>
5:18 pm - Sunday June 15, 5980

ባሕር ዳር ላይ በተከናወነው ኦርቶዶክሳዊ ሰላማዊ ሰልፍ ብጹዕ አቡነ አብረሃም በባሕር ዳር መስቀል አደባባይ ለተሰበሰው ምዕናን ያስላለፉት መልዕክት!

ብጹእ ወቅዱስ አቡነ አብርሃም ለጠ/ሚ ዐቢይ መሀመድ መልዕክት ልከዋል !
ዘካርያስ ኪሮስ ከባሕርዳር
ባሕር ዳር ላይ በተከናወነው ኦርቶዶክሳዊ ሰላማዊ ሰልፍ ብጹዕ አቡነ አብረሃም በባሕር ዳር መስቀል አደባባይ ለተሰበሰው ምዕናን ያስላለፉት መልዕክት!
                ማንም ቤተ ክርስቲያንን በጥፋተኝነት ሊወቅሳት አይችልም ። በየትኛውም ዓለም ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ናት ። ክርስቲያኑ ንጉሥ ሙስሊም ወገኖቻችንን ተቀብሎ እንዳስተናገደ የሙስሊም መጻሕፍት ጭምር የመሰከሩት ነው ። ለዚህም ነው ተከባብረን እየኖርን ያለነው ። አንዳንድ አላዋቂዎች “ቤተ ክርስቲያን ስለ አገር ምን አገባት!” ሲሉ ይደመጣሉ ። ይኸ አላዋቂነት ነው ። ቤተ ክርስቲያን ስአገር ይገዳታል! ። ቤተ ክርስቲያን ስለ ኢትዮጵያ ትጮኃለች! ። ቤተ ክርስቲያን “እኔን ብቻ ይድላኝ” አትልም ።
                        ቤተ ክርስቲያን አግላይ አይደለችም ። ቅድስተሰ ቤተ ክርስቲያን ማንኛውንም ሰው በግድ እና በዱላ እንዲሁም በሰይፍ እና በዛቻ በማስገደድ ወደራሷ በረት አታመጣም! ። እርስት ጉልት እየሰጠች በመደለል ፣ በጋብቻ አስገድዳ ክርስቲያን አታደርግም ። “ክርስቲያን ልሁን” ላለ ማንኛውንም ሰው በፍቅር ስባ ታጠምቃለች ። ይኸንን ያላወቁ ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ላይ ክፉ ስራ እየሰሩ ነው ። እሷን እና ምዕመናኖቿን ለማጥፋትና ለመግደል ቢያድቡም ሞት ግን ክርስቲያኖችን አስደንግጦ አያውቅም! ። የማንንም መብት አለመንካት የዘወትር ተግባራችን ነው ። ኢትዮጵያ የጋራ አገራችን ናት! ። የእኔ እገሌ ብቻ የምትባል አይደለችም ።
                   “ኦርቶዶክስን የነፍጠኞች ሃይማኖት ናት!” የሚሉ አሉ ። ይኸ ፈጽሞ የተሳሳተ አነጋገር ነው ። ኦርቶዶክስ የአማራው የኦሮሞው የአፋሩ የጋምበቤላው የቤንሻንጉሉ የከንባታው … የሁሉም ናት ። ነገር ግን በዘመናች በኃይል የሚመኩ! ፣ በነፍጣቸው የሚመኩ ካሉ እራሳቸውን ወደ እግዚአብሔር ዝቅ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ። ቤተ ክርስቲያን ላይ የመከራ ጭንቅን ማድረጋችሁን አቁሙ! ። ክርስትናችን አነገታችንን እንድንደፋ አድርጋን እንጂ ለወኔ ለወኔማ ኦርቶዶክሳዊያን ያውቁበታል ።
                  የሚወዛወዝ እጅ ስለሌለን አይደለም እጃችንን በአጠቁን ሰዎች ላይ የማናነሳው ። አንድ ሰው ከጮኸ ሰላማዊ ነው ። “ኦርቶዶክስ የአማራ ስለሆነች ነው እዚያ አካባቢ የሚጮኸው” የሚሉ ደካማ ሰዎችንም እሰማለሁ ። ተዋህዶ የሁሉም ናት! ። እንኳን የሚያምነው ቀርቶ የማያምንባትም ሙስሊምም ሆነ ፕሮቴስታንት ስለቤተክርስቲያን መከራና ጭንቅ ሊገደው ይገባል ።
             ለጠቅላይ ጠቅላይ መኒስቴር ዶ/ር ዐቢይ የማስተላልፈው መልዕክት አለኝ ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ መጀመሪያ ሲነሱ ስለተዋህዶ በየትኛውም ቦታ በሄዱ ቁጥር ሲመሰክሩላት ታይቷል ። እዚያና እዚኸ የነበረውንም አሰታረቀዋል ። የተወሰዱባትን ሕንጻዎችም አስመልሰዋል ። በዚኸ በኩሉ አመሰግጋቸዋለሁ ። ነገር ግን አሁን ላይ ያ! ትጋቸው ተቋርጧል ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ እገዛ እስከመጨረሻው መዝለቅ አለበት ። ለምን ተቋረጠ!? ። አሁንም አሁንም ኢትዮጵያን እንደጠሩ በዚያ እንዲቀጥሉ እንሻለን ። ካጠገባቸው ሆነው የሚጎረብጧቸው ሰዎችም ካሉ ይንገሩንና እስከ እቅታ ድረስ አብረን እንታገላቸዋለን ።
                    ወጣቶች አደራ የምላችሁ ማንኛውም ነገር ለመስራት ከአባቶቻችን በተዋረድ በመታዘዝ ይሁን ። እነሱን በተዋረድ እንስማ ። ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያዘንን አድርጉ የሚለንን እንከተል ። አንዳንድ ጊዜ ሞቅ የምንል አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የምንበርድ መሆን የለብንም! ። ወታደር ትጥቁን አይፈታም ። ክርስቲያኖችም የጸሎትና የትጋት ትጥቃችሁን አትፍቱ ። አብረን እንሰራለን ። በርቱ ። አብረን እንሮጣለን ። አብረን ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልዕልና እስከ መስዋዕትነትም ድረስ ቢሆን እንሰራለን ።
                       እንደ ባሕር ዳር ከተማማ የደረሰብን ምንም ነገር የለም ። ቤተ ክርስቲያን ግን አንዲት በመሆኗ እዚያ የተጠቃችው የቤተ ክርስቲያን ጥቃት የእኛም ጥቃት ነው ። ወደፊትም ዛሬም ስለቤተ ክርስቲያናችን እንዲሁም ስለኢትዮጵያ እንጮኃለን ። ጉባኤም እየሰራን አብረን ግንዛ እንጨብጣለን ። በሰላማዊ መንገድ መብታችንን እንጠይቃለን ። በመንፈሳዊነታችሁ በርቱ ። እንደ ዛሬው ሁሉ መስቀል ደርሷልና በደነሸብ አድርገን እንድናከበር ይሁን ።
Filed in: Amharic