>
1:56 pm - Monday January 30, 2023

"ፋኖ የሚባል መዋቅር የገባበት ገብቼ አጠፋዋለሁ !!!" የአማራ ክልል ፕሬዝደንት ተመስገን ጥሩነህ (በሃብታሙ አያሌው)

ፋኖ የሚባል መዋቅር የገባበት ገብቼ አጠፋዋለሁ !!!”

የአማራ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከተናገሩት፡፡
በሃብታሙ አያሌው 
በአጠቃላይ በሃገሪቱ ውስጥ ኢመደበኛ አደረጃጀት እንዳለ ግልፅ ነው:: ፋኖ የሚባለው ኢመደበኛ አደረጃጀት አማራ ክልል እንዳለ ሁሉ ቄሮ የሚባል ኢመደበኛ አደረጃጀት ደግሞ ኦሮሚያ ላይ ይገኛል: የቅርብ ጊዜ የጠቅላይ ሚንስትሩን ንግግር ብናስታውስ ቄሮ የትግሉ brain ነው የዚህ ለውጥ ውጤትና ባለቤት ነው ይህ መንግስት የናንተው ነው እናንተ ባለቤት ናችሁ የሚል ኢመደበኛ አደረጃጀትን ከጠቅላዮ እስከ ታችኛው አመራር ተገቢ እውቅና ሰጥተው እንደውም ይባስ ብሎ መስከረም ላይ የኢሬቻ በአል በሚከበርበት ወቅት እነዚህ ቄሮዎችንና እነሱን እንመራለን የሚሉትን አካላት ሰብስበው ትጥቅ ሰጥተው ወታደር የሚጠቀምበትን ሬድዮ ሳይቀር ሰጥተው የአዲስ አበባ ኢሬቻን በአል ስርዓት አስከባሪ ቄሮ ነው ብለው ከመንግስት ደህንነትና ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ሲሰሩ ነበር::
እኔ ግራ የገባኝ የፌደራል መንግስት ደህንነትና መከላከያ የምንለው አካል በሙሉ ቄሮ ሲባል ልክ እንደ መደበኛ አደረጃጀት ቆጥሮ ከመንግስት ጋር ይሰራል ይላል ፋኖ የሚባለው ሲነሳ ኢመደበኛ አደረጃጀት ነው ሽፍታ ነው ወዘተ የሚል ምክንያት ያመጡና የተቀናጀ ጥቃት ይፈፀምባቸዋል:: የ ኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሸመልስ አብዲሳ ቄሮን እመራዋለሁ የሚለውን ጃዋርን የ ኦሮሞ ህዝብ አይን ነው ብለው ነው የሚጠሩት:: ጃዋር ደግሞ በአደባባይ በመጪው ምርጫ ብንሸነፍ እንኳን ቄሮን በተሟላ ሁኔታ አዘጋጅተነዋል እያለ በ አደባባይ ሲናገር ሰምተናል:: ይህ በሆነበት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ፋኖ የሚባል መዋቅር የገባበት ገብቼ አጠፋዋለሁ የሚል ዘመቻቸው ምን አስበው ነው ምን ፈልገው ነው የሚለው በፍጹም ግልፅ አይደለም::
ኢመደበኛ አደረጃጀት በሃገሪቱ ውስጥ አያስፈልግም ከሆነ ይህ ሲባል የነበረ ነው:: ሃገሪቱ ውስጥ ያለው መደበኛ አደረጃጀት ፍትሃዊ ይሁን መክላከያውንና ደህንነቱ በአንድ ብሄር ጠቅሎ መቆጣጠር ይቁም ከዛ በኃላ በፖሊስ ላይ በመከላከያ ላይ በደህንነቱ ላይ ህዝቡ እምነት ይጣልበትና ሀገሪቱን መደበኛ አደረጃጀት ይምራው ተባለ ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ አይደሉም:: ወደ 31 ዙር የሚጠጋ ልዮ ሃይል ኦሮሚያ አሰልጥኖ አማራ ክልል ለምን አንድ ዙር ስልጠና ሰጠ ነው:: ይህ ስንቶች ለሞት እንዳበቃ ግልፅ ነው:: አማራ ክልል ላይ በማንኛውም ጊዜ ሆን ብሎ በተገኘው አጋጣሚ ለመበታተን ይህን ተልእኮ ለማስፈጸም የሚችሉ አመራር አስቀድሞ ማምጣት ነው:: በነገራችን ላይ ጠቅላይ ሚንስትሩ መከላከያንም ደህንነትንም ማዘዝ አይጠበቅባቸውም:: ፋኖን ከ አማራ ክልል ማጥፋት ከተፈለገ አቶ ተመስገን ጥሩነህ የሚሰጡት ትዛዝ በቂ ነው:: consequence ወይም ውጤቱ ፋኖን ማጥፋት ይቻላል ወይ የሚለው ሌላ ነገር ነው:: ስለዚህ ለምን double standard ይሆናል ነው :: Double standard የሚል ቀርቶ ዘርማ ፋኖ ቄሮ የሚል ኢመደበኛ አደረጃጀት አያስፈልግም ከተባለ በመላ ሃገሪቱ ይህ ኢመደበኛ አደረጃጀት በሁሉም ቦታ ላይ አያስፈልግም ብለህ ትወስናለህ:: ጠቅላይ ሚንስትር ሁነህ በተቀመጥክበት ወንበር ቄሮ እያልክ አመስግነህ ስታበቃ ፋኖ የሚባለውን በያሉበት እያደንክ ለመግደል ተመስገን ጥሩነህን አይነት ሰው አማራ ክልል ፕሬዝዳንት አድርገህ ታስቀምጣለህ:: ጥያቄው ይህ ውጤት ያመጣል ወይ ነው:: ውጤቱ ለክልሉ ህዝብ የምናየውን mess ነው የሚያመጣው::
ይህን ሃሳብ የሰጠሁት ዛሬ አቶ ተመስገን ጥሩነህ እየተናገሩ ካሉት በመነሳት ነው:: በ አንድ በኩል ፋኖ ብለው ሊጣሩ ይፈልጋሉ በሌላ በኩል ደግሞ ፋኖን አጠፋለሁ ብለው ይላሉ:: ይህ typical የተለመደው የኢህአዲግ መለያ character ነው:: ለያይተህ ከፋፍለህ እንዴት አድርጌ ልምታ ነው:: ነገሩ በጣም ያሳዝናል:: ስለተፈጠረው ዝርዝር ጉዳት ወደፊት በዝርዝር እመለስበታለሁ::
Filed in: Amharic