>

"..."ሰበሩን ሰበርናቸው....!!!!"  (ብርሀኑ ተክለአረጋይ)

“…”ሰበሩን ሰበርናቸው….!!!!”
 
ብርሀኑ ተክለአረጋይ
* ወዳጄ የክብደት አንሺና የወጌሻ ስነ ልቦና ይዘህ ሃገር እመራለሁ ካልክ የአደባባይ ንግግርህ ሁሉ “ሰበሩን ሰበርናቸው” ነው!!! 
ከሳምንታት በፊት አቶ ሽመልስ በፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ኢሬቻን በተመለከተ ከወጣቶች ጋር ስብሰባ ባደረጉበት ወቅት እሳቸውም ሆነ አቶ አዲሱ አረጋ ለወጣቶቹ ያስተላለፉት ትእዛዝ በስብሰባው ከተሳተፈ ወጣት ተነገረኝ። የአቶ አዲሱ ይቆየንና አቶ ሽመልስ ለወጣቶቹ፦
 “ኢሬቻን የምናከብረው ሌሎችን በሚያስፈራና በሚያስደነግጥ ሁኔታ አዲስ አበባ የኦሮሚያ መሆኗንም በሚያስመሰክር ሁኔታ ነው። ምንም የሚያስደነግጣችሁ ነገር የለም ለዚህ ተዘጋጁ። አንገት ያስደፉን አንገት ይደፋሉ የተዘጋ ኮንዶሚኒየም ካገኛችሁ ሰብራችሁ ግቡ” ነበር ያሉት። ይህንኑ መረጃ በአባይ ሚዲያ “አውድማ” ፕሮግራም ላይ በገለፅኩት ወቅት ለሽመልስ እንቀርባለን ያሉ ሰዎች እየደወሉ ‘እንዴት እንዲህ ትላለህ?’ ባሉኝ ጊዜ ‘ሰውየውኮ ይህን መናገራቸውን በቦታው ከነበረ ሰው አረጋግጬ ነው የተናገርኩት’ ብልም የሽሜ ቀራቢዎች “እሱ እንዲህ ቢልም አንተ ግን እንዲህ ማለት አልነበረብህም” ነበር ያሉኝ። “ጌቶች ቢፈሱም አገሱ ነው የሚባል” መሆኑ ነው።
-አቶ ሽመልስ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ተገኝተው “የኦሮሚያ ቤተክህነት የሚባል ነገር አይታሰብም ለእስካሁኑም ቤተክርስቲያንን ይቅርታ እንጠይቃለን” ካሉ በኋላ መልሰው “የለም እንዲህ አላልኩም ነገሩ ምክረ ሀሳብ ነው ያቀረብኩት” ባሉ ጊዜ ይህንኑ እውነት በአውድማ ስንገልፀው የእሳቸው ወዳጅ ነኝ ባይ ደውሎ “ሽመልስ እንዲህ አለ ብሎ የነገረህ ሊቀ ጳጳስ ማነው?ሽሜ ይህን እንዳላለ ነግሮኛል” አለኝ እኔም የነገረኝን ሰው ማንነት እንደማልገልፅለትና ነገሩ ግን እውነት መሆኑን በትህትና መለስኩ። ሰውየው መልሶ “ጳጳሳቱን አትመን እነሱ ሰውየውን ስለማይወዱ ነው። እኔ ከእሱ አረጋግጫለሁ” አለኝ።
ከዚህ በላይ መታገሱ ጥሩ መስሎ ስላልታየኝ “የሱ ጓደኛ መሆንህን ብፁአን አባቶችን በመዝለፍ እያሳየኸኝ ነው?አንተ የኦህዴዱን ሽመልስን ለማመን የደፈርክ እኔ እንዴት የመንፈስ ቅዱስ አባቶቼን እንዳላምን ትመክረኛለህ? ይህ የአድርባይነት ጥግ ነው።”ብዬ ነገሩን ማጦዝ ለማንም እንደማይጠቅም በዚያ ከቀጠልንም አቶ ሽመልስ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የተናገሩትን የድምፅ ቅጂ ማግኘትና መለጠፍ ቀላል እንደሆነ ነግሬው ስልኩን ዘጋሁ።
የትናንቱን የአቶ ሽመልስ “እየሰበረ ሰጠው ላሞራ” ንግግርን ተከትሎ ይኽም ውሸት ይሆን? ብዬ ወደዚሁ ቀራቢያቸው ደወልኩ። ተቀይሞኝ ይሆን በሳቸው አፍሮ ስልኬን አይመልስም።እናም ወዳጄ ሆይ በድል በአል ፀብ የለም ስልኬን አንሳ ለማለት እዚህ መጣሁ።
አድርባይነት ይውደም!!!
Filed in: Amharic