>

በታገቱ የአማራ ልጆች ዙሪያ በመንግስት እየተሰራው ያለው ነውረኛ ድራማ ለድራማው በተመረጠችዋ ልጅ ቤተሰቦች ተጋልጧል!  (አቻምየለህ ታምሩ)

በታገቱ የአማራ ልጆች ዙሪያ በመንግስት እየተሰራው ያለው ነውረኛ ድራማ ለድራማው በተመረጠችዋ ልጅ ቤተሰቦች ተጋልጧል! 

 

አቻምየለህ ታምሩ

 
አስራት ቲቪ ዛሬ ለድራማው ከታጩት አንዷ ከሆነችውና ከታሰረችው ከቅድስት ጋሻው አበበ ቤተሰቦች ጋር ቆይታ አድርጎ ጎ እኔ ከሁለት ቀን በፊት ከውስጥ ምንጭ አገኘሁ ብዬ ያጋራሁትን (የዐቢይ አሕመድ ….  )ስክሪፕት አንድ ባንድ አረጋግጠዋል፤ በድራማ የታሰረችውን ልጃቸውን አገዛዙ እንዲፈታ ጠይቀዋል።    …..

በዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ ፍልስፍና መሰረት ስለታገቱ የአማራ ልጆች ድምጽ መሆን ሕዝብን በመንግሥት በማነሳሳት ወንጀል ያስከስላል። አቶ ታዲዮስ ታንቱ በዚህ ሳምንት ከመረጃ ቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ «ኦነግ ሸኔ ከሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶች የሚለየው ትጥቅ በመታጠቁ ብቻ ነው፣ ሁሉም ግባቸው አንድ ነው። ጫካ የገቡ ኦነጎች፣ ከምርጫ ቦርድ ፍቃድ የወሰዱ ኦነጎች፣ በመንግሥትነት የተሰየሙ ኦነጎች ብለን ልንለያቸው እንችላለን»  ብለው ነበር። አቶ ታዲዮስ እውነት አላቸው። ጫካ የገቡ ኦነጎች የአማራ ተማሪዎችን ከደምቢዲሎ ሲያግቱ  በመንግሥትነት የተሰየሙ ኦነጎች ደግሞ ጫካ የገቡ ኦነጎች ካገቷቸው ተማሪዎች ጋር በስልክ የሚገናኙ ቤተሰቦቻቸው ስለ ታገቾቹ ሁኔታ ለሜዲያ በመናገራቸው  ሕዝብን በመንግሥት ላይ አነሳሳችሁ እያሉ በአዲስ አበባ ያስራሉ። በአጋጎቹ ኦነጎችና በመንግሥትነት በተሰየሙ ኦነጎች መካከል ያለው ልዩነት አጋቾቹ ኦነጎች ጫካ መግባታቸው፤ በመንግሥትነት የተሰየሙት ደግሞ ቤተ መንግሥት መግባታቸው ነው።

ባለፈው ስላጋለጥነው የአፓርታይዱ አገዛዝ ድራማ ጉዳዩን መከታተላችንና ማጣራታችን ቀጥለናል። በዚህም መሰረት የድራማው ተዋናይ ስለተደረጉት ስለ ሁለቱ አማራ ወጣት ሴቶች የሚከተለውን ተጨማሪ መረጃ አግኝተናል።
1. ሸዋዬ ገነት ተዘራ :- ጎንደር ከተማ ልዬ ስሙ አየር ጤና የሚባል ሰፈር ትምህርት ቤት፦ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን የተማረችው በዋልያ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
2. ቅድስት ጋሻው አበበ፡-  አድራሻ ጎንደር ከተማ ልዬ ስሙ ሸዋ ዳቦ የሚባል ሰፈር ትምህርት ቤት 1-6ኛ ክፍል ሀሙሲት ከተማ ሀሙሲት 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማረችው ስትሆን  ከ7ኛ ጀምሮ ጎንደር ከተማ አየር ጤና ትምህርት ቤት የተማረች ሲሆን አሁን  ያላት የትምህርት ደረጃ 8ኛ ክፍል ናት።
እነዚህ አማራ ወጣት ሴቶች ከፀበል ተመልሰው ባሕር ዳር ዲማ ሆቴል እንዳረፉ የያዛቸው ሰው የግንቦት ሰባት/ ኢዜማ አመራር የሆነው በለጠ አማረ (ለልጆች ይበልጣል ብሎ የተዋወቃቸው) ግለሰብ ነው። ይህ ሰው ከሌሎች ደኅንነቶች ጋር በመሆን ልጆችን በማስፈራራትም፣ በማባበልም እስከ አዲስ አበባ ድረስ አብሮ መጥቶ ልጆቹ ወደ ሚያርፋበት ሆቴል ከገቡ በኋላ እሱ ወደ ባሕር ዳር መመለሱ ተረጋግጧል።
ልጆቹ ከባሕር ዳር ወደ አዲስ አበባ እንደመጡም ያረፉት ሶር አምባ ሆቴል እንደነበር ተደርሶበታል። በተጨማሪም በነበረው ስልጠና ላይም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት እና በደምቢደሎ ዪኒቨርሲቲ ምሕንድስና እንደተመደቡ የሚያሳይ ማስረጃዎች እንደሚሰራላቸው ተገልፆላቸዋል። ይህንን ትወና በድል ከተወጡትም ከፍተኛ ገንዘብና አዲስ አበባ ላይ የመኖሪያ ቤት እንደሚሰጣቸው እንዲሁም ብሔራዊ ቤተ-መንግሥት ገብተው ከዐቢይ አሕመድ ጋር በአካል እንደሚያገናኟቸው በመግለፅም ጭምር ልጆቹን ለማግባባት ተችሏል። ነገር ግን ይህን ተልዕኮ በአግባቡ የማይወጡ ከሆነ (ማለትም አማራነታችንን ተጥቅመው በአንዳድ ሰዎችና ድርጅቶች ግፊት ተሳስተናል ብለው ለመንግስት አካላት ካላስረዱ እና አርጉ የተባሉትን የማያደርጉ ከሆነ) በእነሱም ሆነ በእናቶቻቸው ሕይወትም እንደሚመጡ ሽጉጥ በማሳየት አስጠንቅቀዋቸዋል
                          *  *    *
ከሁለት ቀን በፊት  የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ በታገቱ የአማራ ልጆች ዙሪያ እየሰራ ስላለው ድራማ ከውስጥ ምንጮች ያገኘሁትን  ሚስጥራዊ መረጃ አጋርቼ ነበር። ለድራማው የተመረጡ ወጣቶች ሴቶች ሸዋዬ ገነት ተዘራ እና ቅድስት ጋሻው አበበ እንደሚባሉ፤ ልጆቹን በገንዘብና በሽጉጥ እያስፈራራ ለድራማው የመለመላቸው  የግንቦት ሰባት/ ኢዜማ ሰው የሆነው በለጠ አማረ (ለልጆች ይበልጣል ብሎ የተዋወቃቸው) የሚባል ግለሰብ እንደሆነ፤ ቅድስትና  ሸዋዬ  እድሜያቸው 18 ዓመት ሲሆን ሸዋዬ የሁለት ልጆች እናት እንደሆነችና ሁለቱም ሴቶች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንዳልሆኑ ጽፌ ነበር።
ከሁለት ቀን በፊት በለጠፍሁት መረጃ ልጆቹ ድርሰታዊ ቃላቸው በተለያዬ የመንግሥት መስሪያ ቤት እንዲቀረፅ ከተደረገ በኋላ መንግሥት ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደሚመልሳቸው ቢጠብቁም «ማጭበርበር» የሚል የክስ መዝገብ ተከፍቶባቸው፤ ማለትም «ሳይታገቱ ታግተናል ብለው እንዳጭበረበሩ እንዲሁም መንግሥትና ሕዝብን እንዳሳሳቱ» ተደርጎ እያለቀሱ ወደ እስር ቤት እንደተወረወሩ ጽፌ ነበር።
ይህን የአገዛዙን ነውረኛ ድራማ ያጋለጥነውን ሰዎች የውሸት ማስረጃ እንደለጠፍን አድርገው የዘመቱብን በጫት ኃይል  የሚተነፍሱ የአገዛዙ ቅልቦች ብቻ ሳይሆኑ  እንቆረቆራለን የሚሉ «አክቲቪስት» እና ጋዜጠኛ ነን የሚሉ ሰዎች ጭምር ነበሩ። ሆኖም ግን እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል፤ ስንቅ እና ውሸት እያደር ይቀላል እንዲሉ  አስራት ዛሬ ለድራማው ከታጩት አንዷ ከሆነችውና ከታሰረችው ከቅድስት ጋሻው አበበ ቤተሰቦች ጋር ቆይታ አድርጎ ጎ እኔ ከሁለት ቀን በፊት ከውስጥ ምንጭ አገኘሁ ብዬ ያጋራሁትን የድራማውን ስክሪፕት አንድ ባንድ አረጋግጠዋል፤ በድራማ የታሰረችውን ልጃቸውን አገዛዙ እንዲፈታ ጠይቀዋል።
እኔ በግሌ ተከታዮቼን ስለማከብር፣ የትምህርት ዝግጅቴ፣ እድሜዬ፣ ኅሊናየና  አስተዳደጌ  ስለማፈቅድ ያላረጋገጥሁት፤ ማስረጃ የማልስብበትን ነገር ይዤ ሰው ፊት አልቆምም። የኅሊና ጉዳይ፣ የአገር ነገር ግድ የሚለን ስለሆንን ከሁለት ቀን በፊት የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ በታገቱ የአማራ ልጆች ዙሪያ እየሰራ ስላለው ድራማ ያጋራሁትንና ዛሬ ለድራማው ከታጩት አንዷ በሆነችው ቤተሰቦች ያረጋገጡትን የአገዛዙ ነውረኛነት በሚመለከት የለጠፍሁትን ማስረጃም የለጠፍሁት አረጋግጬ ነበር። ወደፊትም ይህንን ነው የማደርገው።
ባጭሩ ውሸት አንጽፍም፤ አናጋራም!  ብዙ ሰው የለጠፍሁትን ማስረጃ የተጠራጠረው ሸዋዬ በ18 ዓመቷ ሁለት ልጅ ልትወልድ አትችልም ብሎ ነበር።  ከታች የምታደምጧቸው የቅድስት ጋሻው ቤተሰቦች ግን ስለ ሸዋዬ ልጆችም ይናገራሉ። የአስራትን ዘገባ ተከታተሉና የዐቢይ አሕመድን የአፓርታይድ አገዛዝ  ወንጀለኛነትና  የማይድነውን  ብአዴንን  የወንጀል ተባባሪነት ተመልከቱ!https://www.youtube.com/watch?v=Karv7dl-q0g
Filed in: Amharic