>

«ነጭ» ዘረኛ ማነው? ኅሊና ደሳለኝ  ወይስ ግርማ ጉተማ? ( አቻምየለህ ታምሩ)

«ነጭ» ዘረኛ ማነው? ኅሊና ደሳለኝ  ወይስ ግርማ ጉተማ?  
አቻምየለህ ታምሩ
* የወለጋን ህዝብ “ሻንቅላ የሚሽነሪ ልጆች” ብሎ የተሳደበው ዶ/ር ሀንጋሳ አገር ቤት ገብቷል!!
ግርማ ጉተማና በቀለ ገርባ የተባሉ ዐይናቸውን በጨው ያጠቡ ሁለት ፈላስፎች በጃዋር ቴሌቭዥን ፊጥ ብለው  የሞራና የሰብአዊ ተግባር መምህሮች ሆነው ለመቅረብ ሲሞክሩ ስትመለከት በጎሰኞች መንደር ነውር የሚባል ነገር እንደጠፋ ትረዳለህ። ከሁለት «ተንታኞች»  አንዱ (ግርማ ጉተማ) በኅሊና ደሳለኝ ግጥም  ውስጥ «መንጋ» በሚል የቀረበውን  ጥቅል መጠሪያ  «ነጭ ዘረኛነት ነው» ብሎ በሰጠው ብያኔ ተስማምተዋል፤ ልጅቷም በሕግ መጠየቅ አለባት ብለዋል። ይገርማል!
ዐይኑን በጨው አጥቦ የሞራና የሰብአዊ ተግባር መምህር ለመሆን የሚዳዳው ግርማ ጉተማ ከሁለት ዓመታት በፊት ከሲዳማ ውጭ ያሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ነገዶቹን በሙሉ በማንነታቸውና ፖለቲካ አመለካከታቸው ከሱ ስለሚለዩ ብቻ  እዚህ ደግሜ ልጠቀመው በሚከብደኝ  የዘረኛነት ስድብ ሲያበሳብስ  የነበረ ፍጡር ነው። ኅሊና በዘረኛነት ስድብ የምትጠቅየቅ ከሆኑ ከኅሊና በፊት  እጁ በመጫኛ የኋሊት ታስሮ ሕግ ፊት መቅረብ ያለበት ከሁለት ዓመታት በፊት  53 የደቡብ ኢትዮጵያ ነገዶን በማንነታቸውና በፖለቲካ አመለካከታቸው ከኔ ይለያሉ ብሎ ስላሰበ ብቻ  በዘረኛነት ስድቡ ያበሳበሰው ግርማ ጉተማ  ራሱ ነው።
ባሳለፍነው ዓመት መጋቢት ወር  እንኳ  አንድ የሽሬ ልጅ ደብረ ማርቆስ  ዩኒቨርሲቲ ማንነታቸው በማይታወቁ ሰዎች ሲገደል «በደብረማርቆስ  በትግራይ ተወላጆች ላይ በተካሄደ የበቀል እርምጃ አንድ የሽሬ ልጅ የመንጋ ፍርድ ተፈጸመበት»  ብሎ በመተንተንና   አማራን «መንጋ» አድርጎ በማቅረብ  ከትግሬ ጋር  ለማጋጨት በመሞከር ግርማ ጉተማን የቀደመው ማንም አልነበረም። ይህ ግርማ ጉተማ ነው እንግዲህ ኅሊና ደሳለኝ  በግጥሟ ውስጥ  «መንጋ»  የሚል ጥቅል ቃል  ተጠቀመች ብሎ በነጭ ዘረኛነት የሚከሳት!
ኅሊና ደሳለኝ  የተጠቀመችውን «መንጋ» የሚል  ጥቅል ቃል ከመጠቀሟ  ከስድስት ወር በፊት የደብረ ማርቆስን ማኅበረሰብ  ለማውገዝ  «መንጋ» ሲል ቃሉን የተጠቀመው ዛሬ ላይ መንጋ ተባለን እያለ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚለው ግርማ ጉተማ ኅሊና ደሳለኝን ሊያወግዝ የሚችልበት የሞራ ልዕልና የለውም!
ለኔ ነጭ ዘረኛነት የሚሆነው ኅሊና ደሳለኝ በጥቅል የተጠቀመችው «መንጋ» የሚለው አገላለጽ ሳይሆን  ከስድስት ወር በፊት የደብረ ማርቆስን ማኅበረሰብ «መንጋ» ብሎ የተሳደበውንና ከሁለት ዓመታት በፊት 53ቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ነገዶች በሙሉ በሚያሳንስ የዘረኛነት ስድብ ያበሳበሰውን ግርማ ጉተማን ትቶ ትናንትና «መንጋ» የሚል ጥቅል  አገላለጽ የተጠቀመችውን ኅሊና  ደሳለኝን ለማውገዝ መነሳትና በሕግ እንድትጠየቀም  ማሰቡ ነው።
የኦሮሞ ብሔርተኞች ራሳቸው ነጭ ዘረኞችና ግብዞች ናቸው እንጂ ኅሊና ቢኖራቸው ኖሮ ኅሊና ደሳለኝ በጥቅል  ስለተጠቀመችው  «መንጋ» የሚል ጥቅል ቃል ተነካን ብለው ለማውገዝና  በሕግ ትጠየቅ  ብለው ከመነሳታቸው በፊት  ከስድስት ወር በፊት ይህን ቃል ተጠቅሞ  የደብረ ማርቆስን ማኅበረሰብ «መንጋ» ብሎ የተሳደበውንና ከሁለት ዓመታት በፊት 53ቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ነገዶች በሙሉ  በነገዳቸው ምክንያት በሚያሳንስ የዘረኛነት ስድብ ያበሳበሰውን የራሳቸውን ጉድ  ግርማ ጉተማን  በነጭ ዘረኛነቱ ማውገዝና  በሕግ እንዲጠየቅ ማድረግ ነበረባቸው።
 
ከዛው ሳንወጣ – ሌላው ተሳዳቢ ገብቷል !!
.
የወለጋ ህዝብን ቃል በቃል “ሻንቅላ የሚሽነሪ ልጆች”ቡሎ የተሳደበው ከቋንቋ ይልቅ ወደ ሀይማኖተኛ ቡሔርተኝነት የሚጠጋው ዶ/ር Hangaasa Ibraahim አዲስ አበባ ገብቶል። ኦዲፒም ታዬ ደንደኣን ልካ ሞቅ አድርጋ ተቀብለዋለች። ዶ/ር ሀንጋሴ በአንዳንድ የኦሮሞ ቡሔርተኞች እንደ ከፉፉይ እና በጥባጭ የሚታይ ሰው ነው። ከዚህ በፊት ዶ/ር ሀንጋሴ ታከለ ኡማ ስልጣን እንደያዘ በሶስት ወር ውስጥ የአዲስ አበባን የቀድሞ የሰፈር ስሞች አልመለስክም ቡሎ በOMN በቀጥታ ወይይት ላይ “ሚሺነሪዎች (ጴንጤዎች ) የኦሮሙማ ወኔውን የሰለቡት ገረድ ነው ” ቡሎ ሰድቦት ነበር።

https://www.facebook.com/1248776283/posts/10220044742569388/

Filed in: Amharic