>
5:28 pm - Saturday October 10, 9835

"ናይል ከግብፅ የሚመነጭ ቢሆን ኖሮ በብልቃጥ እያሸገች ትሸጥልን ነበር!!!" (ሱዳናዊ አክቲቪስት አሕመድ አሊ)

“ናይል ከግብፅ የሚመነጭ ቢሆን ኖሮ በብልቃጥ እያሸገች ትሸጥልን ነበር!!!”

ሱዳናዊ አክቲቪስት አሕመድ አሊ

* ግብፅ ማሰብ ያለበት ከኢትዮጵያ ጋር ስለምትገጥመው ጦርነት ሳይሆን ህዝቧን ስለምታጠጣው ውሀ ነው!!!

ዶክተር ፈህድ አልሺለይሚ !
በሱሌማን አብደላ
ኢትዮጵያ የተከበረች ሀገር  ናት።ኢትዮጵያ በመገናኛ ብዙኃኗ ሌሎች ሀገሮችን አትሳደብምኢትዮጵያ ድንበሯን በወታደር አጥራ የሌሎች ሀገር ህዝቦች ወደ ሃገሯ እንዳይገቡ አላደረገችም።እ.ኤ.አ. በ 1995 ኢትዮጵያ የጎረቤት ሀገሯን መሬት ወራ አልያዘችም።የግብፅ ሚዲያዎች የሚሉት ቢያጡ ኢትዮጵያ የሱዳንን መሬት ወራ ይዛለች እያሉ ነው።እውነታው አንድም መሬት አሎረረችም።ኢትዩጵያ ሀሰተኛ ብር እያተመች የሱዳንን ኢኮኖሚ አላፈራረሰችም።ኢትዩጵያ ሃብቷን ተጠቅማበሱዳን የሚገኘውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ለማስቀጠል አልሰራችምኢትዮጵያ ከሱዳን በላይ ሀብት አፍርታ ሱዳንን ድሃእንድትሆን አትፈልግም።ይሄንንም ለማድረግ ሰርታ አታቅምኢትዮጵያ የሱዳኖችን ስልጣኔና ታሪክ አልዘረፈችምኢትዮጵያ በሱዳን ላይ ማዕቀብ ተጥሎ የሱዳንን ለውዝ(ኦቾሎኒ) ስጋ ወተት ሰሊጥ ገዝታ በራሷ ስም እያሸገች አለም ህዝብ አልሸጠችም።ኢትዮጵያ በሱዳን ማዕቀብ ተጥሎ አፏን ዘግታ ዝምም አላለችም።ኢትዩጵያውያን ፍቅርንንና ወንድማማችነትን በአፋቸው ብቻ እያወሩ የሚደልሉ አይደሉም።ቃላቸውን በተግባር የሚያሳዩ ድንቅ ህዝቦች ናቸው።.ኢትዩጵያ ግድቧን እየገነባች ያለቸው የራሷን ፍላጎት ብቻ ለማርካት አደለም።የጎረቤቶቿንም ተጠቃሚነት አስባ ነው ኢትዮጵያ። እኔ በልቼ ሌላው ይራብ የምትል ስግብግብ ሀገር አደለችም።ኢትዩጵያ የሱዳንን መሬት ወራ ይዛ የኤሌክትሪክ ግድብ ማመንጫ ስትሰራ የማታማክር ሀገር አደለለችም።ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዩጵያዊያን ማንም ከመሬት ተነስቶ እንዲህ ናቸው ብሎ ሊያስተምረን አይችልም።ጠንቅቀን እናውቃቸዋለን።እኛ ወንድማማቾች ነን፦ሁላችንም የፍታሃዊዩ አልነጃሽ ልጆች ነን።ሁላችንም የአላማ ፅኑው የጥቁሩ የቢላል ልጆች ነን።እውነት ለመናገር የናይል ወንዝ ከግብፅ የሚፈልቅ ሆኖ ቢሆን፦ግብፅ በቢልቃጥ እያሸገች ነበር የምትሸጠልን።ኢትዮጵያዊያን ግን አለህን ስለሚፈሩ በቢልቃጥ እንሽጥላችሁ አላሉም።በጋራ እንጠቀም ነው ያሉት.እኛ አፍሪካዊ ነን አፍሪካዊ ወንድምና እህቶቻችንን አንሳደብም አናቋሽምም።ፍቅርንና አንድነትን ክብርን የጋራ ጥቅምን ሁሌም እናስቀድማለን።በኢትዮጵያና በሱዳን ህዝብ መሀከል ጥላቻን የምትዘሩ የግብፅ ሚዲያዎች ለምን እንደጠላችሁን እናቃለን።ግን እናተ እንደምትሉት ኢትዮጵያ የሱዳንን መሬት ወረራ አይደለችም።እውነታው ይሄ ነው።
➾ግልባጭ ለግብፅ ጋዜጠኞችና ሚዲያዎች
———
ግብፅ ማሰብ ያለበት ከኢትዮጵያ ጋር ስለምትገጥመው ጦርነት ሳይሆን ህዝቧን ስለምታጠጣው ውሀ ነው!!!
ዶክተር ፈህድ አልሺለይሚ !
ኢትዮጵያ ውሃየን ገድቤ የህዝቤን የኤሌክትሪክ መብራት ችግር መቅረፍ አለብኝ ካለች፣ ግብፅ ማሰብ ያለበት ከኢትዮጵያ ጋር እንዴት ጦርነት እገጥማለሁ ሳይሆን የ100 ሚሊዮን ህዝቤን የውሃ ፍላጎት እንዴት ማሟላት እችላለሁ የሚል መሆን አለበት።
ምክንያቱም ግብፅ የምትጠቀመው የአባይ ውሃ 85% ከኢትዮጵያ ተራሮች ስር የሚመነጭ ነው።
ሰለዚህ ግብፅ ጊዜው ሳይረፍድባት ከተቻለ የአፍሪካ ህብረትን አስተባብራ ከኢትዮጵያ ጋር
ለመስማማት መሞክር ካልሆነ ግን እዛው ግብፅ ውስጥ ውሃ ማግኝት የምትችልበትን እድሎች መፍጠር።
ከዛ ውጭ ከዛሬ 100 ዓመት በፊት ያለፈን አሮጌ ተረት ይዞ አባይ የግብፅ ነው ቢሉት አያዋጣም።
ምክንያቱም በዛን ወቅት ከኢትዮጵያ ውጭ በሙሉ የአባይ ውሃ ተጠቃሚ ሀገሮች በቅኝ ግዛት ስር የነበራችሁ ስለነበራችሁ  በ 1933 በ 1959 የነበረው የአባይ ውሃ አጠቃቀም ስምምነት ውሳኔው አልነበረም።
ታዋቂው የፓለቲካ ተንታኝና የሳዑዲ 24 ቴሌቭዢን አንጋፋ ጋዜጠኛ ዶክተር ፈህድ አልሽለይሚ።
ሞሀመድ ሀበሻ ቪዲዮ ሊንክ �.https://youtu.be/kJmjlfeBaN8
Filed in: Amharic