>

ሀፍረት ጌጡ ኦዲፒ ለጥቅምት 2 በሰልፍ ላይ ሰልፍ ጠራች…!!! (ሀብታሙ አያሌው)

ሀፍረት ጌጡ ኦዲፒ ለጥቅምት 2 በሰልፍ ላይ ሰልፍ ጠራች…!!!
ሀብታሙ አያሌው
የጎጃም በር እና የመከበብ ዳፋ!
ጋዜጣዊ መግለጫ የሚበጠብጡ ወሮበሎች መላክ!
ኦዲፒ እስክንድርን እንደፈራችው ያህል የሰው ልጅ ፈጣሪውን ቢፈራ ኖሮ ዓለማችን ፍፁም ሰላማዊና ምርጥ በሆነች ነበረ።
የኦ.ዲ.ፒ የሰልፍ ጥሪ!!!

የመሪያችን ጠቅላይ ሚኒስቲር ዶ/ር አብይ የ2019 የአለም የሰላም ኖቤል ሽልማት ማሸነፍ ተከትሎ በመላው የክልላችን ወረዳዎች፤ ከተሞችና ዞኖች የደስታ መግለጫ ሰልፍ እንዲፈቀድ እየተጠየቀ ይገኛል። በዚህ መሰረት የፊታችን እሁድ ጥቅምት 2, 2012 በ20ቹም የዞን ከተሞች ሰላማዊ የደስታ መግለጫ ሰልፍ የተፈቀደ ሲሆን በተዎረድ ያሉ አመራርና የጸጥታ መዎቅሮቻችን ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት  ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እንዲከናወን በቱክረት እንዲሰራ የድርጅታችን ኦዴፓ ማእከል ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ገልጸዋል።

——
የጎጃም በር እና የመከበብ ዳፋ!!!
መንግስት ለደህንነቱ ጥበቃ የመደበለት የሜንጫ ዘመቻው መሪ አዲስ አበባ ቁጭ ብሎ “የጎጃም በር ይዘጋ” ብሎ ትዕዛዝ ሰጠ  መንገዱ ተዘጋ። ህፃናት የያዙ እናቶች ሳይቀሩ በሜዳው  በየጢሻው ተበትነው የሚሆነውን ይጠባበቃሉ።  በርካቶች ስለ ኖቤል ሽልማት ያወራሉ የዘመን ግርምቢጥ ይሉሃል እንዲህ ነው።
ወዳጄ የምስራቅ አፍሪካ ሰለም ቀዳሚ አጀንዳቸው የሆኑ አገራት ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንኳን ሸለሟቸው እሰየው። መፅሐፉም “ደስ ከሚላቸው ጋር ሁሉ ደስ ይበላችሁ” ብሏል።  ይሄን ብሎ ግን አያቆምም “ከሚያዝኑት ጋር እዘኑ”  ሲልም ያዝዛል። የኛ ሽልማት ዜጎቻችን ከዚህ ሰቆቃ ሲወጡ ነው።  ወዳጄ  ታዬ ደንደአ “ጎጃሜ አዲስ አበባ አምጥተው አስፍረዋል …ሂሳብ እናወራርዳለን”  ባለ ማግስት አለቃው ጀዋር በጉለሌ ፖስት በኩል የጎጃም መንገድ እንዲዘጋ አዘዘ የኦዴፓ ባለስልጣናት የተለመደ መቀናጇቸውን ተጠቅመው ወደ ተግባር ለወጡት።
ጀነራል አሳምነው “ጎበዝ ይሄ ህዝብ ተከብቧል” ያለው ለዚህ ነበር።  ልዩነትህን አስወግደህ እንደ ችቦ በጋራ ካልቆምክ መጪው ጊዜ ከባድ ነው።  ሰከን በል ፣ ተደማመጥ፣ ተደራጅ !!
Filed in: Amharic