህ ሦስቱ ተራ በተራ መመታት አለባቸው አሉ!
•••
ብዙ ጊዜ በማንነታቸው ቀውስ የገቡ ሰዎች አደገኞች ናቸው። ለሚሠሩትም፣ ለሚናገሩትም፣ ለሚጽፉትም ነገር አይጠነቀቁም። እቆምለታለሁ የሚሉትን ህዝብ ሳይገባቸው አናቱ ላይ ይቆሙበታል። ሌሎችም እንዲቆሙበት ያደርጉታል፣ ይጋብዙታል። እቆሮቆርለታለሁ ለሚሉት ህዝብ ቆርቋሪ ጠላት ያበጁለታል። እነሱ የዚያ ብሔር ተወላጆች ስላልሆኑ ምንም አይሰቀጥጣቸውም። ደንታም የላቸውም።
••• ለምሳሌ እንመልከት።
• ኢሳይያስ አፈወርቂ ንፁሕ ኢትዮጵያዊ ነው። የተንቤኑ አፄ ዮሐንስ የልጅ ልጅ ነው። የኢትዮጵያ ደኅንነት መሥሪያቤት ሠራተኛ የነበረ፣ በደሴና በአዲስ አበባ የተማረ ኢትዮጵያዊ ነው። ጀብሃን እንዲያፈርስ በንጉሡ ሰላይ ተደርጎ በሰርጎ ገብነት ወደ ኤርትራ በረሃ የተላከም የኢትዮጵያ የደኅንነት ሠራተኛም ነበር።
•••
ጀብሃን ካፈራረሰ በኋላ ወደ ሀገሩ ኢትዮጵያ ለመመለስ ፈልጎ ለንጉሡ አቤቶታ ቢያቀርብ የሚሠማው አጥቶ እዚያው በረሃ ለበረሃ ሲንከራተት የቃኘው ሻለቃ አሰልጣኝ የሲአይኤ ሠራተኞች አግኝተውት ሀሳቡን አስቀይረው የዕድሜ ልክ ፕሬዘዳንትና አዲስ ሀገር እንደሚያስረክቡት ቃል ገብተው በዚያው አስቀርተው ኋላም በቃላቸው መሠረት አዲሲቷን ሀገር ኤርትራን ቆርሰው ሰጥተው የዕድሜ ልክ ንጉሥ ሆኖ እንዲቀመጥ አደረጉት።
•••
ኢሳይያስ ኢትዮጵያዊ ስለሆነ የኤርትራውያን መጨቆን፣ መሰደድ ደንታው አይደለም። ለምን አፈር ከደቼ አይግጡም አያገባውም። አይመለከተውም። ኢሳይያስ ጠንካራ ሆኖ አይደለም እነ አሜሪካ ከነ አምባገነንነቱ የሚሸከሙት፣ እሹሩሩ የሚሉት ቃላቸውን ላለማጠፍ ነው። ኤርትራዊ ብሔረተኝነት ጫፍ የሚወጣው በኢሳይያስ ግፍና ጭካኔ መሆኑን ስለሚያውቁ ነው። አውሮጳና አሜሪካን የኤርትራዊ ስደተኛ ሲያጥለቀልቅ እያዩ ዝም የሚሉት ቃል ኪዳን ስላላቸው ነው። ኢሳይያስ አፈወርቂ ማለት ኤርትራን የለ አውቶሚክ ቦንብ ወጣቱን በስደት ጨርሶ ምድሪቱን የሽማግሌዎች መነሃሪያ በማድረግ ከሰው ነፃ በማድረግ ለነጮቹ ለማስረከብ የተቀጠረ ትጉህ ሠራተኛ ነው።
•••
መለስ ዜናዊ በእናቱ ኤርትራዊ፣ በአባቱ አባት ጎጃሜ ነው። የጎጃም አማራ። ለገሰ(መለስ) ዜናዊ አስረስ። በኤርትራ ፍቅር እንዳበደ ሳይድን ሞተ። ኢትዮጵያ ብትበጣጠስ፣ ብትሰደድ ደንታው አልነበረም። እሱ እቴ
•••
አቦይ ስብሃት ነጋ ጭራሽ እህቱ የኤርትራው ኢሳይያስ አፈውርቂ ባለ ሥልጣን ሚስትና የአስመራ ቤተ መንግሥት ሠራተኛ ናት ይባላል። በትውልድ ስፍራ ነውና አሁን ማንነት የሚቆጠረው የአለም ጤና ዳይሬክተሩ ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖምም እንዲሁ የአስመራ ተወላጅ ናቸው። በረከት ስምኦንም የኤርትራ ተወላጅ ስለሆነ ነው ዐማራው ላይ ተሹሞ ዐማራውን አፈር ከደቼ ያበላው። እነ ከበደ ጫኔ ትግሬ ነን ብለው ስለሚያምኑ ነው ዐማራውን እላዩ ላይ ተሹመው እሬቻውን ያበሉት። ጌታቸው ረዳም ወሎዬ ሆኖ ለትግሬ ያደረና በአፉ የሚተዳደር ቅጥረኛ ነው። ትግሬ ተጎዳ አልተጎዳ ለጌታቸው ረዳም ለጌታቸው አሰፋም ጉዳያቸው አይደለም።
•••
ጃዋር መሃመድን እንየው። ሰሞኑን የዘር ሀረጉን በጥልቀት አሳያችኋለሁ። እሱ የሰፋሪ የሀገር አቅኚ የልጅ ልጅ ነው። የሰሜን ሸዋ ሰዎች ናቸው ቤተሰቦቹ። አባቱን ኦነግ ነው በነፍጠኝነቱ የገደለበት። እናቱም አማራ ናት። በዝርዝር እመጣበታለሁ። ነገር ግን ኦሮሞ ነኝ ብሎ በኦሮሞ ህዝብ ስም ኑሮውን ረሃ አድርጎ ተንደላቅቆ ይኖራታል። ኦሮሞ ለምን ድራሽ አባቱ አይጠፋም ለጃዋር ደንታው አይደለም። የእስልምናን ሕግ አያከብርም። ለእስልምና ግን ጠበቃ ነኝ ባይ ነው። ጴንጤ አግብቶ ይኖራል። ከጴንጤዋም ወልዷል። ክርስቲያን ግን በሜንጫ የሚል ጽንፈኛ ነው። ልጁን ኦሮሞ የሚል ስም ሰጥቶታል። ኦሮሞ ጃዋር። ነገር ግን ልጁን በአሜሪካ ሀገር በኦሮሞ።ስም በጎፈንድሚ በሰበሰበው ብር እንጊሊዝኛ ያስተምረዋል። ኦሮሞ ብሎ የወለደውንና ስም የሰጠው ልጁ ኦሮሚኛ አይችልም።
•••
ጃዋር አማርኛ ከኦሮሚያ እንዲጠፋ አበክሮ እየሠራ ነው። ባለፈው ጊዜ ወላጆቹ ሀገር አሩሲ ሄዶ ያለ አንዳች ኦሮምኛ በንፁሕ አማርኛ “ አይዟችሁ ምንም አትስጉ፣ በራሳችሁ ቋንቋ በነፃነት ትኖራላችሁ አትሳቀቁ በማለት ለነፍጠኛ ዘመዶቹ ሊመጣ ካለው መከራ ይድኑበት ዘንድ የቃል መተማመኛ ሰጥቷቸው መመለሱን ዘመዶቹ ይናገራሉ። በኦሮሚያ ፖሊስ ታጅቦ ሄዶ በአማርኛ ዘመዶቹን አጽናንቶ ተመልሷል።
•••
ፀጋዬ አራርሳ የተባለ የሆነ ሬሳ ፊት የዐማራ ሴቶችን ለገርል ፍሬንድነት ጠይቆ እምቢ ስላሉት በንዴት ኦሮሞ ነኝ ያለ። በዚያም እልህ ቅኔ በሚያስዘራው የአማርኛ ቋንቋ አነጋገሩ እንጀራው የሆነውን አማርኛን ሲዋጋ የሚውል የማንነት ቀውስ ውስጥ የወደቀ ምስኪን ነው። ዐቢይ አህመድ፣ አዲሱ አረጋ፣ ሽመልስ አብዲሳ፣ እነ ለማ መገርሳ ሁሉ ንፁሕ ኦሮሞዎች አይደሉም። ነገር ግን ኦሮሞነት እንጀራቸው ሆነ። ለምሳሌ ኦቦ ወርቅነህ ገበየሁ ትግሬ ዘር ነው። ኦቦ አባ ዱላ ገመዳ አቶ ምናሴ ነው ስሙ። ግን ኦሮሞ ነን አሉ። መብታቸውም ነው።
•••
ልክ እንዲሁ ነው እንግዲህ ጃዋርን ያየው እሱንም እያደነቀ ያደገው ጎንደሬው አሉላ ሰሎሞንም የትግራይ ጠበቃ ሆኖ ከች ያለው። ፈረንካ አገኘበት። ኑሮውን ደጎመለት። በየ ሳምንቱ ከአማሪካ ኢትዮጵያ የሚንሸራሸርበት፣ የሚመላለስበት የቢዴናው ዋነኛ አስኳል ሆነለት። ይሄ የጎንደር ዐማራ ልጅ አሉላ ሰለሞን ትግሬ በሌላው ኢትዮጵያዊ ተወደደ፣ ተጠላ ጉዳዩ አይደለም። የእሱ ጉዳይ በትግራይ ስም መነገዱ እንዳይቋረጥበት አጥብቆ መታገሉ ላይ ነው።
•••
አሉላ ሰሎሞንና ጌታቸው ረዳን ትግራዮች ይወዷቸዋል። ሁለቱም ዐማራ ስለሆኑ በአማርኛ ከሌሎች ጋር ይግባቡልናል ብለውም ስለሚያስቡ ይወዷቸዋል። በከፍተኛ ብር እንዳዘዋወሯቸው የእንግሊዝ ኳስ ተጫዋቾችም ነው የሚቆጥሯቸው። በተለይ ህወሓት ጌታቸው ረዳን ማጣት አትፈልግም። ጌታቸው ረዳ፣ ለህወሓትም ለዶክተር ደብረ ጽዮንም አንደበታቸው ነው። ሊቀ ነቢያት ሙሴ አንደበቱ ኮልታፋ ነበር፣ ሙሴ የሚናገረው በአሮን በኩል ነበር። ደብረ ጽዮንም የሚናገረው በጌታቸው ረዳ በኩል ነው።
•••
አሉላ ሰሎሞን የጃዋር ጓደኛ ነው። ኦኤንኤንም መስራች ነው። የአገውና የቅማንት ቡድኖችን አደራጅም ነው። ልክ እንደሱ ዐማራነታቸውን የሚሸጡ ሰዎች ፍለጋ ሲኳትን የሚውል በማንነት ቀውስ የተጠቃ ዲቃላ ነው።
•••
ህወሓትና ኦነግ ሊያፈራርሷት የሚፈልጓትን ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ የያዛትን ገመድ ለይተው ተራ በተራ መዘገቡ።
• ዐማራ
• አማርኛ ቋንቋ
• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
እነዚህ ሦስቱ ተራ በተራ መመታት አለባቸው አሉ። አሉናም ይኸው በመጀመሪያ ዐማራ ላይ ዘመቱ። የአማርኛ ቋንቋም ላይ ዘመቱ። አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ዘመቱ። ያውም እሳትና ሰይፍ ይዘው ነው እየዘመቱ ያለው።
•••
እነ አሉላ ሰሎሞንም የማንነት ቀውሱ ሰለባ ናቸውና ይሄንኑ የእነ ጃዋርን አጀንዳ ይዘው ከች ብለዋል። ትግራይ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መሠረት መሆኗን ዘንግቶ የዐማራ ጥላቻውን ለማራገፍ ሲል ብቻ የጃዋርን አጀንዳ በቅረረቡ በትግራይም እንደሚፈጽመው በደስታ ማውራት ጀምሯል። ጭስ ያለምክንያት አይጨስም። ቀጥሎ እሳት ሲኖር ነው ጭስ ቀድሞ የሚጨሰው። የትግራይ ልጆችም አጆሓ አሉላ እያሉት ነው። በርታ እንደማለት ነው። የትግራይ ኦርቶዶክስ ስትገነጠል የትግራይ ጳጳሳትና የትግራይ ካህናትም ወደ ሀገራቸው ይገባሉ ነው የሚሉት እነ አሉላ ሰሎሞን።
•••
ለኦሮሚያ ቤተ ክህነት መመሠርት እነ ወሃቢያ አባ ጆቢር እንቅልፍ አጥተው ቄስ በላይ መኮንን ሲደግፉ ስታይ የሆነ ነገርማ አለ ትላለህ። ለኦሮሞ ኦርቶዶክሱ የሚከራከሩለት፣ እናውቅልሃለን የሚሉት እነ ፓስተር ቢሊሲማና እነ ኡስታዝ በከሬ መሆናቸውን ስታይ ትደነግጣለህ። ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ናት ይሏታል አሉ የሀገሬ ሰዎች። ኢንዴዢያ ነው።
•••
የትግራይ ኦርቶዶክስ ቀጣይ ነው ብሎናል ለትግራይ ፈርሞ የሚጫወተው ጎንደሬው አሉላ ሰሎሞን። ቀጣዩን ዕድሜ ከሰጠን ማየት ነው እንግዲህ።
•••
ሻሎም !   ሰላም !
ነሐሴ 25/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic