>

"የብአዴን አመራሮች እንኩቶ ናቸዉ!!!" (ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ)

“የብአዴን አመራሮች እንኩቶ ናቸዉ!!!”

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ
——
ክልሎች በገንዘባቸው ከፌደራል ክልል መሳሪያ ይገዛሉ። አማራ ክልል ሲጠይቅ ግን ትናንት የህውሃት፣ ዛሬ የኦሮሞ ጀኔራሎች ያደናቅፋሉ !
ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ
እስኪ አማራን በተመለከተ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ምን እየሰራችሁ ነው? በሏቸው የአማራን ከፍተኛ አመራሮች። አንድም መልስ የላቸውም። ለዚህ መልስ አለኝ የሚል አመራር ካለ አምጡትና ከእኔ ጋር ይሟገት። እነሱ ማለቃቀስ ብቻ ነው ስራቸው። እነዚህን አቅመ ቢስ አመራሮች እንኩቶ ያልኳቸውም ለዚህ ነው። እንኩቶ ማለትም የማይረባ፣ የወደቀ፣ የተጣለ ማለት ነው።
ክልሎች በገንዘባቸው ከፌደራል ክልል መሳሪያ ይገዛሉ። አማራ ክልል ሲጠይቅ ግን ትናንት የህውሃት፣ ዛሬ የኦሮሞ ጀኔራሎች ያደናቅፋሉ። የአማራ ወኪል ነኝ የሚለው አመራር ለምንድን ነው የሃይል ሚዛንህን ያጣህ? በሉት መልስ የለውም። “ኦሮሚያ እና ትግራይ በ50 ሺህ የሚቆጠር ልዩ ሃይል እያሰለጠኑ የሃይል ሚዛናቸውን ሲያሳድጉ፣ አማራ ሁለት ዙር ላይ ቁሟል” ለምን ሆነ? በሏቸው። ለዚህም መልስ የላቸውም።
ህውሃት ለኢትዮጵያ በተለይም ለአማራ ክፉ ቀን ነው የሚመኘው። በሀገሪቱ ችግር ከተፈጠረና ከቁጥጥር ውጭ ከሆነ ተመልሼ ወደ ስልጣን እወጣለሁ የሚል ተስፋ አለው። እኛ የአማራን ህዝብ በአጭር ጊዜ ውስጥም ቢሆን ዳር እስከ ዳር አሰልጥነነዋል። ጠላትን እንዴት መቁረጥና መመከት እንዳለበትም አስረድተነዋል። ህውሃት የሚያውቀው አማራ ግን እነ በረከት ስምዖን የተጫወቱበትን ብቻ በመሆኑ፣ ተስፋው ሰፊ ነው። አይሳካለትም እንጂ!
አሁን ያንን አዚም ቢያንስ በህዝቡ ደረጃ ቀይረነዋል። ያልተለወጠው አመራሩ ብቻ ነው። ህዝቡም አመራሩ መፍትሔ ያመጣልኛል የሚል ተስፋ የለውም። ተስፋው በራሱና በልጆቹ ብቻ ነው። የኦሮሞም፣ የትግራይም ፕለቲካ አማራን በማዳከም የተንጠለጠለ ነው። የኦሮሞ ፖለቲካ አንድም ሀገራዊ ጠብታ የለውም። ሁሉም ነገራቸው አድሏዊ ነው። ኦሮሚያ ለ30ኛ ዙር ልዩ ሃይል ሲያስመርቅ ያጨበጭባሉ። አማራ ሁለት ዙር ብቻ ልዩ ሃይል ሲያሰለጥን ግን ከዶክተር አብይ እስከ ተራው ግለሰብ ማለቃቀስ ጀመሩ።
ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ በአውሎ ሚድያ ቆይታ
Filed in: Amharic