>

በስፋት እየተገነባ ያለው የኦሮሞ ጦር ለአዲስ አበቤውና መሠል ሕዝብ የስጋት ምንጭ ነው!!! (ኤልያስ የኔሁን ገዳሙ)

በስፋት እየተገነባ ያለው የኦሮሞ ጦር ለአዲስ አበቤውና መሠል ሕዝብ የስጋት ምንጭ ነው!!!

ኤልያስ የኔሁን ገዳሙ
– የብአዴኑ ዮሐንስ ቧ ያለው እንዳለው “ዕድል” ሳይሆን ለኔ “ዕዳ” ነው!!
… … … . የኦሮምያ ክልል በተለየ ሁኔታ ማለትም በመጠኑ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እራሱን በልዩ ኃይል እያጠናከረ ይገኛል። ብልፅግና (አዲሱ ኢህአዴግ) የኦሮሞ ነው ያለው አብይ አህመድ መራሹ መንግስት በዙር በአስርት ሺህዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ሚኒሻዎችን የምናሰለጥነው በኦሮምያ ክልል ያለውን የፀጥታ ችግር ስጋት ለመመከት ነው የሚል ነው።
የኦሮሞ ተወላጁ “ጠቅላይ” ሚኒስቴር አብይ አህመድ አዲስ አበባ የኦሮሞ ክልል አካል ናት የሚል ፅኑ አቋም አለው። በተመሳሳይ ሁኔታ የአብይ አህመድ መንግስት በልዩ ድጋፍ የሚያሰለጥነው የኦሮምያ ክልል ፖሊስ፣ የኦሮሞ ልዩ ኃይል እና ኦሮሞ ታጣቂ ሚኒሻ ኃይል ወይም በአጠቃላይ የሠራዊቱ አባላት ወጣት “ፊንፊኔ ኬኛ” በሚለው መፈክር መሰል የወረራ ራዕይ ተጠምቆ ያደገ ነው። ይህ “አዲስ አበባ የኛ ናት” የሚለው አዲስ የጦር ኃይል ነገ ላይ እንኳንና በመንግስት በኩል የሀሳብና የቁስ ድጋፍ እያገኘ አይደልምና ባያገኝም እንኳን ያለአንድም የበላይ የጦር አዛዥ ፈቃድም ቢሆን የአዲስ አበቤው የመኖር ያለመኖር ህልውና ከተማ ብሎም የመላው ኢትዮጵያዊ ዋና ተቀዳሚ መዳረሻ የሆነችውን እናት አዲስ አበባ ከተማን ጥሶ ከመውረር ወደ ኋላ አይልም።
አዎ! በስፋት እየተገነባ ያለው የኦሮሞ ጦር ለአዲስ አበቤው ዋና ተቀዳሚ  የስጋት ምንጭ ስጋት ነው። ለድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ናዝሬት እና መሠል ሕዝብን በተመሳሳይ ሁኔታ ሊያፍንና ሊያጠቃ ይችላል። ይህ ጦር “ትልቅ ዕድል” ሳይሆን #ትልቅ_ስጋት ነው። ስለሆነም #የብአዴኑ ሠው #ዮሐንስ_ቧያለው ዕድል ነው እንዳለው ሳይሆን ዕዳ ነው።
እንደሕዝብ አቅም ያለው ሁሉ እንደሀገር ከወዲሁ ያስብ። እያንዳንዱ ሽርፍራፊ ጊዜ አይባክን። ይኸው ነው።
Filed in: Amharic