>

አማራው በየቀኑ  እየደረሰበት ካለው ውድረት ለመውጣት ምን ማድረግ አለበት?  (አቻምየለህ ታምሩ)

አማራው በየቀኑ  እየደረሰበት ካለው ውድረት ለመውጣት ምን ማድረግ አለበት? 

አቻምየለህ ታምሩ
ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የወሮበሎች ስብስብ የኢትዮጵያ መንግሥት ሳይሆን የኦሮሞ ብሔርተኞች የአፓርታይድ አገዛዝ መሆኑን ከዚህ በፊት  ባቀረብናቸው ተደጋጋሚ ማሳያዎች አሳይተናል። ከሰሞኑ የአፓርታይድ አገዛዙ በአሸባሪው ኦነግ የታገቱ የአማራ ሴት ተማሪዎችን በሚመለከት እያደረገ ያለው ነገር  ግን ከመቼም በላይ አገዛዙ የነበረውን ጭንብሉን አውልቆ በአፓርታይድ አገዛዝነት ራቁቱን እንዲከሰት አድርጎታል።
አማራ ክልል በሚባለው አካባቢ ኦሮሞን የሚመለከት የመሰለው አንድ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር ካገዛዙ ቁንጮ እስከ ልሳኖቹ ድረስ የማያዥጎደጉዱት ውግዘትና ተቃውሞ አልነበረም። አገዛዙ በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰውን በደልና ግፍ  ግን በሰው ላይ እንደደረሰ በደልና ግፍ ስለማይቆጥረው  አገርና መንግሥት ያላቸው መስሏቸው ወደ ዩኒቨርሲቲ  የገቡ ወጣት ሴቶች በትምህርት ገበታ ላይ ሳሉ  በግፍ ታፍነው ተወስደው በየቀኑ እየተደፈሩና የስነ ልቦና ጥቃት  እየደረሰባቸው  በስቃይ ላይ በሚገኙበት በዚህ ወቅት የአፓርታይዱ ቁንጮ «ሴቶች በፖለቲካ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚም ከወንዶች የሚስተካከሉበት መንገድ ለመፍጠር ብልጽግና አበክሮ ይሰራል» እያለ በቁስላችን ላይ ጨው ይጨምርበታል።
በዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ ስሌት መሰረት የአማራ ሴቶች እንደሰው ስለማይቆጠሩ «ሴቶች በፖለቲካ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚም ከወንዶች የሚስተካከሉበት መንገድ ለመፍጠር ብልጽግና አበክሮ ይሰራል» የሚለው የአምበሉ መሪ ቃል በግፍ ታፍነው ተወስደው በየቀኑ እየተደፈሩና የስነ ልቦና ጥቃት  እየደረሰባቸው በስቃይ ላይ የሚገኙ የአማራ ተማሪዎችን አይጨምርም። መቼም የአፓርታይድ አገዛዝ ከዚህ በላይ ቁሞ ሊሄድ አይችልም። አማራው ከእንደዚህ አይነት ውርደት ራሱን  ማውጣት የሚችለው ራሱ ብቻ ነው።
አማራው ከተናቀበትና ከተዋረደበት ሕይወቱ መውጣት የሚችለው  በተደረገበት ሁሉ ከመገረምና ከመቆዘም ወጥቶ  ከዚህ በላይ መዋረድ የለም ብሎ  በአፓርታይድ አገዛዙ ላይ  ደም የሚያስተፋ ንዴትና ቁጣ ማሰማት አለበት። ደም የሚያስተፋ ንዴትና ቁጣ ካላሰማ እንደ ሰው የማይቆጥሩትን የአፓርታይድ አገዛዙ ባለቤቶችና እንደራሴዎቻቸውን ማስወገድ አይቻለውም።
አገዛዙ ኦሮሞን የሚመለከት አንድ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር ከዐቢይ አሕመድ ጀመሮ  ከላይ እስከ ታች  የተዘረጋው የአፓርታይድ አገዛዝ የሚያረግደው ዝም ቢሉ  የሚከፍሉት ዋጋ ስላለው ነው። አማራው ግን ደም የሚያስተፋ ንዴትና ቁጣ ስለማያሰማና የአፓርታይድ አገዛዙን ዋጋ ማስከፈል ባለመጀመሩ ሴት ልጆቹ በአሸባሪ ተጠልፈው ተወስደው በየቀኑ እየተደፈሩና የስነ ልቦና ጥቃት  እየደረሰባቸው ባለበት ሁኔታ  ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ ተቆጥሮ «ሴቶች በፖለቲካ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚም ከወንዶች የሚስተካከሉበት መንገድ ለመፍጠር ብልጽግና አበክሮ ይሰራል» እያለ አገዛዙ ያላግጥበታል።
ባጭሩ አማራው ሰሞኑን ካጋጠመው ብሔራዊ ሐዘን ሰልስት በኋላ አማራን የግፍ ሁሉ መሞከሪያ ያደረጉት ጠላቶቹ  ተጨማሪ ውርደት  ይዘውለት  እስኪመጡ ድረስ  ከመጠበቅ፤ መተማመን ፈጥሮ  ከደረሰበት ውርደትና ሀፍረት ለመውጣት  እንዲችል በአንድነት ደም የሚያስተፋ ንዴትና ቁጣ ማሰማት አለበት።
Filed in: Amharic