>

ጋዝ ጋዝ አለኝ! ( አገር ሆይ!)  ደረጄ ደስታ

ጋዝ ጋዝ አለኝ! ( አገር ሆይ!) 
ደረጄ ደስታ
” ….እንደ እድር እቃ ማንም ለሰልፍም ሆነ ለአጀብና ነውጥ እንዳሻው እሚጠራው ሥራ ባይኖረው አይደል? ይበላ ይሠራ ያጣ ደግሞ ቢገድል ቢሞት ምን ይጨንቀዋል? ደግሞ የማንነት ጥያቄ!!! ማንነቱ ድህነቱ የሆነ ደሀ ቀድሞስ ቢሆን ምንስ ነህ ቢሉት ባይሉት ምን ይረባዋል??
—-
የዚህ ሁሉ ነገር ምክንያቱ አንድም ሥራ አጥነቱ፣ በዚያ ላይ የፖለቲከኛውና ብሔርተኛው ሥራፈትነቱ ተደማምሮ  እንደሆነስ? እንደ እድር እቃ ማንም ለሰልፍም ሆነ ለአጀብና ነውጥ እንዳሻው እሚጠራው ሥራ ባይኖረው አይደል? ይበላ ይሠራ ያጣ ደግሞ ቢገድል ቢሞት ምን ይጨንቀዋል? ደግሞ የማንነት ጥያቄ!!! ማንነቱ ድህነቱ የሆነ ደሀ ቀድሞስ ቢሆን ምንስ ነህ ቢሉት ባይሉት ምን ይረባዋል??
…ድህነት ሥራ አጥነትና የኑሮ ውድነት ..?? ሰውየው ራሳቸው እየሳቁ ሊያንበሸብሹን ጋዝ ሊያፈልቁ በዜናው ተስፋዬን ሲያደምቁ ትዝ ይለኛል። እና ዛሬ “አስታውሳለሁ መች እረሳለሁ…”  እሚለው ዘፈን ትዝ አለኝ። ድህነቱና ኑሮው ጋዝ ጋዝ ቢለኝ ያ አንድ ሰሞን አገሬ ኦጋዴን ላይ ተገኝቷል የተባለው ጋዝ/ነዳጅ መጣብኝ። ምን ደርሶ ይሆን? ይቺ ቀበጥ ሀብታም አገር መቸም ያለችውን ብቻ ሳይሆን ያገኘቸውንም ነገር ትረሳለች። እስኪ አስታውሷት! ወይስ እኔው ረስቼው ይሆን? እኔም እኮ ጥሎብኝ የነገሩኝን ሁሉ ከስር ከስሩ እረሳለሁ። በተስፋ ላይ ተስፋ- ተስፋ ተደርቦ፣  በኢንደስትሪ ዞኑ፣ በዞኑ ግድቡ፣ በግድቡ ጋዙ…..የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች… ቁም ነገሩ እሱ ሳይሆን…የማንነት ሁኔታዎች….አይ ኢትዮጵያ!
እናልህ አንተም ወዳጄ – አገርን እንደ ልብስ ቀድጄ ልልበሰው ባይ – ትግል እያደለብክ ማንነት እየቀለብክ በልማት ከድል በኋላ መፈክርህ ልማታዊነትን እያወገዝክ: ወይ አትረታ ወይ አትሰራ: ለጋዝህ ክብሪት እንደተመኘህ…የተስፋ ጋዜን ብታነደው-   ነደደኝ! ሥራ አጥነት ላይ አገር አጥነት ሲጨመር ደግሞ ይታይህ!
Filed in: Amharic