>

"...ከደምቢዶሎ በኦነግ/ቄሮ የታገቱት ተማሪዎችን «ዘር» አላቸው! አማሮች ናቸው!!!"

“…ከደምቢዶሎ በኦነግ/ቄሮ የታገቱት ተማሪዎችን «ዘር» አላቸው! አማሮች ናቸው!!!”

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ጥር 25 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ
ጠ/ሚ አብይ አህመድ ዛሬ ጥር 25 ቀን 2012 ዓም ከም/ቤቱ አባላት በማንነታቸው ስለታገቱት የአማራ ተማሪዎች ሲጠየቁ በሰጡት ምላሽ ተማሪ ማንነት የለውም ማለታቸው ይታወሳል።
ፀሀፊ አቻምየለህ ታምሩ የጠ/ሚኒስትሩን ንግግር በማውገዝ እንዲህ ብሎ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አስፍሯል:_
“ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተገደሉ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው እንኳን ማንነታቸውን ከማጣራቱ በፊት «የኦሮሞ ተማሪዎች ተገደሉብን» ብሎ መግለጫ ያወጣው የዐቢይ አሕመድ ፓርቲ ነበር።
ዛሬ ግን እሱ ከደምቢዶሎ በኦነግ/ቄሮ በአማራነታቸው ምክንያት ብቻ የተጠለፉ ተማሪዎችን «ዘር የላቸውም» እያለ ሊመጻደቅ ይቃጣዋል።
ከደምቢዶሎ በኦነግ/ቄሮ የታገቱት ተማሪዎችን «ዘር» አላቸው። አማሮች ናቸው።  አጋቾቹም ይህን ነግረውናል።  ሌላው ቢቀር የታገቱት ተማሪዎች «ዘር» ባይኖራቸውማ ኖሮ አማራ ብቻውን ልጆቼን ልቀቁ ብሎ  ሳምንት ሙሉ ሰልፍ አይወጣም ነበር።
 ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተገደሉ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው ራሱ ስለማንነታቸው መግለጫ  ሳይሰጥ  የዐቢይ ድርጅት «የኦሮሞ ተማሪዎች ተገደሉብን» ብሎ መግለጫ ያወጣው በጉዳዩ ዙሪያ ከአማራ አንጻር የኦሮሞን አንድነት ለማጠናከር ሲሆን የአማራ ተማሪዎች ከደምቢዶሎ በኦነግ/ቄሮ  ሲታገቱ  «ዘር» የላቸውም የሚለን ደግሞ በጉዳዩ ዙሪያ ከአጋቾቹ አንጻር  ከሰኔ 15 በኋላ  የበታተኑት የመሰላቸው የአማራው አንድነት መልሶ እንዳይፈጠር ነው። ከአቻም የለህ ታምሩ
Filed in: Amharic