>

ጋዜጠኛ ፍቃዱ ከእስር እንዲለቀቅ መወሰኑን ጠቅላይ ዐቃቢ ሕጓ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ!!! (ህብር ራድዮ)

ጋዜጠኛ ፍቃዱ ከእስር እንዲለቀቅ መወሰኑን ጠቅላይ ዐቃቢ ሕጓ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ!!!

 

ህብር ራድዮ
የኮሮና ወረርሽኝን ለመግታት ለ4011 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ!!!
 
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በጠራው በዚህ መግለጫ ላይ ወ/ሮ አዳነች “አንድ ጋዜጠኛ ከዚህ በፊት በምህርት አጠቃላይ የሀገራችን ጋዜጠኞች በሚታዩበት ሰዓት ጉዳዩ አልታየም ነበር በውጭ ቆይቶ በኃላ ወደሀገር ውስጥ ሲመጣ ተፈርዶበት ማረሚያ ቤት ውስጥ ነው ያለው እስካሁን ድረስ ባለው የመረጃ ማጥራት ሂደት የቆየ ነው ከለውጡ በኃላ ነው ፍርዱ የተወሰነበት፣ ስለዚህ ይሄም ጋዜጠኛ ታይቶ እንዲወጣ፣ ይቅርታ የተደረገበት ሁኔታ አለ። በቅድሙ አንድ አመት የቀራቸው የሚለው ውስጥ ስለማይካተት ነው የሱን ለብቻው ልገልፅላችሁ የፈለኩት። ተፈርዶባታል ከአንድ ዓመት ያህል በማረሚያ ቤት ቆይቷል ስለዚህ በቀሪው ሌሎች የሀገራችን ጋዜጠኞች ባየንበት ማዕቀፍ መታየት ስላለበት የሱም ‘ፍቃዱ ማህተመወርቅ’ እንዲታይ የተወሰነበት ሁኔታ አለ።”
ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማህተመወርቅ ወደ እስር ቤት ከመግባቱ በፊት ሕወሓት ነጻ ፕሬሱን ለማዳከም በግብር ስም የከፈተበት ክስ ውድቅ እንዲሆን  ስድስት ዓመት ከመፈረዱ ዋዜማ ቃሌ በሚል አቤት ብሎ ሰሚ ማጣቱ ይታወሳል።
—-
የኮሮና ወረርሽኝን ለመግታት ለ4011 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ።
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በፌደራል ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ለ4011 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንደሚፈቱ ጠቅላይ ዓቃቢተ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።
በይቅርታው የተካተቱ ታራሚዎች
1ኛ. እስከ 3 ዓመት የሚደርስ ቀላል እስራት የተፈረደባቸው ታራሚዎች
2ኛ. በማረሚያ ቤት ሆነው አንድ ዓመት የአመክሮ ጊዜ የሚቀራቸው ታራሚዎች
3ኛ. በግድያ ወንጀል ያልተከከሰሱ የሚያጠቡ እና ነፍሰ-ጡር እናት ታራሚዎች
4ኛ. ከግድያ በመለስ የተለያዩ ወንጀሎች ውስጥ የተሳተፉ የውጭ ሀገር ዜጎች እንዲለቀቁ እና ወደ የመጡበት ሀገሮች እንዲላኩ መወሰኑን ጠቅላይ ዓቃቢተ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል።
በይቅርታው የተካተቱት ታራሚዎች በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስር ባሉ አምስት ማረሚያ ቤቶች ማለትም በቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት፣ ቂሊንጦ፣ ሸዋ ሮቢት፣ ዝዋይ እና ድሬድዋ የሚገኙ ታራሚዎች ናቸው።
Filed in: Amharic