>

አማራና ትግሬ (መስፍን አረጋ )

አማራና ትግሬ

መስፍን አረጋ

‹‹ሕውሓትና ትግሬወችን በማዳከምና በፌደራል መንግስትና በጠቅላላው በኢትዮጵያ ፖለቲካ የነበራቸውን ሚና ዝቅ እንዲልና ልካቸውን እንዲያቁ ካደረግን በኋላ …. አማራና ትግራይ በቀጣይ እንዲናቆሩ ማድረግ ነው፡፡››  ጃዋር ሙሐመድ

 

‹ኦሮማራ ታክቲክ እንጅ ስትራቴጅ አይደለም፡፡› ሕዝቅኤል ጋቢሳ      

ኦሮትግሬስ?

  

አማራና ትግሬ በጥቅል ሐበሻ

ርስበርስ ተናክሰህ በምክኒያት ተልካሻ

ስትዳከምለት በስተመጨረሻ

ቁርጥምጥም አደርጎ የቦረና ውሻ

ለሃች ይቀብርሃል እሶፍ ኡመር ዋሻ፡፡

 

ሐበሻ ትግሬ ሆይ የመቀሌ አስመራ

ተጠየቅ እንጠይቅ መልስልን አውራ፣

ካበሻ ወንድምህ ከአማራ ጋራ

ከቶ ምን አረገው ጥልህን መራራ?

ሐይማኖት ነው ባህል፣ ቋንቋ ወይስ ፊደል

የቱ ነው ምክኒያትህ ለማይታረቅ ጥል?

በስልጣን የመጣን በስልጣን የሚገል

ያማራ፣ አሮሞ የትግሬ ቅልቅል

የሆነ ገዥ መደብ ለሠራብህ በደል

ተጠያቂ አድርገህ አንዱን በመነጠል

ለምን ትጠላለህ አማራን በጥቅል?

አተርፋለሁ ብለህ ባማራ ኪሳራ

ሰብአዊነት ከሌለው ቅንጣት ከማይራራ

ኦነግ ከተሰኘ አረመኔ ጋራ

እንዴት ታስባለህ መሻረክ ለሤራ?

 

አንተን ከፊት አርጎ ራሱን ከኋላ

ባንተ ተጋድሎ ጥላና ከለላ

ምኞቱ ተሳክቶ አማራን ቢበላ፣

እርኩስ ስለሆነ ሆዱ የማይሞላ

ወዲያው ይጀምራል አንተኑ ጉንተላ፡፡

 

የጠላቴ ጠላት የሚሉት ዘይቤ ደንብ

ተማምሎም እንኳን በየወንዙ ጣገብ

ኋላና ፊት መሄድ ለሚፈራራ ጅብ

አይሰራም ለኦነግ ለመንጋው ስብስብ፡፡

 

ስለማይሆንለት ማሸነፍ ተዋግቶ 

አንደኛውን ባንዱ ክፉኛ አስመትቶ

ጦቢያን ሊቆጣጠር ሊታይባት ጎልቶ፣

ኦሮማራ እንዳለ ትግራይን ለማግለል

ኦሮትግሬ ብሏል አማራን ለመግደል፡፡

 

አባቱ የጥንቱ ዘላኑ አለሌ

ምንትሴውን ገልቦ ሲገርፈው ሱማሌ

እግሬ አውጭኝ በማለት አንጠልጥሎ ጡሌ

ግራኝ በጋጠጠው ያበሻ መስክ ጨሌ

ሲስፋፋ እንዳረገው ጀምሮ ከባሌ፣

ልጁም የዘመኑ አረመኔው ጃሌ 

በድንገት አደጋ ጥሎ በቀበሌ

ከመግደል በስተቀር ሕፃን ሽማግሌ፣

ፊት ለፊት ተፋልሞ ከሚባል እገሌ

አሸንፎ እማያቅ በነፍጥ ወይ በጊሌ

እዚህ ግባ እማይሉት ነበረ አልባሌ፡፡

ዛሬ ግን ገነነ እድሜ ለትሕነግ

ያምደጽዮን ርስት ነው ብሎ የኦነግ

ኦሮምያ ብሎት ባገር ስም ማዕረግ

ስላመቻቸለት ያሻውን እንዲያደርግ፡፡

 

አጼ ልብነ ድንግል ይዞ ብቻ ጋሻ

ግራኝን ለመርዳት ከመጣ ወጠምሻ

በመድፍ ከታገዘ ከቱርክ ጦር ባሻ

የተፋለመበት እየመራ አበሻ፣

ታላቁ ጦርሜዳ ያ ሽንብራ ቁሬ

ስሙ ተለውጦ ዱከም ሁኗል ዛሬ፡፡

ከሚሴም ገነነ ተረስቶ ምድረገኝ

አስታውሶ እሚያነሳው ጀግና እስከሚገኝ፡፡

 

ጦቢያ በእምንቷ እጇን ስትዘረጋ

ፈጣሪ መልሶ ፊቱን ወደሷጋ

የላከላት እንደሁ ዳግማዊ አባነጋ፣

አሩሲና ከፋ፣ ወሎና ወለጋ

በቀድሞ ስማቸው ይለብሳሉ ጸጋ፡፡

 

ኢምንት ነን እንጅ ግዙፉን ለመክሰስ

ምኒሊክ እምየን የምንችል ለመውቀስ፣

ለገዳ ወረርሽኝ ሳይሰጡ ሙሉ ፈውስ

ወረኢሉ ወረምንትስ፣ ለገጣፎ ለገምንትስ

ሰላሌ፣ ጉለሌ፣ ቡልቡላ ቅብጥርስ

የተሰኙት ስሞች ከዘር ጭፍጨፋ መልስ፣

ሁነው ጠባሳወች የተስፋፊወች ቅርስ

በመቅረታቸው ነው እስከዛሬ ድረስ፡፡

 

በኦሮምኛ ቃል ያለ ተሰይሞ

በሚያስብል ደረጃ ሁሉም አስቀድሞ

አይደለም ኦሮሞ ወይም የኦሮሞ፡፡

 

በስሙ ኦሮሞ ከሆነው ሕዝብ ላይ

ዘጠና በመቶ ወይም ከዚያ በላይ

በደሙ ያይደለ ብሔሩን የረሳ

ወይ ጉዲፈቻ ነው አለያም ሞጋሳ፡፡

 

አንዳርጋቸው ብሎ ቢከተል ቂጢሳ

ቂጢሳን ከማለት የኦሮሞ ጎሳ

ይበልጥ ያሳምናል ማለት ነው ሞጋሳ፡፡

 

መቸና የት እንደሁ ሳይገልጽ ሰውሮ

የኦሮሞን ጥያቄ በደልና ሮሮ

ተረክቤያለሁኝ አንድ ባንድ ተቆጥሮ

ብሎ የነገረን ለሚቾ ዘሆሮ፣

ሐረጉ ቢመዘዝ በደም ትንታኔ

የመሆን እድሉ ከረዩ ቦረኔ

እጅግ ያነሰ ነው ከመሆን ብቸኔ፡፡

 

ካስፈለገም ደግሞ እንደው በደፈና

በመመልከት ብቻ የደሙን ወዘና

ምንም እንደሌለው ከወደ ቦረና

መናገር ይቻላል በሙሉ ልቦና፡፡

 

ስለዚህ ለሚቾ ኢጆሌ መገርሳ

ተረከብኩ ያለውን ጥያቄ ሲያነሳ፣

የቦረና ውልዱ ሳለ የምጣዱ

አትንጣጣ በሉት አንተ የሰፌዱ፡፡

ዲኔግዴ፣ ጉበና ቢቂላ ወይ ባልቻ

ኦሮሞ ነው ብሎ በመጠርያው ብቻ

ኦነግ ያደረገው የታሪክ መጫወቻ፣

አብዛኛው ቢታይ በደም መመልከቻ

ወላጆቹ ታርደው በሜንጫ ዘመቻ

የተለወጠ ነው ወደ ጉዲፈቻ፡፡

 

ጉዲፈቻ ደግሞ በመሆኑ ገርባ

ከገርባ በስተቀር ሌላ እንዳያገባ

ስለሚከለከል በገዳ ድነባ

ደሙ የለበትም ጠብታ የሉባ፡፡

 

ኦሮሞን ስናየው በዚህ ረገድ ዓይን

መሆን ይቅርና የጦቢያ ብዙሃን

እጅግ ያነሰ ነው ከሁሉም ሕዳጣን፡፡

 

ከጦቢያ ብሔሮች እሱ ተነጥሎ

መከለል ካለበት የብቻው ተብሎ

ሞያሌም ይበዛል ይሰጠው ተከፍሎ፡፡

 

በግራኝ ወረራ እንደታየው ዓይነት

እንደገና ደግሞ ባብይ አህመድ መተት፣

አበሻ ሲዳከም ብቻ የሚከሰት

የኦሮሞ መስፋፋት ነው እንደ ፓራሳይት፡፡

  ስለዚህ የጦቢያ መሠረተ ችግር

ያበሻ መዳከም እንጅ በመቃቃር

መቸም ሁኖ አያቅም የጠላት መጠንከር፡፡

 

ከጠላቶች ደግሞ ኦነጊቾን መሳይ

ሙሉ ጥንካሬው ነውና ባንዳ ላይ፣

ባንዳ ከሐበሻ ከተለቃቀመ

ኦነግ አለቀለት አበቃ አከተመ፣

የገዳው ታማሚ በግዱ ታከመ

ዓይኖቹን ገለጠ ቅዠቱን አቆመ፡፡

 

ይቅር ተባብለው ለትናንቱ ዛሬ 

ድርና ማግ ሁነው አማራና ትግሬ

ድነው እንዲያድኑ ጦቢያን ከኬኛ አውሬ፣

የሁለቱም ባንዶች ብአዴን ወያኔ

መክሰም አለባቸው ባስቸኳይ ውሳኔ፡፡ 

የትግሬና አማራ በእሳት መንገብገብ

የኦሮሞ እዳር ሁኖ እሳቱን ማራገብ

እንዲህ ይመሰላል ባንበሶችና ጅብ፡፡ 

በእኔ ነግስ እኔ ነግስ ውጊያ በመቀስቀስ

አንበሳና አንበሳ ተፋልመው እርስ በርስ

አንደኛው ድል ሆኖ የሞት ጽዋ ሲቀምስ

ሌላኛው ሲያጣጥር ግቢ ነፍስ ውጭ ነፍስ፣

የሞተን ተራምዶ የቆሰለን ገድሎ ጅቦ ሆነ ንጉስ፡፡ 

 

ያገርህ፣ የምነትህ፣ ያንተነትህ ዳራ       

ባንድኛችሁ እንኳ እንዲኖር ሲጠራ

ሳትፋለም በፊት ከወንድምህ ጋራ

የጋራ ጠላትህ መሞቱን አጣራ፡፡

 

መስፍን አረጋ 

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic