>

የሲኖዶሱ ውግዘት ተጥሷል!!! በላይ መኮንንም መግለጫ እየሰጠ ነው!!! (ዘመድኩን በቀለ)

የሲኖዶሱ ውገዘት ተጥሷል!!!
በላይ መኮንንም መግለጫ እየሰጠ ነው!!! 
           ዘመድኩን በቀለ
★ እኔ ግን በጣም ደስ ብሎኛል። ጳጳሳቱም፣ ኦርቶዶክሳውያኑም ምንም አያመጡም። ዝም ብለህ ቀጥል ብለው እነ ታከለ ኡማ መፍቀዳቸው አስደስቶኛል።
 ፕሮቴስታንትና የወሃቢይ መሪዎቻችን ኦርቶዶክስን አቃጥለውም፣ ከፋፍለውም ካላፈረሷት እንደማይተኙልህ እወቅ።
•••
የኦህዴድኦነግ መንግሥትም ለውጉዛኑ አዳራሽ ፈቅዶ በመስጠት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያለውን ንቀት በግልፅ አሳይቷል።
•••
• ዐቢይ አህመድ እስላምና ኦሮሞና ፕሮቴስታንት።
• ለማ መገርሳ ኦሮሞና ፕሮቴስታንት።
• ሽመልስ አብዲሳ ኦሮሞና ፕሮቴስታንት።
• ታከለ ኡማ ኦሮሞና ፕሮቴስታንት።
• ጃዋር መሃመድ ኦሮሞ እስላምና ፕሮቴስታንት።
• ደመቀ መኮንን እስላምና ፕሮቴስታንት።
• ሙፈሪያት ካሚል ኦሮሞ ስልጤና እስላም። ሌሎቹም እንደዚያው። ከባለሥልጣናት ኦርቶዶክሳውያን ሃባ የሉም። የነበሩትም ሰኔ 15 ተረሽነዋል።
•••
ታከለ ኡማም ፓትሪያርኩን አሞኝቷቸዋል። የሰላም ሚንስትሯም አባ ማትያስን ሸውዳቸዋለች። አሁን ነገሩ እየጠራና ግልፅ እየሆነ መጥቷል። ይኸው ነው ወዳጄ። ባለቤቷን የተማመነች በግ ላቷን ከጋጣው ውጭ ታሳድራለች ነው ነገሩ። እንግዲህ በቀጣይ የሚሆነውን አብረን መጠበቅ ነው።
•••
የቤተ ክህነቱ መግለጫ ላይ ራዲዮ ፋናና ኢቲቪ እንዳይገኙ የተደረገው ለምን ይመስልሃል? አሁን የገጠመን ነገር ከዛሬ 500 ዓመት በፊት ከገጠመን ፈተና የከፋና የባሰ ነው አለ አሳምነው ጽጌ። ነፍስህን ይማረው።
★ በቀጣይ ዋቄፈታና እነ በላይ ደብረ ሊባኖስ የእኔ ነው የእኔ ነው ብለው በመጣላት ወደ ፍርድ ቤት ያመሩልሃል። ዳኛው ኦቦ መገርሳና ሼክ አብዱረሃማን ነው። ያው ለዋቄፈታዎቹ ይፈርድላቸውና ደብረ ሊባኖስን በቁሙ  ያወርስልሃል። ቱ ምን አለ ዘመዴ በለኝ። ጠብቅ።
• የህንድ ኦርቶዶክስ ፈተና በኢትዮጵያም በቅርቡ ይደገማል። የሲኖዶሱ አባላት ፈሪዎችና የካድሬዎች  ስብስብ ስለሆነ በዚያ በኩል እንዲያው ድንገት ተአምር ካልተፈጠረ በቀር ብዙም እምነትና የምጠብቀው ነገር የለኝም።
•••
የፓትሪያርኩ አማካሪ የሊቀ ዘማውያን ትዝታው ሳሙኤል ጓደኛ አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ከአክሱም ሆነው ቄስ በላይ ያመጣው ሃሳብ ትክክል ነው ሲሉ ስታይ ይሄ እኩይ ተግባር የማን ሥራ እንደሆነ ወለል ብሎ ይታይሃል። ሲኖዶስ ተንቋል። ቤተ ክርስቲያን ተደፍራለች፣ ተዋርዳለች።
•••
ጀግና ጀግና የተባሉት ጳጳሳት በራሱ ድራሻቸው ጠፈፍቷል። ካሴትና መጽሐፍ ቸርቻሪው ሰባኪ ነኝ ባዩ ሁላ እናቱ ቀሚስ ስር ተወሽቋል። እናም እነ በላይ በግልጽ ከቤተ ክርስቲያን አፈንግጠው መውጣታቸውን በግልጽ አውጀዋል።
•••
ሻሎም !   ሰላም ! 
ነሐሴ 26/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።
Filed in: Amharic