>

ዛሬም ኤርሚ ጋ ሄጄ ነበር!!! (የማታብርሀን ግርማ)

ዛሬም ኤርሚ ጋ ሄጄ ነበር!!!
የማታብርሀን ግርማ
” ለዶክተር አቢይ አህመድ ምን መደረግ እንዳለበት የሚያመለክት 35 page paper ፅፌ ነበር፤ አንድ ቀን ሚድያዎች የራሳቸው ግኝት አድርገው ሲያቀርቡት ሰምቼ ሽምቅቅ አልኩ ….”
“እንደተፈታህ ወዴት ነው የምትሄደው?” ብዬ ጠየቅኩት! ምን አለኝ መሰላችሁ?
“now a days ኢትዮጵያ ውስጥ ከ 10 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ስራ አጥ ናቸው። በምችለው መጠን ለራሴ መስራት ትቼ ወጣቱን ወደ ሲስተም የማስገባት ስራ መስራት ነው አላማዬ!
እስኪ ጎግል አድርጊ Ethiopian population ላይ የተሰራ research ምን እንደሚል እዪውና ኔክስት ስትመጪ ትነግሪኛለሽ። የዛሬ 40 አመት የኢትዮጵያ ህዝብ ወደ 250 ሚልየን አካባቢ ይደርሳል you see? በአንድ አመት 2 ሚልየን እንጨምራለን ማለት ነው።
ታድያ ይሄኛው ትውልድ ቦታ ሳይዝ እራሱን ማቆምያ ሳይኖረው ሌላ ትውልድ አምጥቶ ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት ቀላል ነው! ይሄን ትውልድ ቦታ ማስያዝ የማንም ሀላፊነት አይደለም የኛው ሀላፊነት ነው።
የማታዬ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ኮማ ውስጥ ነው ያለው ብዬ ለዶክተርር አቢይ አህመድ ምን መደረግ እንዳለበት የሚያመለክት 35 page paper ፅፌ ልኬለት ነበር መልስ አላገኘሁም እንጂ…
ስራ በዝቶበት ሳያየው ቀርቶ ይሆናል ወይ አልደረሰው ይሆናል ብዬ እሱን በቅርብ በሚያውቁት 5 ሰዎች ደግሜ ላኩኝ አሁንም መልስ የለም አንድ ቀን የራሴኑ ጥናት ሚድያዎች የነሱ አድርገው ሲያቀርቡት አይቼ ኩምሽሽ አልኩልሽ” አለኝ ፈገግ
እያለ ኧረ የዚህ ሰው ጥንካሬ የጉድ ነው
“እኔ ግን አንተን ብሆን ስፈታ ጌታን የመጀመሪያ ስራዬ የሚሆነው ይቺን ጣጠኛ ሀገር ለቅቄ መውጣት ነበር” አልኩት
“ያምሻል እንዴ የማታ ለማን ለምን ብዬ ነው ሀገሬን ጥዬ የምወጣው? ያኔ ስመለስ እኮ ይሄ እንደሚፈጠር በደንብ ግምቱ ነበረኝ። እኔኮ የታሰርኩት ገና 9 ወር ነው! ምንም አልደከመኝም!
ምንም አልሰለቸኝም!!!
ታምኛለሽ? እዚህ እስኪጣራ ተብሎ 5 አመት የታሰረ ሰው አለ። ፊዚካሊም ሜንታሊም አቢዩዝ ተደርጎ ህክምና እንኳን ተከልክሎ እኛው ነን እንደነገሩ ትሪት የምናደርገው።
እኔ በእርግጥ ምንም የደረሰብኝን ነገር የለም!! እኔ ሀገር ለቅቄ ከወጣው እዚ ማረሚያ ላሉ ሰዎች ማን ድምፁን ሊያሰማ ነው!?” አለኝ እውነቱን ነው እኮ
“እንደውም ከበፊቱ በተሻለ ጠንክሬ ነው የምመጣው ሰብአዊ መብት አካባቢም ታይኛለሽ”
“ለውጡን እንዴት አየኸው ኤርሚ?” አልኩት
“ለውጡ መጀመርያ ፍቅር አስይዞኝ ነበር በኋላ ጥሎኝ ጠፋ እንጂ! ለውጡን ደግፈውም ለውጡን ተቃውመውም ሚድያ ላይ የሚቀርቡትን ሰዎች አያለሁ ብዙዎቹ ችግርን እንጂ መፍትሄን ሲጠቁሙ አላየሁም አንዳንዶቹ እንደውም ያስቁኛል…………..
ኢኮኖሚው ኢግኖር ተደርጎ ፖለቲካው ጦፏል ለዚህ ህዝብ ግን በዚህ ሰአት አሰፈላጊው ኢኮኖሚውን የተረጋጋ ማድረግ ነበር እንግዲህ …….. እኔ ፖለቲካ ብዙም አይመቸኝም በተለይ የአፍሪካ “
ከዚህ ሰው ጋ ማውራት ምንም አይሰለችም ለደቂቃ ብሄሩን አላነሳም “ሀገር፣ ሀገሬ፣ ሀገሪቱ ፣ ሀገራችን” ነበር የሚለው ይሄ ሰው ዛሬም ጥያቄው ብሄር ፖለቲካ ክልል ጎጥ ቀበሌ ጫካ አይደለም ሀገር ነው። ሀገሬን እወዳለሁ ኢትዮጵያዊ ብቻ ነኝ የምትል ለዚህ ሰው ድምፅህን አሰማ። ፍትህ!!
Filed in: Amharic