>

አማራ ሆይ አሁንም ጉድህን ስማና ላልሰማው አሰማ! (ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)

አማራ ሆይ አሁንም ጉድህን ስማና ላልሰማው አሰማ!

 

 

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

 

 

መንጋቱ ባይቀርም አሁን የምናየው ድቅድቅ ጨለማ እጅግ ያስፈራል – ብዙ ሰው ግን የተረዳው አይመስልም፡፡ ወያኔና የዶክተር አቢይ ኦነግ ይህችን አገር ወዴት እያጣደፏት እንደሆነ መገመት ባይከብድም ፈጣሪና ሕዝቧ ከተባበሩና ከተናበቡ ግን መጪው ዘመን ብሩኅ ለመሆኑ ብዙ ምልክቶችና ቀደምት ንግሮቶች አሉ፡፡ አሁን ወደነዚያ ገብቼ ሰውን ማሳነፍ አልፈልግም፡፡

ዛሬ ጧት በጆሲ ሚዲያ የሰማሁት ያልጠበቅሁት መርዶ ከመጠን ባለፈ አስደንግጦኛል፡፡ በዚህች አገር የማይሆን ነገር እንደሌለ በመሠረቱ አምናለሁ፡፡ ይህን ያህል የፈጠጠ ጉድ መኖሩን ግን አላውቅም፡፡

የአሰለጡ አቢይ ምስለኔዎችና እንደራሴዎች የሚሠሩት ጉድ ዮሴፍ ይጥና የተባለ እንደ ጥቂቶች ስለሀገሩ ወቅታዊ ጉዳይ አብዝቶ የሚብከነከን ዜጋ አንድ ዜና ሲናገር ሰማሁ፡፡ ያም ዜና የጭቃ እሾሁ አቢይ አህመድ የተባለ የመርገምት ፍሬ አማራው ላይ የጎለታቸው ታዛዦቹ ስለሚያባክኑት በጊዜው አጠራር የአማራ ክልል በጀት ነው፡፡ እነዚህ በአብዛኛው አማራ ያልሆኑና አማራን የማይወክሉ ባለሥልጣናት አዲስ አበባ እየኖሩና ባህር ዳር “እየሠሩ” በሰባት ወራት ብቻ 47 ሚሊዮን ብር ከባህር ዳር አዲስ አበባ እንደውኃ ቀጂ በየቀኑ ለሚመላለሱበት ወጪ መደረጉ ነው፡፡ ከዚህ በባዶ እግሩ ከሚሄድ ህዝብ ይህን ያህል ገንዘብ መዝረፍ ወንጀልነቱና ኃጢኣትነቱ እንዳለ ሆኖ አንድን ህዝብ ለማፈን አቢይና መሠሪዎቹ የአማራ ጠላቶች ይህን ያህል ረጂም ርቀት መጓዛቸው የሚጠቁመን ብቸኛ ቁም ነገር የአማራው ህዝብ ዛሬ ነገ ሳይል በኅቡዕ ተደራጅቶ የታሪክ ጠላቶቹን አደብ ካላስገዛ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከምድረ ገጽ ሊጠፋ እንደሚችል ነው – በሰውኛ ዕይታ፤ ሌላውን እንደሁኔታው ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ፡፡

እነዚህ የአማራ ክልል ባለሥልጣናት ለነገ ራሳቸውና ለልጆቻቸው ምንም አይጨነቁም፡፡ አሁን እያሳሰባቸው የሚገኘው ከአብይ የሚጣልላቸው ፍርፋሪ ገንዘብና ሥልጣን ነው፡፡ የኅልውና ጥያቄ ውስጥ ያለው መላው አማራ አፈናውና ድህነቱ ድንበሩን ጥሶ እልሁን ሲያስጨርሰው የሚፈጠረው አስቀያሚ ክስተት አልታያቸውም፡፡ ተመስገን ጥሩነህና ቢጤዎቹ የወያኔና የኦህዲድ ልዑካን ዛሬ ባህር ዳር ላይ በከፍተኛ ጥበቃ ቢሮ ውለው ማታ ማታና ጧት ጧት ከሸገር ባህር ዳር በአየር ይመላለሳሉ – የግፎች ሁሉ ጫፍ ነው በውነቱ፡፡ ይህ ግን እስከወዲያኛው እንደማይቀጥል እነሱ የትሮይ ፈረሶቹም ሆኑ ጠፍጥፎ የፈጠራቸው አቢይ ራሱም አሳምረው ያውቃሉ፡፡ መጥፊያቸው እንደደረሰም ይረዳሉ፡፡ ግን በጃቸው የገባችዋን ወርቃማ ዕድል እስከጥግ ለመጠቀም ባላቸው ሰውኛ ፍላጎት እንዲህ አበሳቸውን ሲያዩ ለማየት ተገደናል፡፡ ዕድል ለክፉዎችም ናት፡፡ የነዚህ አጋሰሶች የመንፈስ አባቶች እነ ሂትለርና ሙሶሊኒም እንዲህ አድርጓቸው ነበር፡፡ መጨረሻቸው ግን ያው ነው – አይሆኑ ሆኖ ከታሪክ ትቢያ ሥር መወሸቅ፡፡

በተያያዘ ከአቢይ ሰሞነኛ ንግግር ብዙ ነገር ተገንዝቤያለሁ፡፡ እንደውነቱ ስለዚህ ዘመን እንከኖች መናገር ጉንጭን ማልፋት መሆኑን እረዳለሁ፡፡ በዝምታ መጽናት ራስንም ስለሚጎዳ እንጂ በተለይ በአሁኑ ወቅት አርምሞ መልካም ነው፡፡ ብዙም ደግ ነገር ስለማይታይ እንናገር ወይ እንጻፍ ብንል ቀኑ ሙሉ አይበቃንም፡፡ ሀገር የጨረባ ተዝካር ሆና ስትታይ ዕብድን ከጤነኛ ለመለየት ይቸግርሃል፡፡ በዚህ ጊዜ ታዲያ ተነበህም ሆነ ተደምጠህ ብዙም ላትፈይድ ዝም ብለህ ወደላይ ብታንጋጥጥ የተሻለ ይመስለኛል፡፡

ለማንኛውም አቢይ የሚሠራውን ብቻ ሳይሆን የሚናገረውንም የማያውቅ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ እያስመሰከረ እንደሚገኝ በቅርቡ በኦሮምኛ ተናገረው የተባለው ቅሌታም ንግግሩ አንድ ማስረጃ ነው፡፡ በዚያ ንግግሩ ከመለስ አባቱ ብዙ ነገር መውረሱን ተረድቻለሁ፡፡ ልጅ በእግር ሲተካ ዐፅምን ከመቃብር ያላውሳል፡፡ መለሲዝም በአቢይዝም ውስጥ ነፍስ ዘርቶ ኅያውነትን አግኝቷልና ሕወሓት ደስ ይበላት፡፡ ግን የተከለችው ጠማማ እንጨት ተቆርጦ የእሳት ማገዶ ሲሆን ነበልባሉ ለርሷም እንደሚተርፍ ገና ከአሁኑ ብዙ እያየን ነውና ለዚያም ትዘጋጅ፡፡ አሁን በኦነግ እየተጎዳ ያለው አማራ ብቻ ነው ከተባለ በርግጥ ጅልነት ነው፡፡

ኢትዮጵያ የእርጉማን መፈንጫ መሆኗን ለመገንዘብ እነዚህን ሁለት በቁም የጠፉ ዜጎችን ማመሳሰል በቂ ነው – መለስንና አቢይን፡፡ መለስ መቀሌ ላይ ሄዶ በትግርኛ ምን እንዳለ ታውቃላችሁ፡፡ “እንኳን ከናንተ ተፈጠርን” በማለት የዋሃንን አነሆለለ፤ አማለላቸውም፡፡ ልብ አድርጉ – ይህን ያለው ጫካ ውስጥ እያለ ቢሆን አይገርምም – የኢትዮጵያ መሪ ሆኖ በጉልበቱ ከተሰየመ በኋላ ነው፡፡ ይህኛው የአስተሳሰብ ድውይ ደግሞ በቀደምለት ኦሮሚያ በሚባለው አንድ አካባቢ ሄዶ የሚከተለውን እንደተናገረ ቢስ አይይብን ልጅም ይውጣለትና ዶክተር አብርሃም ዓለሙ ከተረጎመው ጽሑፍ መመልከት ይቻላል፡፡ 

ሕዝቤ ሆይ!

…. አንዳንድ ሰዎች ብልጽግና ለምን ተፈጠረ? የማን ነው? ብለው ይጠይቁናል። ብልጽግና የኦሮሞ ነው፤ … ብልጽግና የኦሮሞን ጠላቶች ከስልጣን፣ ከቤተ መንግስት ለማባረር የተፈጠረ ነው። ብልጽግና ጠላቶቻችን ከዚህ በኋላ ከኛ ጋር ቁጭ ብለው በሀገሪቱ ላይ መወሰን እንዳይችሉ የተፈጠረ ነው። “ኦሮሞ የራሱን ድርጅት ገንብቶ ሀገር መምራት አይችልም፤ ሀገር መምራት የለበትም፤” የሚሉት ብልጽግናን ይሰድባሉ። ኦሮሞ ግን የብልጽግና አባት፣ የአዲስ ሃሳብ አእምሮ ባለቤት ስለሆነ የራሱን አያሳንስም፤ የራሱን አይገፋም፤ የራሱን አይጠላም። ይሁን እንጂ በሱ (ብልጽግና) ተጠቅሞ ባሌን ያለማል …. “እግዚያብሄር የሰጠንን አእምሮ ተጠቅመን በተግባር በሚታይ ስራ ሀገር ቀይረን የኦሮሞን ህዝብ ለማኩራት በልዩ ቆራጥነት ሌት ተቀን እየስራን ያለን በመሆኑ፣ በዱአችሁ አትርሱን…፤

ያለበለዚያ ይህን ከጅ ካወጣን አጥር ውስጥ ተቀምጠው እንደሚያለቅሱት ዓይነት ለቅሶ ስለሚሆን፣ ከዚህ በኋላ ለኦሮሞ ለቅሶ የማይሆንለት ስለሆነ፣ ያገኘነውን ይዘን፣ የቀረውን ሞልተን፣ ወደ ፊት መሄድ እንድንችል አንድነታችንን እንጠብቅ።…

እንግዲህ ሽሉም ገፋ፤ ቂጣውም ጠፋ፡፡ አቢይ አቢይ እያልክ ስትጃጃል የነበርክ ነፈዝ ሁላ ከዚህ መርዶ በኋላ ምን ውስጥ እንደምትገባ አንተና ሰይጣን ብቻ ናችሁ የምታውቁት፡፡ መለስ ለስትራቴጂም በሉት ለእውነት ትግሬ ውስጥ እንደተለጠፈ በዘረኝነት ደዌም እንደተመታና ሰው የመሆን ዕድል ሳያገኝ  ሕይወቱ አለፈች፡፡ ይህ ልዝብ ሰይጣንም ኦሮሞ ውስጥ እንደመዥገር እንደተጣበቀ ለማየት ያብቃህ በቅርብ ይህችን ዓለም ይሰናበታል፡፡ታላቁ የኦሮሞ ሕዝብ በተረቱ እንዲህ ይላል፤ አንሻፍፌም ቢሆን በኦሮምኛችን ላቅርበው፡-

ቆራን ጨብሲ ጀናን ጭራሮ ጨብሲቴ፤

ነዱን ገዱን ጀናን ኢልካና ጨብሲቴ፤

ኢንተላ ባለጌ ዱቢን በለሲቴ፡፡

(“እንጨት ስበሪ ብትባል ጭራሮ ለቅማ መጣች፤ ሳሚኝ ብላት ጥርሴን አወለቀች፤ ይህች ባለጌ ያሳደጋት ወፈፌ ነገሩን አበለሻሸችው፡፡” እንደማለት ነው በነፃ ትርጉም)

እነዚህ የጨብሲ ወይም የስበር ልጆችም (አቢይና ሽመልስ አብዲሣ) በጨብሲ ጀምረው በጨብሲ ሊጨርሱን ነው (ጫት የምትቅሚ ሁላ “ጨብሲ” ስትይ ምን ለማለት እንደሆነ አሁን ይግባሽ -የጫቱን ኃይል “ለመስበር” ነው ወደ ቁንድፍት ሰፈር የምትበሪው)፡፡ አቢይ ሽመልስን ይቃወመዋል ብዬ ካለፈው የእሬቻ በዓል ጀምሮ ከግማሽ ዓመት ለማይተናነስ ጊዜ ብጠብቅም እንኳንስ ሊቃወመውና ሊተቸው ይባስ ብሎና “ምን ታመጣላችሁ?” ከሚል ትዕቢትም በመነሳት ራሱ ደገመውና “የሰበሩንን ሰባበርናቸው፤ ያዋረዱንን አዋረድናቸው፤ከኛ ፈቃድም ውጪ እንዳይንቀሳቀሱ ኮደኮድናቸው” ብሎን አረፈው – በጣም የገረመኝ ሰይጣናዊ ዕብሪት ነው፤ ሳይከካ ተቦካ ዓይነት ትዕቢት – ገና ምኑን አየና? “ሙያ በልብ” ነው፡፡ ምን እንዲህ ያስቀባጥረዋል? ዝምታ ማንን ገደለ? ልብ አድርጉልኝ – ይህም ሰው የመላዋ ኢትዮጵያ መሪ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መሪ ሆኖ ግን ሽል ምንጠራ ውስጥ በመግባት ለሌሎች ሳይሆን ለኦሮሞ ብቻ የቆመ የሚያስመስል አመራር በገሃድ እያሳየ ነው – ትንሹ መለስ፡፡ “ጉድ ያለው ገንፎ አድሮ ይፋጃል” ማለት አሁን ነው ታዲያ፡፡

አንድ ነገር ብቻ ልናገር – ትግስታችሁን፡፡ ጃዋርንና አቢይን እንዲህ ያሳበዳቸው የማንነት ቀውስ ውስጥ በመዘፈቃቸውና በዚያም ላይ የተላኩበት ሥውር ዓላማ የሚያሰቃያቸው በመሆኑ ነው፡፡ 99 በመቶ እርግጠኛ ስለሆንኩበት ነገር ነው የምነግራችሁ – ስትፈልጉ ዕብድ በሉኝ – በፀጋ እቀበላለሁ፡፡

እውነተኛ ኦሮሞ እንደነሱ አያብድም፡፡ እውነተኛ ኦሮሞ እንደነሱ ይጨብጠውንና ይለቀውን፤ ይናገረውና ይሠራውን አያሳጣውም፡፡ እውነተኛ ኦሮሞ ልክ እንደእውነተኛ አማራና ትግሬ የተረጋጋ ነው፡፡ እነዚህን መሰል ዕብድ ውሾች ግን በውስጣቸው የሚያንቀዠቅዥ የሁለት ዓለም ስብዕናና በመቁሽሽ የተበከለ፣ በሥልጣን አራራ የተለከፈ፣ በገንዘብና በሀብት ፍቅር የታወረ መጥፎ ስብዕና የሚያንገላታቸው ናቸው፡፡ የራሳቸው ስብዕና የላቸውም፡፡ ለመለወጥ አፍታ አይፈጅባቸውም፡፡ በእንግሊዝኛው አጠራር They are simply vessels. ማንም ገንዘብ ያለው ሊገዛቸው የሚችል ቅራቅንቦ ናቸው፡፡አሳዛኝ ስብዕና!

ተመልከት እንግዲህ – ጃዋርም ሆነ አቢይ ኦሮሞ አይደሉም፡፡ ምንም ይሁኑ ወደዚያ አንገባም፡፡ በኦሮሞ ባህልና ቋንቋ ታሽተው ግን ወዶገብ ኦሮሞ ሆነዋል፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ከኦሮሞው በላይ ኦሮሞ መሆን ያማራቸው ተዓማኒነትን ለማግኘትና ኦሮሞ አለመሆናቸው እየታወቀባቸው ከያዙት ሥልጣንና የሥልጣን ምኞት የሚገታቸው እየመሰላቸው ነው እንዲህ ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ ለመሆን የሚሞክሩት፡፡ በፈረንጅኛው “to be catholic more than the pope.” የሚል ግሩም አባባል አለ፡፡ ከጳጳሱ በላይ ካቶሊክ ለመሆን መዳዳት ምን ዓይነት ሥነ ልቦናዊ ቀውስና ኪሣራ እንደሚያስከትል እንግዲህ አቢይንና ጃዋርን ማየት ብቻ በቂ ነው፡፡ እነዚህ የሌሊት ወፎች እዚህ ነን ሲሉ እዚህ እንዳልሆኑ በጨረፍታም ቢሆን ሲነገራቸው ይይዙትን ያሳጣቸዋል፤ እዚያ ነን ሲሉም እዚያ እንዳልሆኑ ሲጠቆምባቸው እንደዚሁ ያወራጫቸዋል – ደግሞም እጅግ ድንጉጦችና ፈሪዎችም ናቸው፡፡ ስለዚህ ቢቻላቸው ሁሉንም ለመሆን ይሞክራሉ፡፡ ያኔ የዕብድ ጠባይ ያሳያሉ፡፡ በመሠረቱና እንደውነቱ ደግሞ ሁሉንም መሆን የሚቻለው የለም፡፡ አሁንም አንድ የፈረንጅኛ አባባል ልዋስ – A friend of all is a friend of none. 

ትክክኛ አባባል ነው፡፡ በአንድ ጊዜ የሁሉም ጓደኛ መሆን አይቻልም፡፡ ዓለም የተቃርኖዎች ኅብረት ናት፡፡ ሴትና ወንድ ተፈጥሯዊ ግን መልካም የሆነ ተቃርኖ አላቸው – ትውልድን ያስቀጥላል፤ ሌላ ሌላም ጥቅም አለው፡፡ ይህን ነገር ከባለቤትህ ጋር ስትተኛ ልብ ብለህ አስተውለው፡፡ እናሳ! አቢይና ጃዋር በአንድ ወቅት ሴትም ወንድም መሆን ይችላሉ? እየጠየቅሁ ነው – መልሱልኝ፡፡ ሌሊትና ቀንስ መሆን ይችላሉ? ኢትዮጵያዊና ፀረ ኢትዮያዊስ መሆን ይችላሉ? በየትኛው ሂሳብ! አቢይ ከሚያዋጣው የኢትዮጵያዊነት ካርድ ቁልቁል ወርዶ ገና ለገና ሦስቱንም ቋንቋዎች እችላለሁ ብሎ እዚያና እዚህ የሚናገረው ቢቃረንበት በአፍ ወለምታ ብቻ የሚወሰድለት እንደማይሆን በተለይ ወዳጆቹ ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ አቢይን የመሰለ ሰው የራሱ የሆነ ፍልስፍናና ቋሚ እምነት ስለሌለው እንጂ፡፡ ሞኝነቱ ደግሞ ኦሮምኛ ሲናገር ሌላው ዜጋ ኦሮምኛ የሚችል አይመስለመውም፡፡ ይህም ከንቱነት ነው፡፡ እዚህ ላይ አንዲት ነጥብ ለማከል –  አምባገነኖች ሁሉን ዐዋቂ፣ሁሉን አድራጊ፣ ምሥኪንና ጭቁን ዜጎችን ጨምሮ ራሳቸውን የሁሉም ነገር ፈጣሪ አድርገው ስለሚመለከቱ አቢይን ፈጣሪ ካልገላገለን በስተቀር በምክርና በተግሳጽ ወይም በዕውቀትና በትምህርት አለዝባለሁ ማለት ህልም ነው፡፡ የአቢይ ለየት የሚለው ደግሞ የማስመሰል “ጥበቡ” ነው፡፡

ሀገራችንን እያጠፋት ያለው እንግዲህ ይህ ከፍ ሲል የጠቀስኩት የሰዎች ሥነ ልቦናዊ ችግር መሆኑን ልብ ማለት ይገባል፡፡ የማንነት ቀውስ ውስጥ፣ የሃይማኖት ቀውስ ውስጥ፣ የግል እምነት ቀውስ ውስጥ፣ የአስተሳሰብ ቀውስ ውስጥ፣… የተዘፈቀ ሰው እንኳንስ ሀገርን ቤተሰቡንም በቅጡ መምራት አይችልም፡፡ ሁሉ አማረሽ ገበያ ከወጣች ገበያውም ራሷም አይረጋጉም፡፡ ለዚህም ነው ዛሩ ያልሰከነው አቢይ ራሱ ፍዳውን እያዬ ሀገሪቷን መቀመቅ ሊከት ዳር ዳር እያለ የሚገኘው፡፡ ካገኛችሁት “ከመጠምጠም ማወቅ ይቅደም” በሉልኝ፡፡ ደግሞም “የጠፉህን የአበባ ተክሎች አገኘሃቸው ወይ?” ብላችሁ ጠይቁልኝ – ያን ያልበላኝን የሚያክልኝን አስመሳይ፡፡ ግዴላችሁም ግን የአራት ኪሎ ወንበር ክፍሉ ይቆጠርለትና ለሰባት ሰባቶች ጠበል ይረጭ – አንድ ሰው ወደዚያ ሲሄድ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ጠባዩ ተለውጦ ኢዲያሚንንና አፄ ቦካሣን የሚሆነው አለነገር አይደለምና!! አቢይ እኮ ዚያድባሬንና ጆሴፍ ስታሊንን ሊሆን ግፋ ቢል አንድ ቅዳሜ ብቻ ነው የቀረው፡፡ ለማንኛውም “ፈይሣ አዱኛ” ይሁነን እንጂ እንደነሱስ ከሆነ አንድ ክረምት መውጣታችንንም እንጃልን፡፡

 

 

Filed in: Amharic