>
7:34 pm - Tuesday January 31, 2023

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ !!

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ !!

 
ጀግናው የአማራ ህዝብ ሆይ!
የአማራ ፋኖ ጎንደርም ሆነ መላው የአማራ ምድር ሰላም እንዲሆን ብሎም እንዲበለጽግ አጥብቆ ይሻል፡፡ በዚህም ጉዳይ ከማንኛውም ድርጅት ጋር ተባብሮ መስራት ይፈልጋል፡፡
“አያ ጅቦ ጅቦ ሳታማኽኝ ብለኝ” ብለህ እንደተረከው አምጠህ የወለድከውን ደም መላሽ ልጅህን ዛሬ ጎንደር ላይ ነገ ደግሞ መላው አማራ ምድር ላይ በውሸት ክስ አማሃይተው ሊበሉት ያሰፈሰፉ ጅቦችን አትኩረህ ተመልከት!
ፋኖ አማራ ከመላው ህዝባችን ጎን በመሳተፍ በገጠርና በከተማ ላለፉት 27 ዓመታት ተጭኖ የነበረውን የመከራ ቀንበር በከፊልም ቢሆን እንደቀለበሰ ያበረከተው መራር ተጋድሎ ታሪክ ምንጊዜም የሚዘክረው ሀቅ ነው፡፡
ሀገራዊ ለውጥ ተካሂዶ የህዝባችን መሰረታዊ ጥያቄዎች ይመለሳሉ፡፡ የጠላት ጥቃትና ወረራ ይቆማል የሚል ተስፋ የነበረን ቢሆንም ራሱን የቅማንት ኮሚቴ ብሎ የሚጠራው የትህነግ/ህውሐት ቅጥረኛ ቡድን በአማራ ህዝብ ላይ ዘርን መሰረት ያደረገ ጦርነት በህዝባችን ላይ ለመክፈቱ ለአንድ ዓመት ያህል የቡድኑን ጥቃት በመቀልበስና ህዝባችን በመጠበቅ የአካባቢውን ሁለንተናዊ ሳላማዊ እንቅስቃሴ ለመደገፍ ዘርፈ ብዙ ስኬቶችን ማስገኘት ችሏል፡፡ በዚህም መላው ህዝባችን በራሳችን የጦር መሳሪያ ውድ ህይወታችንን ቤዛ አድርገን እየሰጠነው መሆኑን በሚገባ በመረዳት በፍቅርና በስስት አቅፎ ይዞናል፡፡
ሆኖም ግን ፋኖ አማራ ለአማራ ህዝብና መንግስት ተጨማሪ አቅም መሆኑን የተረዱ የውጭና የውስጥ ጠላቶች ቀደም ሲል የህውሐት/ትህነግ ርዝራዥ ህዋሶች ፋኖ ላይ አሻጥርና ሴራ መስራት ቢቀጥሉም በህዝባችን መልካም መረዳትና በፋኖ አማራ ጥንካሬ እየተመከተ ቆይቶል፡፡ ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጀግኖች አርበኞችና መሪዎቻችን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ለመሰንዘር መንቀሳቀስ ተጀመረ፡፡ በተለይ በአርበኛ መሳፍንት ተስፋ በአርበኛ ብርሃኑ ነጋና በተከታዩቻቸው ላይ በግልጽ ወታደራዊ ርምጃ ተሞከረ፡፡
ጉዳዩ በሰላማዊ መንገድ በውይይት እንዲፈታ ያደረግነው ተማጽኖ ጆሮ ዳባ ልበስ ተባለ፡፡
መጋቢት 10/2012 ዓ.ም ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ በሰልፍ ለመቃወም የወጡ የጎንደር ከተማ አራት ወጣቶች በቀጥታ በጥይት ተመተው ወደቁ፡፡ በተለምዶ ሸዋ ዳቦ አካባቢ ይህን ብጥብጥ ተገን አድርገው ማንነታቸው በውል ያልታወቀ ሃይሎች የትህነግ ተቀጥላዎች ከስፍራው የነበሩ ወጣቶችን እየበተኑ የነበረው የመከላከያ ሰራዊት ላይ ፋኖ በመምሰል ርምጃ ወሰዱ፡፡ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ራሱን ቅማንት ኮሚቴ ብሎ የሚጠራው ቡድን ጥቃት ሰነዘረ የሚል መረጃ ለፋኖ ስለደረሰው ችግሩን ለመቆጣጠር ወደ
አካባቢው በመዝለቅ ያጣራን ሲሆን ጥቃት አድራሾች ከስፍራው ተሰውረዋል ስለተባለ፡፡ ሁሉም ኃይላችን ወደየ መኖሪያ ቤቱ ሲገባ የሀገሪቱ ጦር ሰራዊት ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ጠዋት ከባድ መሳሪያዎችን ዲሽቃ፤አርቢጅ፤ መትረጊስ ስናይፐር ጨምሮ ከፍተኛ የአውዳሚነት መጠን ያላቸው ቦንቦች አገር ሰላም ብሎ እረፍት ላይ በነበረው የጎንደር ከተማ ሰላማዊ ህዝብ ላይ ጭምር ሲያዘንብ አድሯል፡፡ ከዚህ ደሃ ህዝብ በሚሰበሰብ ግብር ሀገር ይጠበቅበታል ተብሎ የተገዛን የጦር መሳሪ ለህዝብ መጨፍጨፊያና ለሀገር ማፍረሻ በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ላይ ጥቅም ላይ ሲውል ከጣሊያን ቀጥሎ ይህ የመጀመሪያው ነው፡፡
በዚህ ጥቃትም ሰላማዊ ዜጎች የህይወትና የአካል ጉዳት ሰለባ ሆነዋል፡፡ በንብረትና አጠቃላይ የከተማውን እንቅስቃሴና ገጽታም ጎድቶታል፡፡ የፈራረሱ ቤቶችም አሉ፡፡
በድርጊቱም መላው ህዝባችን ከሀገር ውስጥና ውጭ ያለው በከፍተኛ ሁኔታ አስቆጥቷል፡፡ በዚህ ድርጊት ህዝባችን ይቆጣ እንጅ በመንግስት ስልጣን የተደላደሉ ሀገር እንዲፈርስ አማራን ለማዳከም ተልዕኮ ያላቸው ኃይሎች እኩይ አላማቸውን ለማስፈጸም ሳይፈሩ ታትረው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ መጋቢት 15/2012 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ጸጥታ ም/ቤት ስም የተሰጠው የመንግስት የአቋም መግለጫ ማን ለማን በቅጥረኝነት እንደሚሰራ ወለል አድርጎ አሳይቷል፡፡
“ከምግባሩ ንግግሩ” እንዲሉ ፋኖ ለከተማው ህዝብና ለአካባቢው ገበሬ እንዲሁም ለመንግስት የጸጥታ መዋቅር ከፍተኛ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ በመካድ በሬ ወለደ ውንጀላ ውስጥ ገብቷል፡፡ ፋኖ ሌቦችን በተመለከተ በቅርቡ ለጎንደር ጥምቀት ክብረ-በዓል ለስራ የመጣን ግምቱ 2 ሚሊዬን የሚጠጋ ንብረትነቱ የአማራ ቴሌቭዥን የሆነ የቀረጻ ካሜራ ተሰረቅን ባላችሁበት ቅጽበት ከገባበት ገብተን የጎንደር ከተማ ከንቲባ በተገኙበት ለጋዜጠኞች ቡድን ማስረከባችን ይታወቃል፡ ፡ የተሰረቁ በርካታ ንብረቶች ይዘን ለህግና ለባለቤቱ አስረክበናል፡፡ ከባህር ዳር ተሰርቃ የመጣች መኪናም ፋኖ እንደያዛት ህዝባችን ያውቃል፡፡ የአማራ ፋኖ ኃይል የጦር መሳሪያ ይዞ እየራበው ሌባን የሚያሳድድ ሃቀኛ ድርጅት ነው፡፡
“ማሞ ሌላ መታወቂያው ሌላ” ይሉ ዘንድ ነጭን ጥቁር ብለን እናሳምን ማለት የአማራ የኢት/ያን ህዝብ ከመናቅ ሌላ ምንም ሊባል አይችልም፡፡ የዚህ ጉዳይ አቅራቢዎች የመጀመሪያ ተልዕኮ ጎንደር ከተማና አካባቢውን ያላግባብ ለህውሐት/ትህነግ ቅጥረኛ ቅማንት ኮሚቴ የማስረከብ ሴራ መሆኑን መላው ህዝባችን ይረዳልን፡፡
ፋኖ ይህን ሴራ አስቀድሞ በመረዳቱ አሻጥራቸውን እንዲያቆሙ በውይይት ለመፍታት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ ኩሩው እና ጀግናው የአማራ ህዝብ ሆይ በአማራ ክልል አንዳንድ አመራሮች የውሸት ክስ ተመስርቶብን የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የክልሉ ልዩ ኃይል በፋኖ ስም ለአማራ ተቆርቋሪ የሆኑ ልጆችህን የቁርጥ ቀን መከታዎችን ሊበላብህ በርህ ድረስ ተገትሯል፡፡ ራሱን የቅማንት ኮሚቴ የሚለው ቡድን ደግሞ የከተማዋን ምዕራባዊ ክፍል እንዲቆጣጠር የዘመቻው አካል ሆኗል፡፡ ፋኖ አማራም በጀግንነት ለመፋለም በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ ለአማራነት መታገል ምን እንደሚመስል ለቀጣዩ ትውልድ ለማሳየት ፍጹም በሆነ ልበ-ሙሉነት የመጀመሪያዋን የጥይት ድምጽ እየተጠባበቅን እንገኛለን፡፡ በአልሞት ባይ ተጋዳዩነት ተብሎ በሚደረግ ጦርነት ውስጥ ለሚጠፋው የሰውም ሆነ የንብረት ጥፋት ተጠያቂው መንግስት ብቻ እንደሆነ ህዝባችን
እንዲገነዘብልን በጥብቅ እንሻለን፡፡
ህዝባችን ሆይ!
ለጠላቶችህ ፕሮፖጋንዳ ጆሮህን ሳትሰጥ አንተ የምትመክረንን እየተቀበልን የምንሰራ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ለአማራ ልዩ ኃይልና የጸጥታ መዋቅር ትላንት ጠላቶቻችን ከውስጥ በአሻጥር ከውጭ በጦር በሰራቫ፤ በጭልጋና በቡሃና ጉዳት ሲደርስብህ ከሁሉም ቀድሞ የደረሰውና አብሮህ የተዋደቀው የአማራ ፋኖ መሆኑን ታውቃለህ፡፡
ለአማራ ልዩ ኃይል፤ ሚሊሻ፤ ፖሊስ እና የአማራ ተወላጅ፤ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ዛሬ በመንግስት አሻጥረኞችና ጥገኞች ሳትገፋ ከህዝብህና ከፋኖ አማራ ጎን እንድትሰለፍ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡  የቅርብ የጋራ ጠላት ጎንደር ከተማ ቁስቋም ጦር ሰብቆ በተቀመጠበት ሁኔታ ታሪካዊ ስህተት ውስጥ እንደማትገባ ተስፋ እናደርጋለን፡፡
እኛ ወንድሞቻችሁ ፋኖዎች ወደ ልዩ ኃይል ወንድሞቻችን እና ሌሎች የአማራ የጸጥታ ኃይሎች አንድ ጥይት እንደማንተኩስ በዚህ አጋጣሚ እናረጋግጣለን፡፡
በመንግስት መግለጫ የጎንደር ከተማ እና አካባቢው ህዝብን የሚያግተው፤ የሚገለው፤ የሚደበድበው፤ በጥይት ቶክስ የሚያሸብረው እራሱን የቅማንት ኮሚቴ ብሎ የሚጠራው ቡድን የህዝብ ስጋት መሆኑን እንኳ ሄደው መግለጫ አውጥተዋል፡፡
ስለሆነም እስከ መጋቢት 19/2012 ዓ.ም
1. የመንግስት ውሳኔ ሰጭ አካል የተጣራ መረጃ መያዛችሁን አረጋግጣችሁ ለሰላማዊ ውይይት የማትዘጋጁ ከሆነ፤
2. ሰላማዊ ዜጋን መግደልና ማሰር ማንኛውም እንቅስቃሴ መገደብ ብሎም ማሸበር ከቀጠላችሁ፤
3. የቅማንት ኮሚቴ ነኝ ከሚል የሽብር ቡድን ጋር የሚደረግ የሴራ ግንኙነትና ህዝብን ለመጉዳት የዘመቻው አካል ከማድረግ ካልተቆጠባችሁ፤
4. ህዝባችን ከጉሮሮው ነጥቆ ለደህንነቱ መጠበቂያ የገዛውን የጦር መሳሪያ ለመንጠቅ ከሞከራችሁ፤
5. አርበኛ መሳፍንት ተስፉ፤ አርበኛ አረጋ አለባቸው፤ አርበኛ ሰፈር መለስ እና መሰል አርበኞችን ለመግደል ጦር ካዘመታችሁ፤
6. የአማራ የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ ተገቢ ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ፤
7. የጎንደርና መላው አማራ የኮሮና ቫይረስ ወይም Covid 19 ተላላፊ በሽታ እንዲከላከል መንግስታዊ ሃላፊነት መወጣት ሲገባችሁ የህዝቡን ትኩረት በሌላ
ጉዳይ እንዲያደርግ አድርጋችሁ ተጋላጭ እንዲሆን ካደረጋችሁ፤
8. ቅጥረኞችን በመጠቀም የፋኖን መልካም ስም የማጠልሸትና የውስጥ አንድነቱን ለመሸርሸር ከመስራት ካልተቆጠባችሁ፡- ፋኖ አማራ ጀግናውን
ህዝባችን መጋቢት 19/2012 ዓ.ም የህልውና ሁለገብ ትግል ለማድረግ ህዝቦችን ክተት በመጥራት በጀግንነት የምንታገል መሆናችን እናሳውቃለን፡፡
የተከበርከው መላው የአማራ ህዝብና የሀገራችን ህዝቦች ዘርህን ሊያጠፋ የመጣውን ኃይል ለመመከት ለሚደረገው የክታት ጥሪ ቀንም ሆነ ሌሊት ዝግጁ ሆነህ በንቃትና በተጠንቀቅ እንድትጠባበቅ መእክት እናስተላልፋለን!
መጋቢት 17/07/2012 ዓ/ም
Filed in: Amharic