>

ከእኩለ ሌሊት በፊት - የኢትዮጲያ የጦር ሥልጣን ተዋረድ...  (ዮሴፍ ተገኔ)

ከእኩለ ሌሊት በፊት – የኢትዮጲያ የጦር ሥልጣን ተዋረድ… 

 

ዮሴፍ ተገኔ
ንጉሠ ነገሥት
   የአገሪቱ ግዛት ጦር ጠቅላይ አዛዥ ነው።
ንጉሥ
    የራሱ ግዛት ጦር ጠቅላይ አዛዥ ነው።
ራስ
ፊልድ ማርሻል ሲሆን የራሱ ግዛት ጦር ወይም የንጉሠ ነገሥቱ ወይም የንጉሡ አንድ ጦር ጠቅላይ አዛዥ ነው።
ደጃዝማች
ሙሉ ጀነራል ወይም ሌተናል ጀነራል ሲሆን የግል ጦሩ ወይም የንጉሠ ነገሥቱ ወይም የንጉሡ ወይም የአንድ ራስ ክፍለ ጦር አዛዥ ነው።
•ፊታውራሪ
ሜጀር ጀነራል ሲሆን ራሱን የቻለ የአንድ ጦር ወይም የንጉሠ ነገሥቱ የንጉሡ የግሉ ወይም የደጃዝማች አንድ ክፍለጦር አዛዥ ነው።
 ( ሌላ ትርጉሜ የግንባር ቀደም ጦር አዛዥ ማለት ነው።)
ቀኛዝማች
ኮሎኔል ሲሆን የአንድ ክፍለ ጦር አዛዥ ነው። ዘማች ማለት መኮንን  ማለት ነው። ቀኛዝማች ማለት የቀኝ መኮንን ወይም የቀኝ ዘማች ማለት ነው።
ግራዝማች
ሌተናንት ኮሎኔል ወይም የግራ መኮንን (ዘማች) ሲሆን የንጉሠ ነገሥቱን፣  የራሱን፣ የደጃዝማቹን ወይም  ፊታውራሪውን አንድ ጦር ሊመራ ይችላል።
ባላምባራስ
የጥበቃ አዛዥ ነው። ትርጉሙ የምሽግ አዛዥ ማለት ሲሆን ማዕረጉም ከሻምበል እኩል ነው።
አፈንጉሥ 
ዋና ዳኛና ዓቃቤ ሕግ ነው።
አዛዥ
አጋፋሪና የርስት ጠባቂ ነው።
በጅሮንድ 
   ለግምጃ ቤት ኃላፊና ለእጅ ባለሙያዎች አለቃ የሚሰጥ የቤተመንግስት ሹመት ነው።
• ሊቀመኳስ
 ከንጉሡ የማይለዩና ተሰሚነት ያላቸው ባለሥልጣኖች ናቸው።
ሁሌም ይገርመኛል የቱ ጋር ነው የራሳችንን ጥለን የሰው ማግዘፍ የጀመርነው? የአያቶቻችን መንፈስ ይደርብንና ወደራሳችን እንመለስ ዘንድ ምኞቴ ነው!

♦ዓድዋ የጥቁር ህዝብ ኩራት

♦ዓድዋ – 124

♦የኢትዮጵያውያን ድል

Filed in: Amharic