>
9:14 am - Tuesday July 5, 2022

ጃዋር መሐመድን ለፍርድ የሚያበቁት 11 ወንጀሎች‼ (ግራ ወርቅ ዝናቡ)

ጃዋር መሐመድን ለፍርድ የሚያበቁት 11 ወንጀሎች‼
ግራ ወርቅ ዝናቡዮቶር ሚዲያ
የኦሮሞው አክቲቪስትና የኦኤምኤን ቴሌቪዥን ጣቢያ ስራ አስኪያጅ አቶ ጃዋር መሐምድ በኢትዮጵያ ፖሊስ እየተጠበቀ፣ ህዝብ በሚከፍለው ግብር እየተዝናና ከአረብ ሀገሮች እርዳታ እየተቀበለ ኢትዮጵያን ለማፈራረስና እስላማዊ መንግስት ለመመስረት የማይፈነቅለው ድንጋይ፣ የማይሰራው ወንጀል የለም፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ በመለያየትና ጥላቻ አጀንዳ ላይ እንድትጠመድ ሰፊ ስራ ሰርቷል፣ ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ታሪካዊ፣ ባህላዊና ፖለቲካዊ ጉዳት አድርሷል፡፡ ህዝብ በስጋትና በስቃይ እንዲኖር አድርጓል፡፡ ከፍተኛ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽሟል ፡፡ ይህ ሰው ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሚከተሉትን ዋና ዋና ወንጀሎች የፈጸመ ስለሆነ በዓለም አቀፍም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚስከስስ ወንጀሎችንና በደሎችን ፈጽሟል፡፡
1.    ሁለት መንግስት አለ ማለቱ ፡- ጃዋር መሐመድ በመንግስት ስልጣን ምንም አይነት ኃላፊነት የሌለው ሲሆን በተለያዩ ስብሰባዎች የሚቀመጠው ከርዕሰ መስተዳድሩ ወይም ከጠቅላይ ሚኒስተሩ ጎን ነው፡፡ መግለጫ የሚሰጠውም እንደ አንድ ሀገር መሪ እራሱን እያሰበ ነው፡፡ በዚህ አስተሳሰቡ በአንድ ወቅት ሚዲያ ላይ ቀርቦ ‹‹ ሁለት መንግስት አለ አንዱ የዐብይ መንግስት አንዱ እኔ የምመራው የቄሮ መንግስት ›› ብሎ በመናገር የሀገሪቱን ስርዓተ መንግስት ተዳፍሯል፣ አምጽና አድማን ቀስቀሷል፣ የመንግስት ተቀባይነትን አዋርዷል፡፡ ይህ ንግግሩ ለህዝብ አንድነትና ለመንግስት ታማኝነት፣ ለሀገር ህልውና አደጋ በመሆኑ በህግ ሊስጠይቅ ይገባል፡፡
2.    ህዝብ የሚያጋጭ የኦነግን ካርታ በመሰረት ድንጋይ ላይ ማስቀመጡ ፡- ጠብ አጫሪውና ጸረ ሰላሙ ጀዋር የአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎችን በተለይም ወሎ የተካተተበትን የኦነግ ካርታ በኦኤምኤን ቴሌቪዥን ጣቢያ የግንባታ መሰረት ላይ በማስቀመጥ በአንድነትና በፍቅር የነበረውን የአማራንና የኦሮሞን ህዝብ ለማጋጨት ተንኩሷል፡፡ በአንድነት የነበረውን ህዝብ ጥርጣሬና ግጭት ውስጥ አስገብቷል፡፡ በተለይም የአማራ ህዝብ ባይታገስ ኖሮ ወደ ጦርነት የሚያመራ ወንጀል ፈጽሟል፡፡
3.    በኮየፌቸ ኮንድምኒም ቄሮን በማስተባበር ችግር  መፍጠሩ ፡- እንደ ሰይጣን ነገር ሲፈልፍል የሚያድረው ጀዋር መሐመድ የአዲስ አበባ ህዝብ ቆጥቦ የሰራውንና የሀገሪቱ መንግስት የገነባው ኮንደሚኒየም የኦሮሞ ነው በማለት የሚጠላውን የሚኒሊክን ባህር ዛፍ ዱላና ገጀራ አስይዞ ሞተን ሳናልቅ አይገቡበትም በማለት ሰላም እንዲደፈርስና ከአለቆቹ ጋር ተባብሮ እጣ የወጣላቸው ቀርተው ኦሮሞዎች ብቻ እንዲወስዱት አድርጓል ወይም የእኔ ብቻ በሚል ስስት እጣ የወጣላቸው ዜጎች ያለ ቤት እንዲቀሩ አድርጓል፡፡
4.    ክርስቲያኑን በሜንጫ በሉት አንገቱን ቀና እንዳይ እናድረገው ብሎ ክርስቲያኖች እንዲሞቱ ማድረጉ፡- ጀዋር ሙስሊሞን ሰብስቦ የፖለቲካ ስልጣኑን ያዙ፣ ኢኮኖሚውን ተቆጣጠሩ፣ ክርስቲያኑ ቀና ብሎ እንዳይሄድ አንገቱን በሜንጫ እንበለው ብሎ በመናገር በተለይም እርሱ የተወለደበትን አካባቢ በመጠቀስ ማንም ክርስቲያን ቀና ካለ በሜንጫ አንገቱን እንደሚለው በመዛት በተለያየ ወቅት በኦሮሚያና በአካባቢው የሚኖሩ ክርስቲያኖች እልቂት ምክንያት ሆኗል፡፡
5.    ሲዳማን በኃይል ክልል እናደርገዋለን በማለት ለብዙ ሕይወት መጥፋትና የኃብት ውድመት መንስኤ መሆኑ ፡- የሲዳማ ህዝብ ክልል እንሁን የሚለው ጥያቄ ኃያል ኦሮሚያን ለመመስረት ለሚደረገው ጥረት አጋዥ ስለሆነ አዛኝ ቂቤ አንጓቹ ጃዋር ሐዋሳ ሂዶ መንግስት ካልፈቀደ በኃይል ክልል እናደርገዋለን ብሎ በመዛትና ለኤጀቶዎች ተልዕኮ በመስጠት ሐምሌ 11/11/2011 ዓ.ም በሲዳማ ዞን ከፍተኛ የሆነ ንብረት እንዲወድም፣ አብያተክርስቲያናት እንዲቃጠሉ፣ ምእመናን እንዲታረዱና እንዲሞቱ ምክንያት ሆኗል፡፡ ይህ ሰው ለሞቱት ሰዎችም ሆነ ለወደመው ንብረት ሙሉ ተጠያቂነት አለበት፡፡
6.    በፌስቡክ ገጹ ጥበቃዎች ሊነሱብኝ ነው ብሎ ቄሮን በመቀስቀስ የዘር ጥፋት ማድረሱ ፡- መጮህ የለመደው ጃዋር ሀገር ሰላም ሲሆን ስለሚጨንቀውና ያለበት የጥላቻ መንፈስና ጭንቀት ስለሚረብሸው በሌሊት ጥበቃዎቸ ሊነሱ ነው ፣ ሊገሉኝ ነው ብሎ ማገናዘብ ለማይችሉ ተከታዮቹ ጮኸላቸው፡፡ በዚህ ጩኸቱ ከ86 በላይ የንጹን ደፍ ፈሰሰ፣ አካል ተቆራረጠ፣ ንብረት ወደመ ፣ በምድር ላይ ያልተፈጸመ ግፍና በደል በኦሮሚያ ምድር ላይ ተፈጸመ፣ የዘርና የሃይማኖት ማጽዳት ዘመቻ ተከናወነ፡፡ ታዲያ ይህ ሰው ዘላለማዊ ፍርድና ቅጣት ቢሰጥ እንኳን ፍትህ አይሞላም፡፡ ዘርና ሃይማኖትን መሰረት ያደረገ ጥፋት በመፈጸሙ ዓለም አቀፍ ወንጀለኛ ነው፡፡
7.    በኦሮሚያ ክልል በተለያየ ጊዜ መንገድ እንዲዘጋና ህዝብ እንዲገላታ፣ ንብረት እንዲወድም ማድረጉ ፡- ጃዋር መሐመድ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን (ጥቅምት 2012 ዓ.ም) ቄሮ የተባለውን ቡድን መንገድ እንዲዘጋ፣ ቤት፣ንብረት፣ ፋብሪካ እንዲያቃጥልና እንዲያወድም በማዘዝ በመላው የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ ንብረት አወድሟል፣ ህዝብ ተንገላቷል፣ ለችግር ተዳርጓል፣ ስራ ተስተጓጉሏል፡፡ በቅርቡ በጥቅምት ወር ባስተላለፈው መልእክት እንኳን ህዝብ ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል በተለይም የጋራ መዲናችን ወደ ሆነችው አዲስ አበባ እንዳይገባ በመታገዱ በሽተኞች፣ ተማሪዎች፣ ህጻናት፣ አዛንቶች ከፍተኛ የሆነ መንገላታት ደርሶባቸዋል፣ ለአላስፈላጊ ወጭ ተዳርገዋል፣ አብያተክርስቲያናት ተቃጥለዋል፣ በርካታ ሀብት ንብረት ወደሟል፡፡ ስለዚህ ጃዋር ለዚህ ሁሉ ጥፋትና በደል ተጠያቂ ዓለም አቀፍ ወንጀለኛ ነው፡፡
8.    የመደመር ክልኩሌተር እኔነኝ መንግስት ሆነን እየመራን ነው ማለቱ ፡- ጥሩን ነገር በሙሉ ለእርሱና ለቄሮ በመስጠትና ለሚኒሊክና ለፍጠኛ በሚለው ህዝብ የሀሰት ታሪክ በመናገር የሚታወቀው ጃዋር የሀገሪቱን መንስግት ተቀባይነት ለማሳጣትና እራሱን ለማግነን በቴሌቪዥን ቀርቦ ለውጡን የመራሁት እኔ ነኝ፣ የመደመር ካልኩሌተር እኔ ነኝ መንግስት ሆነን ሀገር እየመራን ነው ብሎ በመናገር የህዝብን አንደነት የሚጋፋና ጥርጣሬ የሚፈጠር መልዕክት አስተላልፏል፡፡ በዚህም የሀገሪቱ አንድነት አደጋ ላይ እንዲወድቅ አድርጓል፡፡
9.    የጋራ ታሪክ የለንም በማለት ህዝብን ለግጭት ማነሳሳቱ ፡- ነገረኛው የተንኮል አርቃቂው ጀዋር በራሱ የኦኤምኤን የቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርቦ የጋራ ታሪክ የለንም በማለት አፄ ምኒልክንና አማራን በማውገዝ የፌደራል መንግስቱን በመውቀስ የሀገር አንድነት የሚፈታተን ጠብ አጫሪና አመጽ ቀስቃሽ መልእክት በማስተላለፍ በተለያየ ጊዜ ቄሮ ለሚፈጥራቸው ግጭቶች ምክንያት በመሆኑ አሸባሪ ወንጀለኛ ነው፡፡
10.    የብሔራዊ ፈተናን በማውጣት ሀገሪቱን ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጉ ፡- ጃዋር አሜሪካ ሆኖ እየዝናና የ12ኛ ክፍል ፈተናን በፌስቡክ በመለጠፍ በሀገሪቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ፣ የሰው ኃይል፣ የጊዜና የማቴሪያል ኪሳራ አድረሷል፡፡ በመላ ሀገሪቱ የነበሩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ የሞራል ኪሳራ አድረሷል፣ የወደፊት ሕይወታቸውን አጨልሟል፡፡ በዚህም ጊዜው የተረኝነት በመሆኑ እንጅ በወቅቱ በት/ሚኒስተር የነበሩ የኦነግ አባላትን ተጠቅሞ ላደረሰው ጥፋት እስር ቤት መገኘት ነበረበት፡፡ ነገሩ በተቃራኒው ሆኖ ጠባቂ ተመደበለት፡፡
11.    በሚዲያው ህዝብና ህዝብ የሚያጋጭ ተደጋሚ መግለጫና መረጃ መስጠቱ ፡– ጸረ ሰላሙና ጸረ አማራው ጃዋር እንደፈለገ የሚዘውረውን የራሱን ኦኤምኤን ቴሌቪዥ ጣቢያን በመጠቀም በአማራ ክልል በተለይም በማእከላዊ ጎንደር በቅማንትና አማራ መካከል ከፍተኛ ግጭት እንዲፈጠር የሀሰት መረጃ በማቅረብ፣ የተለያዩ የሐሰት ትርክቶችንና መረጃዎችን በማሰራጭት በሀገሪቱ ግጭት እንዲስፋፋና ሰላም እንዳይሰፍን፣ የሰው ሕይወት እንዲጠፋና ንብረት እንዲወድም በማድረጉ አሸባሪ ወንጀለኛ ነው፡፡
Filed in: Amharic