>

ሕይወቴን ውሰድና - ሞትህን አቀብለኝ! ዮሐንስ መኮንን

ሕይወቴን ውሰድና – ሞትህን አቀብለኝ!

 

 

ዮሐንስ መኮንን
ቢቢሲ እንደዘገበው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በጣልያን ብቻ ከ50 በላይ ቀሳውስት ሕይወታቸውን አጥተዋል። የአንደኛው ካህን ህልፈተ ሕይወት ግን ልብ ይነካል።አባ ጁሴፔ ቤራርዴሊ ይባላሉ።
በጣልያኗ ካስኒጎ ከተማ ሊቀ ካህን ሲሆኑ በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው ሎቬሬ ሆስፒታል የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነበር።
 በቫይረሱ በደረሰባቸውከፍተኛ ጉዳት ምክንያት መተንፈስ በመቸገራቸው የሚያገለግሉባት ቤተክርስቲያን አጥቢያ ምእመናን በማዋጣት የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያ (respirator) ገዝተው ሆስፒታል ያመጡላቸዋል።ሐኪሞቹ እስትንፋስ በመስጠት ሕይወት የሚቀጥለውን የመተንፈሻ መሣሪያ አባ ቤራርዴሊ ሊቀጥሉላቸው ሲሉ ካህኑ “አሻፈረኝ” ይላሉ። ምክንያታቸውን ሲጠየቁ “ከእኔ ይልቅ ወጣት ለሆነው ታካሚ ስጡት” በማለት እምቢ ይላሉ። የሚገርመው ነገር አባ ቤራርዴሊ ከዚህ ቀደም ዐይተውት ለማያውቁት፣ ዘሩንም ሆነ ሃይማኖቱን ለማይለዩት ታማሚ ነው “ሕይወቴን ውሰድ እናሞትህን አቀብለኝ” ያሉት።በትእዛዛቸውም መሠረት ከምእመናን ተገዝቶላቸው የመጣላቸውን ብቸኛውን የመተንፈሻ መሣሪያ ሐኪሞቹ ለወጣቱ ታካሚ ይሰጡታል። አባ ጁሴፔ ቤራርዴሊም በዚሁ ሆስፒታል በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል።
ብዙዎቻችን ኖረን እንሞታለን። ጥቂቶች ደግሞ ሞተው ይኖራሉ። የአባ ቤራርዴሊን የመሠሉ ታሪኮች በብዙ መቶ አመታት መካከል አንዴ የሚተረኩ እንጂ የአዘቦት ወጎች አይደሉም። በርካቶች የፈጣሪን ቃል ያነባሉ። አንዳንዶች ደግሞ ቃሉን ይሰብኩታል። እጅግ ጥቂቶች ግን ቃሉን ይኖሩታል።”እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል” (1 ዮሐንስ 3 ፥16)
– እጆቻችንንበሳሙና እንታጠብ
– ከመተፋፈግ እንራቅ
Filed in: Amharic