>
5:13 pm - Monday April 19, 6404

ዳንኤል ክብረት በዳግማዊ ምኒልክ  ታሪክ ላይ ከደረሰው ይማር ይሆን? (አቻምየለህ ታምሩ)

ዳንኤል ክብረት በዳግማዊ ምኒልክ  ታሪክ ላይ ከደረሰው ይማር ይሆን? 

አቻምየለህ ታምሩ
የኢትዮጵያ እና የአማራ ጥላቻ አጥንታቸው ድረስ ዘልቆ የሚሰማቸውን ፋሽስት ወያኔዎችንና ናዚ ኦነጋውያንን እንደ ዳንኤል ክብረት ለማስታመም የሞከረ ሰው ያለ አይመስለኝም። ኦነጋውያን አባገዳዎች ከባሌ በታች ተነስተው በወረራ የሰፈሩበትን የኢትዮጵያውያን ርስት የምናባዊ አገራቸው አካል አድርገው  እንገንጠል ሲሉ ዳንኤል ክብረት ወንድሞቻችን ናችሁ እያለ የሌላቸውን ታሪክ «በጎንደር ዘመን ሳይቀር ነግሳችሁ  ነበር፤ ከግራኝ በፊት ሸዋ ነበራችሁ፤ እገሌ ንጉሥኮ  ኦሮሞ ነበር፤  ወዘተረፈ. . . » በማለት የፈጠራ ታሪክ በመጻፍ ለማባበል ብዙ ደክሟል። እነሱ ግን ምን ቢደረግላቸው ውላቸውን አይረሱምና የውሸት ታሪክ ሳይቀር እየጻፈ የሌላቸውን ታሪክ ያሸከማቸውን ዳንኤል ክብረትን  ሳያፍሩ «በሃይማኖት እኩልነት የማያምን» እና «በዜጎች መካከል  ክፍፍል እንዲፈጠር የሚሰራ» በማለት ከሰውት አረፉ። በእውነቱ ዳንኤል ክብረት መከሰስ ካለበት መከሰስ ያለበት  በዜጎች መካከል  ተፈጥሯል ብሎ የሚያስበውን መከፋፈል ያጠፋ መስሎት የውሸት ታሪክ እየጻፈ ኦሮሞ ያልነበረበትን ዘመንና  ያልሰራውን ታሪክ  እንደነበረበትና እንደሰራ አድርጎ በመጻፍ የሌላውን ታሪክና ርስት ለኦሮሞ በመስጠቱ ብቻ ነው።  ዳንኤል ክብረት በሃይማኖት እኩልነት የማያምን ተደርጎ ፈጽሞ ሊቀርብ የሚችል ሰው አይደለም።
በዳንኤል ላይ ፋሽስት ወያኔዎችና ናዚ ኦነጋውያን ባልዋለበት የሐጢዓት ክስ ያወረዱበት ከታሪክ ለመማር ባለመቻሉ ነው። ዳንኤል ኦነጋውያን ዳግማዊ ምኒልክን ለምን እንደሚጠሏቸው ቢያውቅ ኖሮ ከብዙ ስተት ይድን ነበር። ኦነጋውያን ለኢትዮጵያ፣ ለዳግማዊ ምኒልክ እና ለአማራ ሕዝብ ያላቸው ጥላቻ ወደማይድን በሽታ ደረጃ እንዳደገ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ዳግማዊ ምኒልክን ስሟቸው እንኳ ሲነሣ የሚያቃዣቸው፣ ወደእብደት ደረጃ የደረሠ ጥላቻ ያደረባቸው ንጉሡ ኢትዮጵያዊ አይደላችሁም ስላሉ አይደለም። ኦነጋውያን ንጉሥን እስኪአብዱ ድረሥ የሚጠሏቸው የኦሮሞን ሕዝብ ስለበደሉትም አይደለም። ዳግማዊ ምኒልክ “ኢይንጽሕ ደም ዘእንበለ ደም” (ደም ያለደም አይነጻም)፤ “በዘሠፈርክሙ ይሠፍሩ ለክሙ ንሕኑሐ ወዝኃዙሃ” (በሰፈሩት ቁና ይሰፈርባቸዋል”) የሚሉትን ሃይማኖታዊ መርሆዎች የሚነገሩበት ብቻ ሳይሆን ከሚተገበሩበት አገር ተወልደው ያደጉ ናቸው። ነገር ግን ዳግማዊ ምኒልክ ከትልቅነት እንጅ ከቂምና ከበቀል አልተነሡም። የኦሮሞ አባገዳዎች በአማራው ሕዝብ ላይ ላደረሱት የማይረሳ በደል፣ ላፈለሱት ርስት፣ ለዘረፉት ሐብትና ንብረት፣ 300 ዓመት ኢትዮጵያን ወደኋላ እንድትጓዝ ላደረጉት በበደሉ ቁና እኩል ሠፍረው አጸፋውን ልመልሥ አላሉም። እንዲያውም ኦሮሞዎችን ለምደዋል፣ ተዛምደናል ብለው ያማራውን ርስት እንደሠፈሩበት እንዲቀሩ ፈቀዱላቸው።
ከዳግማዊ ምኒልክ በፊት የነበሩ የኢትዮጵያ ነገሥታት ሁሉ የነበራቸው አላማ ኦሮሞን ወደመጣበት መመለስና ነባሩን ሕዝብ በርስቱ ባለቤት ማድረግ ነበር። ዐፄ ዮሐንስ ኦሮሞን በሚመለከት የነበራቸው ፖሊሲ «ጋላ ይጥፋ፤ ዱር ይስፋ» የሚል ነበር። ይህን የሚጠራጠር ቢኖር ፍቃዱ ቤኛ “Land and the Peasantry in Northern Wollo 1941-1974: Yajju and Rayya and Qobbo Awrajjas” በሚል ርዕስ ያቀረበውን ጥናት ይመልከት። ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ዮሐንስ  ሸዋን በጎበኙበት ወቅት ለንጉሥ ምኒልክ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላልፈው ነበር። ትዕዛዙም «ጋላን ወደመጣበት እንዲመለስ አድርገህ   የለወጠውን የቦታ  ስም ወደጥንት ስሙ እንዲመለስ አድርግ» የሚል ነበር። ይህን ታሪክ አለቃ አጽሜና ጉራጌው ተስፋ ገብረ ሥላሴ ዘምድረ ከብድ «አይመለል የጉራጌ ሕዝብ አጭር የታሪክ ማስታወሻ» በሚል በጻፉት የዘመን ማስታወሻዎች  መዝግበውታል። ዳግማዊ ምኒልክ ግን  የዐፄ ዮሐንስን ትዕዛዝ ተቋቁመው «ጥጃ ጠባ፤ ሆድ ገባ» በማለት የኦሮሞ ሉባዎች ነባሮቹን የኢትዮጵያ ነገዶች ወረው በመደምሰስ በያዙት የነባሮቹ ርስት ላይ የሰፈሩትን ወራሪ ኦሮሞዎች ወደ አገራችሁ ተመለሱ ሳይሉ  እንደ ተቀረው ሕዝባቸው ሁሉ የራሳቸው ሕዝብ አድርገው ባለርስት አደረጓቸው።
ምን ይሄ ብቻ! ዳግማዊ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ሲሆኑ ከሳቸው በፊት የነበሩት ነገሥታት በወረራ ከያዙት አገር ለቀው እንዲወጡ ያደረጓቸውን ኦሮሞዎች ሸዋ በማስፈር ባለርስት እንዲሆኑ እንዳደረጓቸው ኦሮሞው የዳግማዊ ምኒልክ ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ «ታሪከ ዘመን ዘ ዳግማዊ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ» በሚል በጻፉት ታሪከ ነገሥት ነግረውናል። ኦነጋውያን ግን ለኦሮሞ ይህን ሁሉ ያደረጉትን ዳግማዊ ምኒልክን አጥንታቸው ውስጥ ዘልቆ እስኪሰማቸው ድረስ ይጠሏቸዋል፣ የተለከፉበት ጥላቻቸው ሞልቶ ከመገንፈሉ የተነሳ ዳግማዊ ምኒልክ ከአረፉ ከ107 ዓመት በኋላም ለተቃውሞ በመጡ ቁጥር መፈክራቸው “ምኒልክ ይውደም” [Down Down Menilek[ ወደሚል እብደት እና ከፍተኛ የሆነ የሥነ ልቦና እና የአእምሮ በሽታ አድጓል።
ዳንኤል ኦነጋውያን ለዳግማዊ ምኒልክ የሚያሳዩት በሰውልጅ ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ወደእበደት እና በሽታ ያደገ ጥላቻ ያልተማረው ነገር ቢኖር  ኦነጋውያን ምን ቢደረግላቸው ምስጋና የማያውቁ መሆናቸውን ነው። ለጠብ የሚፈልግሕን በምንም መንገድ ወዳጅ ልታደርገው አትችልም። ኦሮሞዎች ኑ ሳይባሉ ወደምኒልክ አያት ቅድምያቶች ወደአማራው ዐጽመ ርስት የማይረሳ ወንጀል ፈጽመው መተው እንደሠፈሩ የቀሩትን ሰዎች ባለርስት ከማድረግ በላይ አንድነት ሊያመጣ የሚችል ነገር ፈጽሞ የለም። ነጻ የሚያወጣን እውነት ብቻ ነው። ውሸት  በመናገር የኦነጋውያንን ልብ መግዛት አይቻልም። በውሸት ማስታረቅ ትክክል ቢሆን ኖሮ ኦነጋውያንን ለማስታመም ያልሞከረው ነገር  በሌለው  በዳንኤል ክብረት ላይ ያሁሉ ተቃውሞ ባልተነሳበት ነበር። በመሆኑም የሚጠሉንን፣ የሚገፉንን የውሸት ታሪክ እየጻፉ ለማቀፍ  መሞከር  ትልቁ የዓለም  ቂልነት ነው። በገዛ ጠባችን ገላጋይ፣ አስታራቂ ለመሆነ መሞከር ትርፉ አሁን በዳንኤል ላይ እንደደረሠው ያለ አመድ አፋሽ መሆን  ነው። ዳንኤል ለጠብ የሚፈልጉትን የውሸት ታሪክ በመጻፍ ለማባበል መሞክር ትርፉ ምን እንደሆነ አሁን ከደረሰበት ተቃውሞ ይማራል ብለን ተሥፋ እናደርጋለን።
ሲጠቃለል ምኒልክ አባ ገዳዎች አሕመድ ግራኝ ባደከማት ኢትዮጵያ ላይ ወረራ ከፍተው የማይረሣ በደል ያደረሱትን፣ የአማራውን ርስቱን ያፈለሱትን፣ ለ400 ምዕት ዓመታት ገደማ የዘለቀ እሬሳ ያስገተቱትን፣ አገራቸውን ወደኋላ እንድትሄድ ያደረጉትን ወራሪዎች ለምደዋል፣ ተዛምደዋል ብለው በወረራ የያዙትን የአማራውን ዐፅመ ርስት ማጽናታቸው ከጥላቻ አላዳናቸውም። ለጠብ የሚፈልጉንን፣ በማባበል ለማቀፍ መሞከር፤ በገዛ ጠብ ሽማግሌ መሆን ነው። በውሸት የጸና አገርም የለም። ኢትዮጵያ እውነት ስለተነገረ የምትፈርስ አገር አይደለችም። ኢትዮጵያ የምትድነው ርስቱ የፈለሠበት ርስቱ ሲመለስ ብቻ ነው። በውሽት አገር አድናለሁ ማለት ከሁሉም የከፋ ጅልነት መሆኑን ከዳንኤል ልንማር ይገባናል።
Filed in: Amharic