>

የጨለማው  መንገድ ጉዞ !!!!  (አቤል ዘመን)

የጨለማው  መንገድ ጉዞ !!!!
 አቤል ዘመን
* እነ ብሉምበርግ እና አጃንስ ፍራንስ ደግሞ “የበራው መብራት ወደ መጥፋት እየሮጠ ነው” ሲሉ ይሰማሉ።
የዶ/ር አብይን አመራር ከመሰረቱ መነሻ ቃሉን ይዘው ሲያንቆለጴጵሱት የነበሩት የሀያላኑ አገራት መንግስታት እና ሚዲያወች ዛሬ ላይ ፊታቸውን ያዞሩ ይመስላሉ።
ሁኔታወችን አስቀድመው በመተንበይ የሚታወቁት የሚዲያ ሞግላን ስለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመጣጥ የሰጡት አስተያየት እና ትንበያ ኢትዮጵያን ጠንቅቆ ከሚያውቃት በላይ ጠለቅ ብለው ያዩትን ያወጡበት ይመስላሉ።
የሂደቱን ጅማሬ ከሚኒሊክ ቤተመንግስት ንግግራቸው ጀምሮ ወደ መንደመሩ ምዕራፍ ያመጡበትን የጉዞ ሰነድ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ አንደበት ይመዛሉ።
ከዛም በኢትዮጵያዊነት ህልውና የአንድነትን ስንቅ ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮያ ያሉትን እንደ ዋና ሰበዝ ይመዛሉ ከዛም ያቀባበሉበትን ሰበዝ ከመዘዙት የሚኒሊክ ቤተመንግስት ንግግራቸው ያመጥቁትና ወደ ታላቁ ሰው ምድር ደቡብ አፍሪካ አባት ከኔልሰን ማንዴላ ጋር ያመሳስላሉ ።
ሆኖም የመነሻቸውን ሰበዝ በመበጠስ የዶ/ር አብይን የለውጥ አብዮት ያልበሰለ ሲሉ ይቀብሩታል።
ነገሩን በሚገርም ሂደት ያጠኑት እውቁ አሜሪካዊ ፖለቲከኛ ጆርጅ ” የሰውየው አነሳሳዊ ንግግር ከማርቲን ሉተር ኪንግ ጋር ይመሳሰላል የአፊሪካ ሁለተኛዋ ባለትልቅ ህዝብ አገር መሪ እንደ መግነጢስ የህዝቡን የተስፋ መንፈስ በቅዱስ ቃላቸው ሞልተውት ነበር በዚህም ኢትዮጵያውያን ሁሉም በሳቸው አነሳሳ እጅጉን ትልቅ ተስፋን ጥለው ነበር ሆኖም የተለኮሰውን ችቦ በይበልጥ ለማብራት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የንግግር ዱካ አሻራ ከወራት አልዘለለም ” ሲሉ ይጠቅሱና ሂደታቸው ከአገር መሪነት አልፈው ወደ አፍሪካ ወካይ መሪነት ሰው ከመሸጋጋር ይልቅ አስፍቶ የሚሰማው ጆሮዋቸው ወደ መንደር ዝቅ አለ ሲሉ የሰላ ትችት ይሰጣሉ።
እነ ብሉምበርግ እና አጃንስ ፍራንስ ደግሞ የበራው መብራት ወደ መጥፋት እየሮጠ ነውም ሲሉ ይሰማሉ።
ዶ/ር አብይን ጠንከር ባለ ትችት ሰሞኑን የተቹዋቸው ብዙ ሲሆኑ በዚህ እርምጃ ኢትዮጵያ ወደ ከፋ አደጋ ለመሄድ እየተንደረደረች ነው ይህን የአንድ አገር መሪ መገንዘብ ነበረበት በሚል የአብይን የብቃት ማነስ ችግር በቁና እየሰፈሩ ይለካሉ።
በተለይ ደግሞ እሳቸው ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በኢትዮጵያ በአማካይ በቀን ከአስር ሰወች በላይ በግፍ እንዳለቁም ነው ያወሱት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይ በአማራ በትግራይ እና ከጌዲዮ ህዝብ ላይ ያሳዩትን የአመራር ጥበብ ማነስ ” እንደ አንድ አገር ህዝብ መሪነት የማይሰማቸው የሞት ዜና ለምን ብለው ከመቆጨት ይልቅ ከየት ነው ብለው በቸላ እስከ ማለፍ የደረሱ” በማለት የለወጡን ሂደት ከተስፋ ወደ ልምላሜ ሳይወስዱ እየመሸ እንደሆነ ገልፀዋል።
በአገሪቱ በተስፋ መቁረጥ በእንግልት እና በመከራ በተወለዱበት የአገራቸው ስፍራ ሸሽተው ወደ ትግራይ ብዙወች ሲሰደዱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከንግግር ባለፈ ትልቅ እርምጃን መውሰድ ይችሉ ነበር በዚህም የትግራይ ህዝብ በሳቸው ምክንያት ከኢትዮጵያዊነት እየወጣ ወደመገለል ስሜት ተገፍቶዋል ካሉ በሁዋላ
” ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአንድ አገር ህዝብ መሪ ቢሆኑ እና እንደሰለጠነው አለም አገራት ቢያስቡ ኖሮ ቀድሞ ወቶ የደገፋቸውን የአማራን ህዝብ ከመቸውም ጊዜ በላይ ለግፍ ባልደረጉት ነበር ።
ዛሬ በቁጥር አንድ እስር ቤቶች እየሞሉ ያሉት በአማራ ህዝብ ነው በሳቸው የስልጣን ዘመን ገና በጅምሩ ከስድስት መቶ በላይ ያላነሱ የአማራ ህዝብ በግፍ ተገድሉዋል ” ሲሉ የጊዜ ሰለዳን ስተው የተነተኑበት እይታቸው የት እንደደረሰ ስለ ኢትዮጵያ ያዩትን እውነት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጅምሩን በማድነቅ ድንበር ተሻግረው አለምን በብልሀት አመራር እዛ ከሚርመጠመጡት የአፍሪካ መሪወች አንዱ ወደመሆን እየሄደ እንዳለም ጣታቸውን ቀስረው ተንትነዋል።
የሀያሉዋ አሜሪካ የአፍሪካ ጉዳይ ተወካዮች ሰሞኑን ያደረጉትን ውይይት ብዙ ኢትዮጵያውያን ተቀባብለውት ነበር በዚህም የአገራቸው መንግስት ” የኢትዮጵያ የአመራር ለውጥ ወደ ባሰ ያነሰ ዘረኝነት ውስጥ እየገባ እንዳሉ አስረድተዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለጉዳዩ ያላቸው አቁዋም ከንንግግራቸው ወርዶ መሬት ላይ ያልታየ ይባሱኑ ነገሮች አቅጣጫቸውን እንደቀየሩ ገልፀዋል።
በጌዲዮ ህዝብ መከራ ሲደርስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚዲያን በመዝጋት ያ ሁሉ ህዝብ ለስቃይ ሲዳረግ መትሄን ለማምጣት ከመጣር ይልቅ ሁኔታውን ለማስተባበል ያደረጉትን ጉዞም ደካማ ከማለት አልፈው የአንድ አገር መሪ ሁሉንም በእኩል የሚያይ ሁሉም ዜጎች እኩል የሚመለከት ነው ሆኖም ዶ/ር አብይ ዜጎችን እንኩዋን በመለየት ከአንድ አገር መሪነት ይልቅ ወደ አንድ አቅጣጫ ብቻ የሚየዩ ሆነዋል ካለ በሁዋላ በአገሪቱ በየስፍራው እየተደረጉ ያሉትን ግፎች እያወቁ ወደመፍትሄ መስጠት ከመሄድ ይልቅ ቸልተኛ ሆነዋልም ብለዋል።
በዚህ ከቀጠለች ኢትዮጵያ በብዙ ችግር ውስጥ ለማለፍ ትገደዳለች የአመራር ጥበብ ክህሎትን ወደ ወንድ መንደር ቀይረው እኩል አገልጋይነትን ካላሳዩ በዜጎች መሀል የሰፋ ልዩነት ድህነት እና ተስፋ መቁረጥ ይንሰራፋል ይህ ደግሞ የአንስ አገር ህልውና ዋልታና ማገር ተናደ ማለት ነው ኢትዮጵያ የነበራት ብሩህ ተስፋ አርቆ ካለማሰብ የተነሳ አንዳይጨልም ስጋት አለ ሲሉም ይተነትናሉ።
ሰሞኑን በአማራ ክልል ስለተደረገው ጉዳይ ዛሬ በሰፊው የዘገቡት የሀያላኑ አገራት ሚዲያወች እንደ አንድ አገር መሪነት ስለ ጉዳዩ ያሳዩት ቸልተኝነት ከዚህ ቀደም ታይቶ አያውቅም እስከማለት በደረሱ ቃላት ነው ።
ብቻ ዞር ዞር ብላችሁ የሀያላኑን ሚዲያወች ባለፉት ስምንት ቀናት የፃፉትን እና በዜናቸው የዘገቡትን ስታዩ ከእንደ እስከዛሬው ወሬያቸው ይልቅ ስለ ኢትዮጵያ መሬት ላይ ያለ ተጨባጭ መረጃን መያዛቸውን ትረዳላችሁ።
አገሪቱ ሴራን ሲዘግቡ የሚውሉ ቴሌቭዥኖችን ጋዜጦችን ተናጋሪወችን ታቅፋለች ግማሹን ያለምንም ጥፋት ስታስር ሌላውን ደግሞ በነጻነት አገር የማፈራረስ ስራ እንዲሰራ ፈቅዳ ሁዋላቁር የአፍሪካውያንን አመራር ይዛ በመጉዋዝ ላይ ነች ያሉም ኢትዮጵያውያን ብቅ ብለዋል።
እውነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአንድ መቶ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ላላት አገር ከጨላማው ምድር አፍሪካ አስተሳሰብ ተላቀው አስቀድመው ነገሮች ከመጨለማቸው በፊት ኢትዮጵያውያንም የሀያላኑ አገራት የፖለቲካ ተንታኞች የሰጡትን ሀሳብ በማጤን በሳል አመራርን በመከተል ታሪክ ይሰሩ ይሆን ? ነው ወይስ ዛሬ ላይ ይበልጥ የመድሎ አገርነትን ወደመፍጠር እና ህዝብን በመለያየት የከሰረ የማያሻግር ጉዞን ይመርጡ ይሆን?
እውነት አንድ ኢትዮያዊ ያለጥፋቱ ሲሞት ህዝብ በሴራ ሲሰቃይ አንደመሪ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው ብለው እኩል ለሁሉም የሚቆሙ መሪ ለውጥን በወሬ ሳይሆን በተግባር የሚዘውሩ ታላቁ ሰው ይሆኑ ይሆን?
ብቻ ሌላውን እንተወው ሆኖም በሳል መሪ ከመቀመጫ ዙፋኑ ወርዶ የህዝብን ሮሮ ያላየውን ጉድለት በማረም የተራመደበት መንገድ ስህተት ከሆነ በመቀየር የሚመራቸውን ህዝቦች ስቃይ ህዝቡን በማስተባበር በመቀየር እና አንድም የአገሩ ሰው ዜጋ መድሎ መገፋት እና መጨቆን እንዳይደርስበት እኩል እይታን በመያዝ የሀያ አንደኛው ክፍለዘመን አስተሳሰብን በምክኒያታዊነት በመለካት ጉዞን በብቃት እይታ መትለም ወሳኝ ነው ።
ሰላም ያገናኘን ኢትዮጵያ !
Filed in: Amharic