>

የኦሮሞ ፅንፈኞች ዘሃ ፖለቲካ እና አረመኔያዊ ገፅታው!!! (አሰፋ ሃይሉ)

የኦሮሞ ፅንፈኞች ዘሃ ፖለቲካ እና አረመኔያዊ ገፅታው!!!

አሰፋ ሃይሉ
 
(The Parasitic Revenge Politics of Today’s Oromo Extremists)
           —   ክ  ፍ  ል   :   ሁ  ለ  ት   —
ባለፈው ሳምንት መጥጥፌ የኦሮሞ….‹ዘሃ›› የሚለውን ቃል የወቅቱን የኦሮሞ ፅንፈኞች ፖለቲካ ለመግለፅ የተገለገልኩበትን አግባብ መልለፄ ይታወስልኝ፡፡ ዘሃ ጥንካሬ የሌለው፣ ራሱን ችሎ መቆም የማይችል፣ ስለዚህም እንደ ፓራሳይት ሌሎች ጠንካራ ግንዶችን ፈልጎ በእነሱ ላይ ተጠምጥሞ የሚኖር፣ ልፍስፍስ ሐረግ ነው ብያለሁ፡፡ ይህን የኦሮሞ ፅንፈኞች ዘሃዊ ባህርይ ከነአረመኔያዊ አካሄዱ ለማሳየትም – የማዕከላዊ መንግሥቱን የሲቪልና ወታደራዊ ሥልጣን ከወያኔዎች በውርስ የተላለፈላቸው የዛሬዎቹ ፅንፈኞኛ የኦሮሞ ፖለቲካ ዘዋሪዎች – የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት ተጠቅመው – በሶማሊዎች ላይ ያሳደሩትን የቆየ በቀላቸውን – እንዴት ባለ መልኩ – በሶማሊ ሕዝብና በአብዲ ኢሌ ላይ እንደተወጡት በጥቂቱ ለማስረዳት ሞክሬያለሁ፡፡
የዛሬው የኦሮሞ ፅንፈኞች ስልታዊ አካሄድ – ራሱን ችሎ የማይቆመውን በኦሮሞ ፅንፈኛ ኤሊት የሚመራውን – እና በአንድ ክልል እንደ ህዳሴ ግድብ እየተጠራቀመ ያለውን የታጠቀ ኃይል – ‹‹የራስን ዕድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል — ታላቋን ኦሮሚያ እስከ መመሥረት!›› በሚል የመጨረሻ ሕልም ሥር በድብቅና በግልፅ አሰባስቦ – እስከዚያው በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት የሲቪልና ወታደራዊ ሥልጣን ላይ ተንጠላጥሎ፣ ይህን ይቀናቀኑኛል የሚላቸውን ኃይሎችና ሕዝቦች ሁሉ አፈርድሜ እያበላ – የበቀል ረሃቡን በኢትዮጵያ ሕዝብ ኪሣራ እያስታገሠ – ወደ መጨረሻ ግቡ ለመሄድ ያለመ አረመኔያዊ አካሄድ ነው፡፡
የዚህ የዘሃ ፖለቲካ አረመኔአዊ አካሄድ አመንጪዎች ራሳቸው የኦሮሞ ፅንፈኛ ኤሊቶች ናቸው ማለት ግን አይደለም፡፡ የዘሃን ፖለቲካ ለፅንፈኛ ኦሮሞው ኃይል ያስተማሯቸው የብዙዎቹ የጊዜያችን ሀገራዊ ጠንቆች አመንጪዎች የሆኑት ወያኔዎች ናቸው፡፡ ሁላችንም እንደምናስታውሰው ከ1997ቱ ምርጫ አስቀድሞ ናዝሬት (አዳማ) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መቀመጫ እና የኦሮሚያ ዋና ከተማ  ስትደረግ – እስከ 500 ሚሊዮን ብር የፈጀ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ገንዘብ በኢንቬስትመንት ስም መሬት ላይ ተረጭቶ – የኦሮሚያ ምክር ቤት፣ የኦሮሚያ መሥሪያ ቤቶች፣ የሰማዕታትና የአባገዳ ኃውልቶች፣ ከተለያዩ ክልሎች ተዘዋውረው የሚሠሩ የኦሮሞ ሲቪል ሰርቫንቶችና ባለሥልጣናት መኖሪያዎችና ኮብራ ተሽከርካሪዎች፣ እና ሌሎች መደለያዎችና ማባበያ ጥቅማጥቅሞች ተዘርቶላቸው ነበር፡፡
የ1997ቱን ምርጫ ተከትሎ ወያኔ (ማለትም ኢህአዴግ) በዝረራ ሲሸነፍ ግን – ያ ሁሉ አዳማ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ነች ተብሎ የተዘራ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃብት እንደ አፈር ተቆጥሮ – ፊንፊኔ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ነች ብሎ ታወጀ፡፡
ያንን የፊንፊኔ አዋጅ ያስነገረው – እና ‹‹ሲጠሩት አቤት፣ ሲልኩት ወዴት›› በሚል ባህርዩ የታወቀው (እና እንደ ዘሃ የተልፈሰፈሰው) የኦሮሞው ፅንፈኛ ኃይል አልነበረም፡፡ የአዳማውን የንዋይ ርጭትና ክልላዊ ዳንኪራ ሁሉ በ24 ሰዓት ውስጥ ሠርዞ – ፊንፊኔ የኦሮሞ መቀመጫ መሆኗን ያወጀላቸው – ሞግዚታቸው (እና ፈጣሪያቸው) ወያኔ ነው፡፡ ወያኔ የፅንፈኛውን ኃይል ልብና እስትንፋስ ከነሕልሙ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ አዲስ አበባ ከዚህ በኋላ ‹‹ፊንፊኔ›› በሚል ስም የምትጠራ የናንተ መዲና ናት ሲል አበሰራቸው፡፡ አንድ እንኳ ለምን ከናዝሬት ወደ አዲስ አበባ እንዛወራለን? የያዝነው የህፃናት ዕቃ-ዕቃ ጨዋታ ነው ወይ? ብሎ የጠየቀ ህሊና ያለው ሰው ሳይገኝ… ‹‹ፊንፊኔ ኬኛ›› ብለው እየጨፈሩ መሥሪያ ቤቶቻቸውን ሁሉ አዳማ ላይ እርግፍ አድርገው አዲስ አበባ ጠቅልለው ገቡ፡፡
መጀመሪያ አዲስ አበባ እየዋሉ – ማታ በኮብራዎቻቸው አዳማ እያደሩ ጀመሩት፡፡ ቀጥለው አዲስ አበባ ውስጥም እንደ አዳማው በተመሣሣይ በመቶ ሚሊዮኖች ወጪ ተነስንሶላቸው – መኖሪያ ቤቶች፣ መሥሪያ ቤቶች፣ የኦሮሚያ ባንኮች፣ የባህል ማዕከሎችና፣ የኦሮሚያ ታፔላዎች ተገነቡላቸውና ወያኔ ራሱ እስኪገርመው ፍጥጥ ብለው ‹‹አዲስ አበባ መዲናችን ናት›› ብለው ተግተልትለው ተጠቃልለው ገቡ፡፡
እንግዲህ ‹‹ነፍጠኛ!›› የሚባል ጭራቅ በሕልማቸው ብቻ ሳይሆን በቁማቸው እንዲያቃዣቸው ሆነው በወያኔ ተጠፍጥፈው የተሠሩት እነዚህ የኦሮሞ ፅንፈኛ ኃይሎች አዲስ አበባ ገብተው አስተዳደሩን ከነመዋቅሩ የተቆጣጠሩት የአዲስ አበባ ሕዝብ መርጧቸው አልነበረም፡፡ አዲስ አበባን የሚቆጣጠር የራሳቸው ጠንካራ ሠራዊት ኖሯቸውም አይደለም፡፡ ነገር ግን – በግንቦት 1983 ‹‹ለሕዝብ ሲል በአዲስ አበባ የሚገኘውን የሬዲዮ ጣቢያ በተቆጣጠረው›› እና የመከላከያ ሠራዊቱን ከፖለቲካ ሥልጣኑ ጋር አጣምሮ በሚዘውረው – እና የኦነግን ሠራዊት ከኢትዮጵያ ጠራርጎ ካጠፋው እና እንደ እዝጌር በሚፈሩት – በወያኔ ኃይል አይዟችሁ ተብለው ነው፡፡ ወያኔ በቁጥጥሩ ሥር ባዋለው የመከላከያና ደህንነት ኃይል ተመክተው ነው፡፡ ወያኔ እንዳሻው የሚያዝበት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀብትና ገንዘብ ለእኩይ ዓላማቸው ማስፈፀሚያነት ተመድቦላቸው ነው፡፡
ሳስበው – ወያኔ ለኦሮሞ ፅንፈኞቹ – በሥጋ ብፆት እየማለ – እንዲህ ብሎ ቃልኪዳን ሳያስርላቸው የቀረ አይመስለኝም፡-
‹‹ከናዝሬት ጨፌ ኦሮሚያ ነቅላችሁ ኑ!
በአዲስ አበባ ቤተመንግሥቴን ከባችሁ ተቀመጡ!
አዲስ አበባን ልባችሁ እንደሚወደው ‹‹ፊንፊኔ››
ብላችሁ ሰይሟት! በሥጋ ብፆት እምልላችኋለሁ –
ከዛሬ ጀምሮ ቅንጅትን የመረጠችው ፊንፊኔ –
የናንተ ናት! መዲናችሁ አድርጓት! የፊንፊኔን
መዲናነት የሚቃወማችሁ ቢኖር – እርሱን ለኔ
ተዉት! ጉልበቱን ሰብሬ.. መቅኔውን በኦሮሞ
የባህል ማዕከል ጉብታ ላይ.. አፈስላችኋለሁ!››
ብሎ በሥጋ ወ ደሙ ዋስትና ሳይሰጣቸው እንደልቀረ አያጠያይቅም፡፡ ያኔ የሕዝብ ድርቅ ባጋጠመው በአናሳው የወያኔ ኃይል የተደገፈው የኦሮሞ ፅንፈኞቹ ዘሃ ፖለቲካ፣ ዛሬ ደግሞ ፊቱን ቀይሮ – ወያኔ ላለፉት 27 ዓመታት ያደረሰችብኝን በደል እበቀላለሁ ብሎ ተነስቶ አየነው፡፡
ደግሞ ይህንንም ሲያደርግ ራሱን ችሎ አይደለም፡፡ ቂምበቀሉን ለመወጣት ወያኔን ከቦ ልክ ያስገባዋል ብሎ ባመነው በሻዕቢያ ኃይል ላይ እምነቱን ጥሎ ነው፡፡ የተነጠቀውን መሬቱን ለማስመለስ ከዛሬ ነገ ወያኔን ይወጋልናል ብሎ ባመነው በአማራ ሕዝብ የደም ዋጋ እና በጥቅም በተሸበበው ሆዳሙ ብዓዴን ላይ እምነቱን ጥሎ ነው፡፡ በእነዚህ መካከል በሚፈጠረው እሣት ኦሮሚያ ቢሊሱማን አተርፋለሁ ብሎ ነው፡፡ ወያኔን ወርሶ ወደ ቤተመንግሥት ሥልጣን እንዲገባ ፕሪስክሪፕሽን በፃፈችለት በልዕለ ኃያሉ የአሜሪካ መንግሥት ዋስትና ተማምኖ ነው፡፡ ወያኔዎች በተከሉለት ከፍተኛ የወታደራዊና የደህንነት መኮንኖቹ ተማምኖ ነው፡፡ ከግር እስከ ራሱ በተቆጣጠረው የኢትዮጵያ ህዝብ የመከላከያና የፖሊስ ኃይል የኦሮሙማ አጀንዳዬን አስፈፅማለሁ ብሎ ተማምኖ ነው፡፡
እንግዲህ ይህን – በጥንካሬ ራሱን ችሎ የማይቆም – በሌሎች መስዋዕትነት የራሱን ጠባብ የዘረኝነትና የመገንጠል አጀንዳ እያስፈፀመ ያለ እና ለማስፈፀምም ያሰፈሰፈ፣ በሸፍጥና የቀውስ ትንቢት የሚመራ አረመኔያዊ አካሄድ ነው – የኦሮሞ ፅንፈኞች ዘሃ ፖለቲካ እና አረመኔያዊ ገፅታው (The Parasitic Revenge Politics of Today’s Oromo Extremists) – የሚል ስያሜ የሰጠሁት፡፡
ዛሬ ደግሞ ይኸው ዘሃ ኃይል – ከዚህ ከቡስኳው የይምሰል የተረጋጋ ፖለቲካ አካሄድ በስተጀርባ ውስጥ ውስጡን ተካርሮ በጦዘው የሀገራችን ወቅታዊ የፖለቲካና ወታደራዊ ትኩሳት ፊት – ራሱን በወያኔ ወራሽነት ባጨበት ግንባር ቀደም ሥፍራ ላይ ራሱን ችሎ ቆሞ ቢገኝ – ነገና ከነገ ወዲያ – እንደለመደው በቆመበት ኦነጋዊ አውድ – ተለይቶ ድባቅ እንደሚመታ ያወቀው ይህ የኦሮሞ ፅንፈኞች ኃይል – ራሱን የሚደብቅበት ሼል (መጠለያ ካባ) የፈለገ ይመስላል፡፡
ማንም ከማንም የማይለይበት ‹‹ብልፅግና›› የተሰኘው ማደናገሪያ ፓርቲ ያስፈለገበት ምክንያትም ይኸው የዘሃ ባህርይው የፈጠረው – እስካለና ሁሉም ዕቅዱ በእሺታ ከሠመረለት በሌሎች ትከሻ የመጨረሻ ግቡን ለማሳካት የሚሆነውን – ነገር ግን ይህ አልሆን ብሎት ሁሉም ጎራውን ቢለይ ግን – ጎራው በተደበላለቀበት ጥላ ፓርቲ ሥር – በሌሎች ተከልሎ በራሱ ላይ በተናጠል ከሚመጣበት አደጋ ለማምለጥ – ከወዲሁ ያበጀው የጋራ መደበቂያ ከለላ መሆኑ ነው እንግዲህ፡፡ ከአረመኔያዊ የፈሪዎች የዘሃ ፖለቲካ ከዚህ ክፋት በላይ ምን የተለየ ቱሩፋት ይጠበቃል? አንድዬ የኢትዮጵያ አምላክ ይወቅ፡፡ ክፍል ሶስት ይቀጥላል፡፡
አምላክ የጥበብ ማደሪያውን ኢትዮጵያን አብዝቶ ይባርክ፡፡

Filed in: Amharic