>

የቤት ቀጋ የውጭ አልጋ !!  (ዘመድኩን በቀለ )

የቤት ቀጋ የውጭ አልጋ !!

 

   ዘመድኩን በቀለ 

•የሰፈረ 22 የ24 ቀበሌ የአዲስ አበባ ሰማእታት በረከታቸው ይደርብን። አሜን ሃሌሉያ! 

 
• ዱባዮች ሰከን በሉ። ያለልክም ከመጠን በላይ አትበጥረቁ። ሰከን በሉ። ሰከን። የምን አቅል ስቶ ማሽቃበጥ ነው? 
•••
“ አዲስ አበባ ከእንብርቷ ላይ ከቤተ መንግሥቱ ግርጌ ከመኖሪያ ቤቱና ከቢሮው አጠገብ 22 ሰፈር፣ 24 ቀበሌ ውስጥ የሪፐብሊካን ጋርድ የተባለ ገዳይ ሠራዊቱን ልኮ ሁለት ገድሎ፣ ብዙዎችን አቁስሎ አልጋ ላይ አውሎ፣ ቤተሰብ በትኖ፣ ገሚሱን ከወኅኒ ዱሎ፣ ቤተ ክርስቲያኑን አፍርሶ፣ በእሳትም አቃጥሎ፣ ጽላቶቹን ፖሊስ ጣቢያ እወስዶ እስር ቤት ከቶ ሲያበቃ፣ ቀድሞ ተደክሞበት ባለቀ ጉዳይ ከአናት ላይ ደረሶ በመጣድ ፖለቲካ ሊሠራበት ዱባይ ላይ ቤተ ክርስቲያን እንዲሠራ አስፈቀደ ብለህ ስትደሰኩር ውለህ ብታድር እኔ መች እሰማህና። ”
•••
በጥጋባቸው የተለያዩትን ሁለቱን ሲኖዶሶች አስታረቀ ብለህ ጮቤ ረግጠህ ሳታበቃ የፓርቲውን የኦህዴድን የእንባ ጠባቂ ኮሚሽን ባለሙያ ሆዳሙንና በምስር ወጥ ብኩርናውን የሸጠውን በላይን መኮንንን አሰልጥኖ ጃስ እያለ ስደተኞቹን አስታርቆ ባመጣበት በዚያው በሀገረ አማሪካ “ ተገንጣይ የኦሮሞ ቤተ ክህነት ሲኖዶስ የሚያቋቁመው ማን ሆነና ነው የማሽቃብጠው ብለህ ነው። አጎቴ። 86 ሰው በአንድ ቀን ያረደን አራጅ ለሕግ የማያቀርብ አስብቶ አራጅ፣ 17 ህጻናት ሴቶች አፍኖ ተለቀቁ፣ ተያዙ፣ ተደበቁ እያለ በወላጆች ነፍስ የሚቀልድን እንጥፍጣፊ ሰብዓዊነት የማይሰማው ጨካኝ ምን ሁነኝ ብዬ ነው የማሽቃብጥለት።
•••
በዚያ ባለፈው ሰሞን የሊቢያ ሰማእታትን አመጣለሁ ብሎ ጮቤ ካስረገጠ በኋላ አሁን ከምን እንደደረሰው እንኳ የሚጠይቅ የሚሞግት እንደሌለ አውቆ በፕሮፓጋንዳ ሆድህን የሚነፋህ ማነውና ነው እንዲህ የምታሽቃብጠው? ባለ ሾርት ሚሞሪ ስለሚበዛ እንጂ ትናንት ልሙጡን ባንዲራን ዓይኔ አይይ፣ አይመልከት ይል የነበረው ሰውዬ ዛሬ በዱባይ ምድር ንፁኋን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ምን አግኝቶ ነው የብልጽግና ፓርቲው ማጀቢያ ያደረጋት ብሎ የሚጠይቅ እንኳ የለም? ብልጽግና እኮ የየት ሀገር ፓርቲ እንደሆነ አይታወቅም። የኢትዮጵያ እንዳይባል ኢትዮጵያን የሚጠየፍ ስለሆነ አይጠቀምም። ብልጽግና ብልግና ነው ወዳጄ።
•••
እደግመዋለሁ እስከ ግንቦት ድረስ ያውም እስከዚያ ከደረስን አቢይ አህመድ በዓታ ለማርያምና ቅድስት ሥላሴ ሊያስቀድስ፣ ለማ መገርሳ ቅዳሴ ጠበል ሲያድል፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ግንቦት ልደታ ለማርያምን ዝክር ልትዘክርና ፎቶ ተነስተው ሊበትኑልህ ይችላሉ። ይሄ ስሜቱ እንደ እርያ የሆነ ህዝብ አግኝተዋል አረግው ይቀልዱበታል።
•••
እሪያ ቆዳዋ ስስ ነው ይባላል። ይበርዳትና ፀሐይ ፊት  ትቆማለች፣ ወዲያው ይሞቃትና ስትቃጠል ከጭቃ ከውኃ ትገባለች። ጭቃ ውኃውም ውስጥ ብዙ አትቆይም ቆዳዋ ስስ ስለሆነ ይበርዳትና ፀሐይ ለመሞቅ ትወጣለች፣ ፀሐዩ ሲነካት ደግሞ ወዲያው ትቃጠልና ወደ ጭቃ ውኃዋ ትመለሳለች። የእርያ እጥበት የሚባለው ለዚህ ነው። ስሜተ ስሱዎች ፀሐዩ ፕሮፓጋንዳ ሲመታን የምንቀልጥ፣ ጭቃ ውኃው ፕሮፓጋንዳ የሚያቀዘቅዘን። ገድሎህ፣ ገርፎ አስገርፎህ ሲያበቃ ሜካፑን ተቀብቶ በቴሌቭዥን በፌስ ቡክ ብቅ ብሎ ሲያደነዝዝህ፣ እትት ሲልህ ወከክ የምትል። ወንድምህን ገድሎ አንተን አቅፎ የወንድምህን ገዳይ ሊያፋልግህ ሲሞክር አደራውን ለእርሶ ሰጥቼዎታለሁ ብለህ እንድትደነዝዝ የሚያደርግህን ተሸክመህ የምትዞር ባለ ስስ ልብ እኮ ነህ። ረጋ በል እንጂ።
•••
የዓረብ ዓለሙ ጥያቄ የቆየ ነው። ባለፈው ጊዜ በዓረብ ዓለም ቤተ ክርስቲያን መሥሪያ ቦታ ተፈቀደልን ተብሎ የኤንባሲ ሠራተኞች በተገኙበት እልል ሲባል አልነበረም እንዴ? እና ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው እንደ አዲስ ለምርጫ ቅስቀሳ በሚመስል መልኩ ጠቅላዩ አስፈቀደ ተብሎ እንደ አዲስ ጮቤ የሚረገጠው? መጀመሪያ ኢትዮጵያ የተገደሉት ቤተሰቦች ፍትህ ያግኙ። ገዳዮቹን ለፍርድ አቅርብ። ከዚያ ስለ ዱባዩ እናወራለን።
•••
በዱባይ እስከዛሬ ድረስ እኮ ቅዳሴ አልተቋረጠም። ማኅሌት ሰዓታቱም አልተቋረጠም። ዝማሬ ስብከቱ አልተቋረጠም። ውለታም አትብሉ። የእህት አብያተ ክርስቲያናትን ውለታም አትርሱ እንጂ። ተው ረጋ በሉ። ከ50 በላይ የፈረሱና የተቃጠሉ አብያተ ርስቲያናት በሞሉበት ሀገርን ሳንሠራ፣ ከ10 ሺ በላይ ምዕመናን በመላ ሀገሪቱ ተፈናቅለው ከ1ሺ በላይ በሃይማኖታቸው ምክንያት በሰማዕትነት አልፈው፣ የማርያም አራስ፣ አረጋዊ ሽማግሌ ሳይቀር ተቀጥቅጦ በተገደለበት ሀገር የሟቾች አስከሬን ሳይፈርስ በምድረ አረቢያ ተፈቅዶ የቆየ ቤተ ክርስቲያን እንደ አዲስ አስፈቀደ ብላችሁ ከጣሪያ በላይ እያሽካካችሁ ባትረብሹን እላለሁ። እኔ አክባሪ ወንድማችሁ። ስላዳመጣችሁኝ አመሰግንሻለሁ።
•••
አሁን እንግዲህ ተራው የብልጽግና ፓርቲ አሽቃባጮች ኮመንት የሚሰጡበት ሰዓት ነው። እነ አቡዱልአዚዝ፣ እነ የጌታ ልጆች የእኛዎቹም አኞዎች ሲንበጫበጩብኝ ያምሹ። እኔ ዘመዴ እንደሁ ኬሬዳሽ።
•••
ሻሎም !    ሰላም !   
የካቲት 6/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic