>

ሐረር "ታቦታቱን አናሳልፍም" ባሉ ሰዎች ረብሻ ተነሥቷል!!! (አደባባይ ሚዲያ)

ሐረር “ታቦታቱን አናሳልፍም” ባሉ ሰዎች ረብሻ ተነሥቷል!!!

 

አደባባይ ሚዲያ፤ 
በታሪካዊቱ የሐረር ከተማ ከትናንት የከተራው በዓል የጀመረውና መጣ ሔድ ሲል የቆየው ረብሻ ዛሬም ቀጥሎ ታቦታቱን ለማጀብ በመጣውና መንገድ ዘግተው አናሣልፍም በሚሉ ሰዎች መካከል ችግር መፈጠሩን የአካባቢው ክርስቲያኖች እየተናገሩ ነው። «የመድኃኔዓለም ታቦት በጥድፊያ ገብቷል፤ የቅዱስ ጊጎርጊስን ታቦት ማስገባት አልተቻለም፤ ታቦታቱ ታግተው እንደቆሙ ነው» ሲሉ አንድ እማኝ በፌስቡክ ገጻቸው ጽፈዋል።
በአካባቢው መከላከያ እና ፖሊስ ቢገኝም በዓሉን በጉልበት እያወኩ ያሉትን ሰዎች ሥርዓት ከማስያዝ ይልቅ ሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ አስለቃሽ ጥይት እንዲሁም መደበኛው ጥይት መተኮሳቸውን እማኞች ተናግረዋል። በተኩሱ እስካሁን ባለን መረጃ ሁለት ሰዎች መቁሰላቸው እና ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ለማወቅ ችለናል።
በቅርቡ በሐረር ከተማ በተደረገ አንድ «የሰላም ኮንፍረንስ» ላይ «ሐረር አራተኛዋ የእስልምና ቅዱስ ከተማ ናት» በሚል በከተማይቱ ይገባኛል ጥያቄ ሕዝበ ክርስቲያኑ እንግዳ እንደሆነ እና ባለቤት እንዳልሆነ ሲነገር የነበረው ሰበካ አሁን አካል ገዝቶ ለነውጥ እንደበቃ ነገሩን አስቀድመው ሲከታተሉ የነበሩ ምሁር አስረድተውናል።
«ዛሬ መንገድ ላይ ታቦታቱ እንዳይወጡ እንዳይገቡ የሚያደርገውን ከዚያ ነውጠኛ ሰበካ ጋር አስተያይቶ መረዳት ነው» ያሉት የጉዳዩ ተከታታይ «ታሪክን ለመከለስ» እና በኢትዮጵያ ውስጥ በክርስቲያኑ ብቻ የተጻፈውን ታሪክ አሽቀንጥረን ጥለን «የእኛ ታሪክ» የምንለውን አዲስ ቅጂ እንፈጥራለን የሚል ከፍ ያለ ምሁር መሰል እንቅስቀሴ በመካሔድ ላይ መሆኑን ምሁሩ አብራርተዋል።
«በርግጥ በዚህ ሁሉ ሕገ ወጥነት ውስጥ የክልሉ መንግሥት ዜጎቹን መብት ለማስጠበቅ ያሳየውን ዳተኝነት» ምሁሩ ነቅፈዋል።

በመጨረሻም አሸንፈናል….ታቦታቱ በሰላም ወደ ማደሪቸው ገብተዋል!!!

በመጨረሻም ቄሮ የተባለው አሸባሪ ቡድን በግንድና በድንጋይ መንገድ ቢዘጋም፣ሰንደቅ ዓላማችንን ቢያቃጥልም፣ንብረት ቢያወድምም፣ክርስቲያኖቸን ቢያቆስልም ታቦታት በሠላም ገብተዋል።
የሐረር ክርስቲያኖች ከከተራ እስከ ጥምቀት በቄሮ  መንገድ ቢዘገባቸውም፣በመከላከያ ኃይል አስለቃሽ ጭስ ቢተኮስባቸውም፤እየደሙና እየቆሰሉ የተዘጋውን መንገድ እያስከፈቱ የቅዱስ ገብርኤል፣የቅዱስ ጊዮርጊስ፣የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እና የቅዱስ መድሃኒዓለምን  ታቦት አጅበው መሰዋዕትነት እየከፈሉ  አስገብተዋል።የቆሰሉ ሁለት ክርስቲያኖችም ሆስፒታል ይገኛሉ።
የዘንድሮው ጥምቀት መቼም ልዩ ነው።ቢገሉንም ከትናቱ በላይ በዝተናል።የኢትዮጵያን ምድር ከትናት እስከዛሬ ሞልተናታል።ኢትዮጵያ በአረንጓዴ፤ቀይ፣ቢጫ ሰንደቃችን አሸብርቃ ውላለች።
ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን🙏
Filed in: Amharic