>

አዝማሚያው ያላማራቸው ኦቦ ለማ መገርሳ "ብልጽግና ኬኛ" ብለዋል!!! (ዳንኤል አሰፋ)

አዝማሚያው ያላማራቸው ኦቦ ለማ መገርሳ “ብልጽግና ኬኛ” ብለዋል!!!

ዳንኤል አሰፋ
 
 * ኦቦ ለማ መገርሳ ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ለመስራት መስማማታቸውን OBN በሰበር ዜና አብስሯል!!!
የለውጡ ፊታውራሪ ከሆኑት አንዱ ኦቦ ለማ ነበሩ። የለውጡ ቡድን ስምም በአብዛኛው በእሳቸው ስም ይጠራ ነበር (Team Lemma) በወቅቱ  ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የአብዛኛውን ህዝብ ይሁኝታም አግኝተው ነበር።
የሆነው ሆኖ  ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አወዛጋቢ ሆነው ብቅ አሉ። በተለይ ኦሮሞን “ከከተማ ፖለቲካ ጋር ለማላመድ የዲሞግራፊ ለውጥ ማድረግ ያስፈልጋል፤ ይህንንም ጀምረናል” ያሉበት ንግግር ውግዘት አስከትሎባቸው የፖለቲካ ጉዟቸውም ቅርቃር ውስጥ መቆየቱ የአደባባይ ሚስጢር ነበር።
በተለይ ከፅንፈኛ ብሔርተኞች ጋር በመተባበር በአብይ መንግስት ላይ እያሴሩ ነው የሚለው ጭምጭምታ ከአክራሪዎቹ “Abiy Must Go” ጥሪና ሀሽታግ ጋር ተዳምሮ ኦቦ ለማ አንዳች ክፉ ስራ ውስጥ ስለመዘፈቃቸው ፍንጭ የሚሰጥ ነበር።
የአብይን “ፍጥነት” መግታት የተሳናቸው ኦቦ ለማ ተስፋ መቁረጣቸውን በሚያሳብቅና የዓለምን ፖለቲካ የመረዳት አቅም ውስንነት ጋር ተዳምሮ የመጨረሻ ያሉትን ካርድ በVOA አማካኝነት መዘዙ። ከዚያም በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ White Hause ተጠርተው “ተመክረውና ተቆንጠጠው” ተመለሱ። እነሆ የቁንጥጫው ውጤትም በOBN በኩል ዛሬ ተነገረ።
ኦ.ቢ.ኤን ገዳዩ በዚህ መልኩ ነው አለባብሶ ያቀረበው :-
 
ኦቢኤን ታህሳስ 13፣ 2012-አቶ ለማ መገርሳ በመደመር ፍልስፍናና በፓርቲዎች ውህደት ላይ የነበረቸውን ልዩነት አጥብበው የህዝቡን ትግል ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለማሻገር መስማማታቸው ተገለጸ
አቶ ለማ መገርሳ ከዚህ ቀደም በመደመር ፍልስፍናና በፓርቲዎች ውህደት ላይ ያላቸውን ልዩነት በኦሮሞ ባህል መሰረት ስምምነት ከተደረገ በኋላ ልዩነታቸውን አጥበው ከዚህ በኋላ በጠንካራ አንድነት በጋራ በመስራት የህዝቡን ድል ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር ከስምምነት ተደርሷል፡፡
ይህ ስምምነት የተደረሰው የቀድሞ የODP ስራ አስፈጻሚዎችና ነባር አመራሮች በጋራ ባደረጉት ውይይት ነው፡፡
ፓርቲው የዴሞክራሲ ስርዓትንና በኦሮሞ ባህል መሰረት ውስጣዊ ችግሩን እና የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ጠንክሮ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
በፖለቲካ ሂደት ውስጥ በተለይ ደግሞ ሪፎርም በሚደረግበት ወቅት የሀሳብ ልዩነቶች መኖራቸው የተለመደ መሆኑ ነው የተጠቆመው፡፡
የሀሳብ ልዩነት መኖር በራሱ ችግር እንዳልሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ትልቁ ነገር የሀሳብ ልዩነትን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ  መሆኑ  ተገልጿል፡፡
“ፌደራሊስት ነኝ” የሚለው የዝንጀሮ መንጋም በኦቦ ለማ በኩል ለመጫወት ያሰበው ካርድ ተቃጥሎበት ቁዘማ ላይ ነው።
Filed in: Amharic