>
5:01 pm - Thursday December 3, 4742

ጊዜ ደጉና አረመኔዋ ህወሓት !!! (ዘመድኩን በቀለ)

ጊዜ ደጉና አረመኔዋ ህወሓት !!!
ዘመድኩን በቀለ
 
*  ጊዜ ደጉ ያለ ምርጫ በድፍጥጫ ህወሓትን ተቃዋሚ ፓርቲ አድርጎ አሳረፋት፣ ጎለታት፣ ዘፈዘፋት፣ ወዘፋት፣ አስቀመጣት፣ ጣዳት። የክፋትን ውጤት ዓይኗን በዓይኗም አሳያት። የእጇንም ሰጣት። ከ45 የጥጋብ፣ የትዕቢት፣ የማንአህሎኝ፣ ማንነክቶኝ፣ ማን ደርሶብኝና የጉራ ዓመታት በኋላም እምበር ተጋዳላይን አንደ አዲስ መዘፈን፣ ማንጎራጎር አስጀመራት። እመበር ተጋዳላይ  !!!
•••
ጊዜ ደጉ፤ የጊዜና የዘመን ባለቤት ልዑል እግዚአብሔር ገና ብዙ ያሳየናል። ያሰማናል። ብልጦች ከእነሱ በበለጡ ብልጦች ተሸውደው ጉድ ተሰርተዋል፣ ጨካኞች ከእነሱ በበለጡ ጨካኞች የእጃቸውን ማግኘት ጀምረዋል። ብቻ ዕድሜና ጤናውን ይስጠን እንጂ ገና ብዙ እናያለን።
•••
ለህውሓት መጪው ጊዜ መልካም አይመስለኝም። የትግሬ ህዝብ አስቀድሞ እነዚህን እንደ ትኋን፣ እንደ መዥገር፣ እንደ አልቅት በላዩ ላይ ተጣብቀው ለ50 ዓመታት ከቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ከዐማራ ወንድሙ ጋር ያቆራረጡትን፣ ያቀያየሙትን አረጋውያን የህወሓት መስራቾች ጡረተኛና በዳይፐር የሚንገሳቀሱ የሽማግሌ ጎረምሶችን አደብ ካላስያዘ ገና ብዙ ዋጋ የሚከፍል ይመስለኛል።
•••
አሁን እመበር ተጋዳላይ ማንንም አይቀሰቅስም። የህወሓት አባላት እንደሁ ተመልሰው አይዋጉም። ኬክ ለምደዋል፣ ቁርጥና ክትፎ ለምደዋል። ውስኪና ቢራ እንደ ውኃ መጋት ለምደዋል። ኃላፊዎቹ ቀሚስ ዓይተው የማያልፉ ሴሰኞች አመንዝራዎችም ሆነዋል። ሲሻቸው በጨላ፣ በፈረንካ፣ ሲሻቸው በሽጉጥና በዱላ አስፈራርተው በመድፈር በሽታ ተለክፈዋል፣ ክላሽ ሳይሆን ቆንጆ ሴት መታቀፍ ለምደዋል፣ ቦንብ ሳይሆን ኮንዶም ማንጠልጠል ለምደዋል። ዳግም በረሃ አይወርዷትም። በዚያ ላይ ቦርጫቸውስ፣ በሽታቸውስ፣ ኤድሱ፣ ስኳሩ፣ ጣፊያው፣ ጉበቱስ፣ ሪሁስ፣ ልብ ድካሙስ በየት በኩል በረሃ ያስገባቸዋል? በፍጹም አይሞክሯትም።
•••
የቀደመችዋ ህዋሃት ብልጥ ነበረች። ከኤርትራ ጋር ተሞዳምዳ ሸአቢያን አጭበርብራ አደንዝዛ፣ ጎረቤቷን የዐማራን ገበሬ አደናብራ፣ አፍዝዛ፣ አደንዝዛ፣ ምርኮኛ የኦሮሞ ወታደሮችን በጀማ ወንዝ ዳር ሰብስባ፣ በካድሬዎቿ ሰበካ አደንዝዛ አፍዝዛ፣ ደቡቡን፣ ሶማሌውን ጋምቤላውን ቁስሉን ነክታ፣ አነሳስታ፣ የደርግን ወታደሮችን፣ አንድም በሴት ሌላም ጊዜ በጉቦ በቅሌት፣ አደንዝዛ፣ አወዛግባ ነበር ሥልጣን የያዘችው፣ ደርግን ያወረደችው።
•••
አሁን ግን ለህወሓት ይከብዳታል። ቀኑ ጨልሞባታል። እህል ውኃዋ አልቆ መቃብር ብቻ ይጠብቃታል። እንደድሮው ሸአቢያ አይረዳትም። እነ አሜሪካም እንግሊዝም አዲስ ፍቅር ከአቢቹ ይዟቸዋልና ዞር ብለውም አያይዋትም። ነፍሱን አይማረውና በትኔ መለስ ዜናዊም ፈረንጆቹን አበሳጭቶ ኢትዮጵያንም ከእነሱ አጋጭቶ ቂምና በቀል እንዲያስቡ አደራጅተ ነውና ያለፈው አይረዷትም። እኛን ከድቶ ቻይናን አስጠግቶ አብልቶ፣ አስብቶ እያሉ ይከሱታል ሁል ጊዜ ሲጠጡ ማኪያቶ። ዓረቦቹም እንደዚያው። ቻይና ሳትቀር ፊቷን አዙራለች። ከዐማራው ጋር የማይታሰብ ነው። በደህናው ጊዜ ርስቱን ቀምታው ለሞት ነው የሚፈልጋት። ሌሎቹም እንደዚያው እናም ለህወሓት አሁን እመበር ተጋዳላይ ይከብዳታል።
ጸሎት ፦ አምላኬ ሆይ እንደ ህወሓት አታድርገኝ!!!
 
ከፍ አድርገህ ሰቅለህ አትፈጥፍጠኝ። ከአራት ኪሎ በአንድ ጊዜ አሽቀንጥረህ ክልኧተ አውላሎ አትጣለኝ። ከአስፋልት ጎዳና ከሸራተን ከሂልተን ውሎ ከጉለሌና ከቦሌ አውጥተህ መቐሌ አክሱም ሆቴል ከርችመህ አታስቀረኝ። ለቁርስ ለንደን፣ ለምሳ ዱባይ፣ ለራት ኒዎርክ ስታንሸራሽረኝ ከርመህ አሁን አዲስ አበባ እንዲናፍቀኝ አታድርገኝ። በዶላር ጢባጢቤ ስታጫውተኝ ከርመህ አሁን እንደ ጨረቃ አታርቅብኝ። አምላኬ ሆይ እባክህን ጸሎቴን ስማኝ።
•••
በቀጣይ ህወሓት ምን ትሆን ይሆን? ማስፈራሪያ አድርጋ በመተዳደሪያ ደንቧ ያሰፈረችውን፣ ኢትዮጵያንም እጅና አፏን ከርችማ የጠረነፈችበትን አንቀጽ 39 የተባለው ማስፈራሪያ አያ ጅቦ ነገር ልጠቀመው ልትል ትችላለች። ይጠቅማት ይሆን ወይ? ያዋጣት ይሆን ወይ? ፌደራል መንግሥቱስ ህወሓት መስመር እስታለሁ ካለች እንደድሮው እሹሩሩ ወይስ ኡሩሩሩ ይልባት ይሆን? ይለማመጣታል ወይስ ይዠለጣታል? ኮርኩሞ ያስተካክላታል? ወደፊት በሉለት ይለይለት ብሎ የደርግን ዘፈን ከፍቶ ያፎገላታል? እሱም ጊዜው ሲደርስ ይታያል።
ምክር ለህወሓት!!!
ከወደቁ ወዲህ አጉል መንፈራገጥ ለመላላጥ ነው እንዲሉ አበው አንቺም ከበፊቱ ይልቅ የወደፊቱ ይከፋብሻልና ዊኒጥዊኒጡ ይቅርብሽና ህዝቡንም ምድሪቱንም ዳግም ወደ ትርምስ ሳታስገቢ በተሎ ወደ መስመር ብትገቢ ይሻልሻል። አይ አይሆንም ካልሽ ደግሞ የሚከተለው ደፋ ይከተልሻል።
• ሻእቢያ የቀደመ ቁርሾውን ይወጣብሻል።
• ዐማራ በፈጸምሽበት በደል ይበቀልሻል፣ አያግዝሽም። አይተባበርብሽም። ይሄ ቅማንት ምናምን እያልሽ የምትዪውንም ነገር ብትተዪው ይሻልሻል።
• ቀይባህር ዙሪያ የሰፈሩት አረቦች፣ አሁን ያለአቻ ጋብቻ ከአቢቹ ጋር የፈጸሙት ዓረቦች በአክሱም ሙስሊሞች ስም ይቀጠቅጡሻል። የመን ላይ ያዘነቡትን መዓት በምድርሽ ላይ ያዘንቡብሻል። ይሄ ዳፋው ለዐማራውም እንዳይተርፍ እሰጋለሁ። በሰበቡ ኦርቶዶክስን ይበቀሏታል።
• በህወሓት መሪዎች ስህተት ምክንያት የቆሰሉ ልቦች ሁሉ እንዳይጫኑሽ መላ ፈልጊ።
•••
የተከበርከው የትግራይ ህዝብ (ህወሓት ስታይል ) 
• ከጃጁ ሽማግሌዎች፣ ከበቀለኞቹ፣ አብዛኛዎቹ ውሸታም፣ ሌቦች፣ የሰው ሚስት ቀምተው ደፋሪዎች ከሆኑ፣ ሃይማኖት አልባ፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር ከሌላቸው ከህወሓት መሪዎች ጋር አታብር። ከአነሱ ጋር ጋር አብረህ አትቀበር፣ አትውረድ ወደ መቃብር። ይልቁኑ ህወሓትን አንተው እንደፈጠርካት አንተው ቅበር። ምንም ዓይነት ወሬ ሳያስፈልግ ሳይፈጠር ግርግር አንተው ህወሓትን ቀብረህ ኢትዮጵያንም ትግራይንም አድን። አደራ በሰማይ አደራ በምድር።
•••
ሻሎም !  ሰላም !
ጥቅምት 5/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic