
ሙስሊሞቹ የጦር አበጋዞች እና ዓድዋ!!!

ብሩክ አበጋዝ
በተለያዩ ጠሀፊወች በተደጋጋሚ እንዳስተዋልነው በታላቁ የአድዋ ጦርነት ለድሉ ከፍተኛውን ድርሻ ያበረከተው በራስ ሚካኤል ዓሊ ሥር የዘመተው የፈረሰኛ ጦር ነበር፤ በሌላ ግንባር ሲዋጉ የተማረኩት የጠላት ወታደሮች ሳይቀር የሚወረወረውን የፈረሰኛው ጦር ሚና እጅጉን የላቀ መሆኑን ሳይዘነጉ ቃላቸውን ሰጥተዋል። ይህ ጦር በዓድዋ ጦርነት ወቅት ከንጉሠ ነገሥቱ ምኒልክ በእስከ ቀኝ በኩል ተሰልፎ የጠላትን ጦር እንዳልነበር ያደረገ እና ውሽመጣቸውን የቆረጠ ነበር።
.
በጦርነትም ጄነራል አልበርቶኒን ሊረዳ የመጣውን በጄነራል ዳቦርሜዳ የሚመራውን ሙሉ ብርጌድ ለወሬ ነጋሪ ሳያስቀር የደመሰሰው ይኼ ፈረሰኛ ሰራዊት ነው። የጄነራል ዳቦርሜዳ ሬሳ እንኴን አልተገኘም፤ ምንም ምርኮኛም አልነበረም። እንደሚታውቀው ይኼ ጦር Proper Wollo ከሚባለው የዛሬው ደቡብ ወሎ ክፍል የተውጣጣ በአብዛኛው የእስልምና ተከታይ የነበረ የገበሬ ወታደር ሲሆን በሙስሊም የጦር አበጋዞችም ይመራ ነበር።
.

.
ክርስትያኑ ንጉሥ ነገሥት በማርያም እየማለ ተከተሉኝ ያለውን አዋጅ እና የዘመቻ ጥሪ ተቀብሎ የሃይማኖት ልዩነት ሳይገድበው ለእናት ሀገሩ እና ለራሱ ክብር ሲል የተዋደቀው ይህ ሙስሊም የእግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር የአገራችንን ዳይቨርስቲ ደመቅ አድርጎ ከሚያሳዩ ምንጊዜም ከማይረሱ ሁነቶች ውስጥ የሚመደብ እና ክብር የሚገባው ነው። ዓድዋ ከተካሄደ ከሁለት ዓመት በኋላ የትግራዩ ራስ መንገሻ ሲያምጥ ከራስ መኮነን ጦር ጋር ተቀናጅቶ በቀላሉ ራስ መንገሻን በቁጥጥር ሥር ያዋለው በእነ ራስ በሽር እና ፊታውራሪ ሥራህ ብዙ የሚመራው ይኼው ጦር ነበር።
.
እስኪ ነገ ደግሞ በራስ ወሌ ብጠል ሥር ሆነው የየጁን ሙስሊም ጦር ወደ ዓድዋ ስለአዘመቱት ሼህ ሞሀመድ ሚዐዋ እና ባላምባራስ ይማም አሙቡሎ እናወራለን።