>
5:13 pm - Monday April 19, 7362

ጽንፌቄሮ  እና ኮቪዲኮረና  - ኢትዮጵያዬ  እና ዓለሚቱ!!! (ዘመድኩን በቀለ)

ጽንፌቄሮ  እና ኮቪዲኮረና  – ኢትዮጵያዬ  እና ዓለሚቱ!!!

 

 

ዘመድኩን በቀለ
• ወዳጆቼ ይሄኛው ቄሮ-ኮሮና ገራገር ነው። በፍጹም አያዳላም። ፍትሃዊም ነው። እንደ ወያኔና እንደ የወሀቢይ እስላም ዘርና ኦርቶዶክስ እየመረጠ አይገድልም። እንደ ሲዳማ ጴንጤ ቤተ ክርስቲያን መርጦ አያቃጥልም። እንደ ዐቢይ አህመድ አፈ ቅቤ ልበ ጩቤ አይደለም። አያሾፍም።
• የተዋሕዶ ልጆች ሆይ ለዚህኛው ኮቪዲ-ቄሮ አትደንግጡ። ኮቪዲቄሮ በፀበልም፣ በመስቀልም፣ ይለቃል። ካልነኩት አይነካም። ካልደረሱበት አይደርስም። እንደመቅሰፍት ያለ ቄሮ ስለሆነ ሳኒታይዘር ቢኖርህም መርጦ የሚያጭደን ስለሆነ ብዙም አትስጉ። አራጅ መቅሰፍት የክርስቶስ የደሙ ምልክት የሌላቸውን ሊያርድ፣ ኢትዮጵያን የነኩ በሙሉ ሊነካ የተላከ መቅሰፍት ስለሆነም ብዙም አትፍሩ።
• ያም ሆነ ይህ ግን ሳይረፍድባችሁ፣ ቀሳፊው መልአክ አጨዳውን በስፋት ሳይጀምር ፈጥነን በቀረን 5 ደቂቃ ውስጥ ንስሐ እንግባ። ርቀታችሁን ጠብቁ፣ እጃችሁን በሳሙና ልባችሁን በንስሐ እጠቡ። ከቤታችሁ ዘግታችሁ ተቀመጡ። እንደ አጋሰስ ያገኛችሁትን ሁሉ በየሰዓቱ አታግበስብሱ። በጥቂት በጥቂቱ ብሉ። አብዝታችሁ ጹሙ፣ ጸልዩ። ይሄኛው ኮቪዲቄሮ እንደ ወሐቢያው ቄሮ በር አይሰብርም። እሳት በላይህ ላይ አይለኩስም። ንብረትህን አያወድምም። ዐማራና ኦርቶዶክስን ለይቶ አያርድም።  ኮቪዲየተባለው ቄሮ ሲበዛ የዋህና ደግና ካልደረሱበት የማይደርስ፣ ከያዘም ሁሉንም የማያግድል ሩህሩህ ነው። የማይሰሙትን በሙሉ ግን ያለ ርህራሄ የሚያጭድ መቅሰፍት ነው።
  ከእንግዲህ ኢትዮጵያ ብቻዋን አታለቅስም። ደግሞም የምታለቅስበት ምክንያትም የለም። ዓለም ሁሉ ከእኛ ጋር በጋራ በጥፍሩ ቆሞ ያለቅሳል እንጂ ከእንግዲህ ብቻችንን በቄሮም በኮቪዲም አናለቅስም!!!
•••
የቻይናው ቄሮኮረና ከመምጣቱ በፊት፣ ዓለምም ደንግጣ እንዲህ ሱባኤ ከመግባቷ በፊት፣ ያኔ ያኔ ጥንት በመንግሥት ስፖንሰር ይደረግ የነበረ “ጽንፈኛ ቄሮ” የሚባል አደገኛና ጨካኝ ገዳይ ጽንፈኛው የወሃቢ እስላም ቄሮኮሮና የተባለ ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ ነበረ። ጽንፈኛው ቄሮና የቻይናው ኮቪዲኮሮና መንትዮች ናቸው።
በጭካኔውና በአሰቃቂ ግድያው የሃገሬ ኮሮና ቢበልጥም፣ ሁለቱም ግን የሚመሳሰሉበት አንድ ባህሪ አላቸው።
 
 መንገድ ማዘጋት – ልሣን ማዘጋት
 ሱቅ ማዘጋት – ጉሮሮ መዝጋት
ከክልል ማስወጣት –  ከቤት ማዋል
መድረሻ ማሳጣት – ንፋሽ ማሳጠር
በደቦ መፍጀት –  በጅምላ  መረፍረፍ ….
 
የኮሮናም፣ የጽንፈኛው ቄሮም ተመሳሳይ ባህሪያቸው ነው። ኮቪዲ ግን በሳሙናም በኪኒንም ሊምርህ ይችላል። 
•••
ኢትዮጵያ በጽንፈኛው ቄሮኮሮና ስትሰቃይ ዓለሚቱ ባላየ፣ ባልሰማ ጮጋ ብላ ታየን ነበረ። ከጂቡቲ አዲስ አበባ ያለው መንገድ፣ የወለጋ አዲስ አበባ መንገድ፣ የሸኖ አዲስ አበባ መንገድ፣ የሰላሌ አዲስ አበባ መንገድ፣ የናዝሬት የሐረር፣ የጅማ፣ የአሩሲ አዲስ አበባ መንገድ በቄሮኮሮና ቫይረስ ሲዘጋ ዓለምዬ ሶራ ባላየ ባልሰማ ላሽ ብላን ነበረ። እንዲያውም ከትከት ብላ ሳትስቅም አትቀርም።
•••
ያኔ በቅድስት ኢትዮጵያ ጽንፈኛው ቄሮኮሮና ቫይረስ፣ ሆቴሎችን ሲያዘጋ፣ የእነ ሸምሱን ሱቅ ሲያዘጋ፣ ዳቦቤት፣ ሽሮ ቤት ሲያዘጋ፣ ሆስፒታል ትምህርት ቤት ሲያዘጋ፣ ቤተ ክርስቲያን መስጊድ ዩኒቨርሲቲ ሲያዘጋ ዓለሚቱ ባላየ ባልሰማ ጫ ብላ ታይ ትመለከትም ነበረ። ኮረናችን የ15 ቀን የማርያም አራስ የሆነች እናት በመሰላ ከተማ አናቷን ጨፍጭፎ ሲገድል፣ በበሮዳ አቶ ደመናን፣ የአቶ ደመናን ወንድም ደረጀን፣ የአቶ ደመናን ባለቤት ወይዘሮ ወላንሳን በአንድ ቀን ከአንድ ቤተሰብ 3 ሰው መርጦ ሲያርድ፣ ንብረት ሲዘርፍ፣ ከክልሌ ውጡ ብሎ ሃገር ምድሩ ላይ እሳት ሲለቅ ዓለሚቱ ጉዳያችሁ ነው ብላ ባላየ ባልሰማ ላሽ ብላን ነበረ።
•••
የጽንፈኛቄሮኮሮና ቫይረሱ ስፖንሰሮች የሆኑት እነ  ኮቪዲዐቢይ–ሚሊዮኔና የጽንፈኛ ቄሮኮሮና ቫይረሱ ፈጣሪ ኮቪዳጃዋር–86 ተጠቃቅሰው በጋራ በፈለሰሙት ቄሮኮሮና ቫይረስ በጅምላ ሲያስፈጁን ዓለም የራሳችሁ ጉዳይ ብላ በሯን ጠርቅማብን ነበረ። አማሪካም፣ ቻይናም፣ ጣልያንም፣ ስፔንም፣ ጀርመንም፣ ለንደንም ጮጋ ብለውን ነበረ። ቫይረሱ የአንገት ማዕተብ እያየ፣ ዐማራ፣ ጉራጌና፣ የደቡብ ሰው፣ ጥቂት ትግሬም ኦሮሞ ኦርቶዶክሶችን፣ ወላይታና ዶርዜ እየመረጠ ሲያርድ፣ ሲያቃጥል ዓለም እኔ የለሁበትም ብሎ ሃሌ ሉያ ኢየሱስ ጌታ ነው እያለ ቢች ዳር ፓርቲ አዘጋጅቶ ይጨፍር ነበረ።
•••
እንዲያውም ይውጣላችሁ። ምንአባታችሁ ታመጣላችሁ ብለው ላፈናቀለን፣ ላሳረደን፣ ላስገደለን፣ ላቃጠለን፣ የመከራ ዶፍ በላያችን ላይ ላወረደብን ለአፈ ቅቤ ሆደ ጩቤው ለአጋሮው ወጣት፣ ለኮሎኔል ዐቢይ አህመድ የኖቤል ሽልማት ሸለሙት። በርታ ኮሮናችን፣ በርታ ቫይረሳችን ያሉት እስኪመስለን ድረስ ለሞት ነጋዴው ሶዬ ለኮቪዲያችን ብርም፣ ክብርም ሸልመው ኤትአባታችሁ አሉን። ቀረቀሩልን። አላገጡብን ቅድስት ኢትዮጵያም አለቀሰች። እኛም ዝም አለነ።
•••
ይሄን ያየ መድኃኔዓለም። ይሄን የተመለከተ እግዚአብሔር የቅድስት ሃገር ኢትዮጵያ አምላክም ተነሣ። ብድግ ብሎ ቆመ። ለዓለሚቱ ከቻይና ተነሣ የተባለ እኔ ነኝ ያለ ግብዲያዬ ቄሮ ላከባታ፣ አስነሣባታ። የእኛ ቄሮ የሚታይ ነው። የሚዳሰስ ነው። የሚጨበጥም ነው። የእኛ ቄሮ በስም፣ በመልክ፣ በብሔር፣ በሃይማኖትም ይታወቃል። እናት አባቶቻቸው ወላጆቻቸውም፣ ስፖንሰሮቻቸውም ጭምር ይታወቃሉ። “ ኣላህ ወአክበር እያለ የሚያርድ የወሐቢይቄሮ ነው። የዓለሚቱ ቄሮ ግን ሃይማኖት የለው፣ ብሔር የለው። ደግሞም የማይታይ፣ የማይዳሰስ፣ የማይጨበጥ  ይሄን ያክላል፣ ይሄን ይመስላል እንዳይባል አድርጎ አስነሣዋ አባቴ። አስነሣው አልኩህ።
•••
የዓለሚቱ ቄሮ ኮሮና 19 ይኸው ምድርን ባዶ አደረጋት። ጭጭ፣ ምጭጭም አደረጋት።  ሱፐርማርኬት ዝግ፣ ሲኒማ መዝናኛ፣ ሆቴል ሬስቶራንት ዝግ፣ ጭፈራ የለ፣ መጠጥ የለ፣ ዝሙት የለ፣ መሳሳም መሥሪያቤት፣ መስጊድ፣ ቸርቹ ዝግ። ትራንስፖርት፣ አውቶቡስ ባቡር፣ መርከብ አውሮጵላን ዝግ፣ ድንበሩን ሁሉ ጥርቅም አደረገዋ የቻይናው ቄሮ። አዳሜና ሔዋኔ ክትት። ወንድ የሆነ ከቤቱ ይውጣ አለላቸዋ ቄሮኮረና።
•••
የዓለሚቱ ቄሮኮሮና ሲበዛ ደፋር ነው። ሲፈልግ ቤተ መንግሥት ይገባል። እንግሊዝም፣ ስፔንም ገብቶ ልዑላኑን ነገሥታቱን ይዞ። ረብሾ። የስፔኗን ንግሥት ገድሎ፣ የእንግሊዙን ልዑል አልጋ ላይ ጥሎ፣ ጠቅላይ ሚንስትሩን ከሰው ለይቶ ለብቻው አግልሎ አስቀምጦ አሳይቶናል። ይሄ ቄሮ ደፋር ነው ወታደር አይፈራም። የግብጽ ጀነራሎችንና ወታደሮችን ከኢትዮጵያ ጋር የቋመጡለትን ውጊያ ሳይጀምሩ ረፍርፎ ረሽኖ አሰናብቷቸዋል። የቻይናው ቄሮ ኒዩክሌር የታጠቀ፣ አውቶሚክ ቦንብ ያለውም አይፈራም። የእኛ ቄሮ ግን ቢያንስ ቢያንስ ነፍሱን ይማረውና የድሮውን የአግአዚ ወታደርና የጥይት ድምጽ ሲሰማ ይፈራ፣ ይሮጥ ይበተንም ነበር። እናቴ ይሄኛው ኮረናቄሮ ግን መስሚያው ጥጥ ነው።
•••
ለዚህ ጦማር መነሻ እሳት የቆሰቆሰችልኝ ዶክተር መስከረም ለቺሳ በስሱ እንዲህ ስትል እኔ ዘመዴ ደግሞ የመስኪን ሐሳብ ወፈር አድርጌ እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ።
•••
ከቻይናኮሮና በፊት በእኛ ቄሮኮሮና ጊዜ ሰው በውኃ እጥረት ተቸግሮ ሲሰቃይ እያየ ቄሮው መንግሥታችን ለጽንፌ ቄሮኮሮና መዠለጫ ይሆን ዘንድ ዛፍ ተክሎ አበቦችን ውኃ ሲያጠጣ ነበር።
•••
ከቻይና ቄሮከኮሮና በኋላ ግን ከመንግሥት ባለሥልጣናት እስከ ጥበቃ ሠራተኞች ድረስ ያሉትን የሰው ልጆችን ሁሉ እጅ እያስታጠቡ ደንገጡር አድርጎ አሳረፋቸው። ያውም በየሜዳው በየአደባባዩ በርሜልና ሳሙና አቁመው፣ አስቀምጠውም ጭምር ነዋ። ይኸው አበቦቹም ዛፎቹም ተረስተው መጠውለግ ጀምረዋል። ኤትአባታቸው። የሰውልጅ ክቡር ነው። ከአበባም ከዛፍም ይበልጣል።
•••
ከቻይና ቄሮኮሮና በፊት በኮረና ታናሽ ወንድም በኢትዮጵያው ኮረናቄሮ ምክንያት ቤተክርስቲያን እየተቃጠለ፣ ካህናት እየታረዱ፣ ንፁሕ ሰው እየተገደለ ቄሮው ጠቅላይ ሚኒስትራችን ግን በኢትዮጵያ አየር መንገድ በየሃገሩ እየዞረ “ቢዚ” ኾኖብን ነበረ። ቁርስ ጅቡቲ፣ ምሳ ካርቱም፣ ራትና አዳር አስመራ ምጽዋ እያለ ሽርሽር አብዝቶ ነበረ። ከአውሮጵላን አልወርድ ብሎም አስቸግሮን ነበረ።
•••
ከቻይና ቄሮኮሮና በኋላ ግን የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንኳን አቢቹን ሊያንሸራሽር እሱን ይዞ ሊዞር ይቅርና በየአገሩ የቫይረስ ምልክት ኾኖ “ድርሽ እንዳትልብን” ተብሎ ፊት ተነሣ። ቫይረስ አከፋፋይም የሚል ቅጽል ስምን አተረፈ። አቢቹም ፈራ፣ ደነገጠም። እንኳን በአውሮጵላን ሊሳፈር ከአልጋውም አልወርድ አለ። በሚኒሊክ ቤተመንግሥት ተደብቆ በፕላዝማ ሥራ ጀመረ። ካሜራ ማን እንዳትጠጋኝ አላለም። እርፍ።
•••
ከቻይና ቄሮኮሮና በፊት ኢትዮጵያዊ ሰው በአገር ውስጥ በግፍ እየተፈናቀለ፣ በጽንፌቄሮ እየተረፈረፈ፣ እየተጨፈጨፈ ጠቅላያችን “ይኽን ያኽል ስደተኛ ከግብጽና ከዱባይ፥ ከሳዑዲና ከገለመሌ አስጭኖ አስገባልን። እናም ወንዶች በጭብጨባ፣ ሴቶች በእልልታ አመስግኑት፣ እልልበሉለት፣ ” እየተባለ ጡሩንባ እየተነፋብን ጆሮአችን ደንቁሮ ነበር። መጡ የተባሉት እስረኞች እኮ በአብዛኛው የኦነግ ቄሮቫይረሶች ናቸው። ክርስቲያን እየመረጡ የሚያርዱ ኮሮናዎች።
•••
ከቻይና ቄሮኮሮና በኋላ ግን ጠቅላያችን ከውጭ የሚመጡ ኢትዮጵያውያን ላይ ድንበር ለመዝጋት ተገደደ። ከገቡም በራሳቸው ወጪ skylight hotel ለ14 ቀን ራሳቸውን እንዲለዩ ዐዋጅ ዐወጀ። የገቡትንም ከለይቶ ማቆያ እንዳይወጡና አገሬውን እንዳይበክሉ በፖሊስ ሳይቀር እያስጠበቀ ለናቀውና ድምጹን ላልሰማው ለአገሬው ሰው ሳይወድ በግዱ የቅድሚያ ግዴታውን እንዲወጣ አስደረገው። በአየር ላይ እንዳሉ “ወደ መጣችሁበት ሀገር ተመለሱ” የተባሉ ኢትዮጵያውያንም አሉ።
•••
ከኮሮና በፊት “በቱሪዝም ስም ነጮች ግብረሰዶምን እንዳያስፋፉ መንግሥት ጥብቅ ቁጥጥር ያድርግ” እያለ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲጮኽ ኮሮናው መንግሥታችን ግን የኢትዮጵያን በህል፣ ሃይማኖት ለማርከስ የቆረጠ ነውና ነገሩን ዓይቶ እንዳላየ፣ ሰምቶም እንዳልሰማ በቸልታ ያይ ይመለከትም ነበር።
•••
ከኮሮና በኋላ ግን በኢትዮጵያ ውስጥ የውጭ ሃገር ዜጎች ከሃገሬው ሰው ጋር ታክሲ እንኳ አብሮ ለመሳፈር እስኪያቅታቸው ድረስ “ኮሮና” እያለ የሚጸየፋቸውና የሚጠራጠራቸው በዝቶ ለመደንገጥ ተገደዱ። በዚህ ካልተማሩና ካልተመለሱ ደግሞ በቅርቡ #ኦርቶ_ቪስታ የተባለ ሌላ ቀሳፊ መልአክ ገና ለግብረሰዶማውያን ብቻ ወረርሽኝ ሆኖ እንደሚመጣም እየተነገረ ነው። በዓለም ላይም የቱሪዝም ኢንዱስትሪው በኮሮና ምክንያት ከደረሰበት ቀውስ ለማገገም በትንሹ አንድ ዓመት እንደሚወስድበት በአሜሪካ ባለሥልጣናት እየተነገረ ነው።
•••
ከኮሮና በፊት ሃገር የምትመራው አሥሬ ተቃቅፎ ፎቶ በመነሳት ነበር። ጉንጭ እየሳሙ እያሳሙ። ያገኙት ሁሉ ደረት ላይ እየተለጠፉ። ላገኙት ሁሉ እጅ እየሰጡ ነበረ ሃገር የምትመራው። ፎቶና ካሜራ ዋነኛ የለውጡ ሞተሮችም ነበሩ።
•••
ከኮሮና በኋላ ግን መተቃቀፍ የለም። እፉ ካካም ሆነ። መሳሳም፣ መላፋት፣ የፎቶ ፕሮፓጋንዳ ቀረች። ፎቶ አንሺውም ፎቶ ተነሺውም ጠፉ። ጠቅላዬ ናፈቀኝ። ሁላቸውም ተደበቁ። ማነው አንሺ? ማነው ተነሺ? አለ ኦቦ ዳውድ ኢብሳ። ኢንዴዦያ ነው።
•••
ከኮሮና በፊት ዳንኪራ በዝቶ ነበር። ድግስ፣ ዘፈን፣ አስረሽ ምቺው እንደጉድ ነበር። ስደተኛ የሌለባት፣ የተራበ የሌለባት፣ ያደገች፣ የተመነደገች፣ ምዕራባዊት ሀገር በቴክኖሎጂ የሰለጠነች። የበቃች የተራበ የተጠማ ሰው የሌለባት ሃገር እንደሚመራ ሰው የቦለጦቃ መሪዎቻችን ጠዋት ማታ አሸሼ ገዳሜውን እንደጉድ አብዝተውት ነበር። መጪው ዘመን የብልጽግና ነው ብለው ደሰኮሩብን።
•••
ከኮሮና በኋላ ሕዝብም መንግሥትም ከዋልድባ መነኮሳት ከዘጉ ባሕታውያን በበለጠ መልኩ የሌለ ግሩም ብሕትውናን እየተማረ እየቀጸለ እየተገበረውም ነው። መንግሥትም እኮ ፈልቶበት ነበር አሁን አደቡን ገዛ። ለአንቺም ቅጂ ለእኔም አምጪ ቀረ። አይ ኮሮና።
•••
ከኮሮና በፊት የማኅበረ ሥላሴ ገዳም አባቶች ለኢትዮጵያና ለቤተክርስቲያን ሰላም የ14 ቀን ብሔራዊ የጾምና የምሕላ ጸሎት ሲያውጁ ያንጊዜ የኢትዮጵያ መንግሥት በሌለ ሰላም የሰላም ኖቤል ሽልማት ተሸልሞ አሸሼ ገዳሜ ላይ ነበር። ጎንደርና አክሱም ሲጸልዩ አዲስ አበባና ሌሎች ጫ ብለው ያቀልጡት ነበር።
•••
ከኮሮና በኋላ አይደለም የኢትዮጵያ መንግሥት የዓለም መንግሥታት የግዳቸውን የ14 ቀን ኳራንቲን (ወሸባ ቤት) ገብተው የማኅበረ ሥላሴ አባቶችን ትእዛዝ እያስተገበሩ ይገኛሉ። ገና የ21 ቀኑ ሱባኤ ይቀጥላል። የ30 ቀኑም አለ። ትእዛዝ ከእግዚአብሔር ሲመጣ እንዲህ በአንድም በሌላም በግድ ይፈጸማል።
•••
ከኮሮና በፊት ስለ ዓረባዊቷ ሮቦት ማዳም ሶፊያና ስለአርቲፊሻል ኢንቴሊጀንስ እየተፈላሰፍን ነበር።
ከኮሮና በኋላ ስለመሠረታዊ ነገሮች እያወራን ነው። ስለሕዝቡ ገንቢ ምግቦች ማግኘትና ስለተፈጥሯዊ በሽታ መከላከል አቅሙ መነጋገር ጀምረናል። ይኽ ሕዝብ ቢታመም የሚተኛበት አልጋ፣ የሚውጠው መድኃኒት፣ የሚያክመው ሃኪም እንኳ እንደሌለው እያስተዋልን ነው።
•••
ከቻይና ቄሮኮሮና በፊት የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ግቢዎች በጽንፌቄሮኮሮና አማካኝነት የምስኪን ተማሪዎች ግንባር መፈንከቻና ከፎቅ ተወርውሮ መሞቻ ኾነው እናቶች እያለቀሱ፣ መንግሥት ግን በፖለቲካ ስሌት ከፓርቲዎች ጋር ብልጥ ብልጥ ሲጫወት ነበር። ለመፍትሔዎችም እየዘገየ ተማሪ ይጉላላ ነበረ። ሰላም በመጥፋቱ በራሳቸው ወጪ ወደ የሃገራቸው በጊዜ የተመለሱትን አላሳልፍ ብሎ መንገድ ዘግቶ ይገድል ያፍን የነበረ።
ከቻይና ቄሮኮሮና በኋላ ግን ይኸው በራሱ ወጪ መንግሥት ሆዬ ተማሪ ወደየአገሩ መላክ ጀመረ። እናት ሆይ እንኳን ደስ አለሽ።
•••
ብልጦ ጽንፌቄሮኮረና መንግሥታችን ወደ 49 ሺ የዐማራ ተማሪዎችን አፈናቅሎ፣ ከዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ገበታቸውም አባሮ፣ የራሴ የሚላቸውን ወገኖቹን አቅፎ ያስተምር ነበረ። ብልጦ የደብተራ ልጆችን አባርሮ፣ አቆርቅዞ በእሱ ቤት የራሴ የሚላቸውን በእውቀት፣ በኢኮኖሚ ማሳደጉ ነበረ።
•••
አባቴ መድኃኔዓለም ከላይ አየልሃ። ተመለከተልሃ። ፈረደልሃ። የቻይናውን ቄሮ ኮቪዲኮሮናን አስነስቶ ሁሉንም እኩል ጠረቀመው። የዐማራ ተማሪዎች ደፍተራው አባ አመሀ ኢየሱስ ዘንድሮ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የትም አትሂዱ፣ ትምህርት የለም ቢሏቸው አልሰማም ብለውም ነበረ። ነገር ግን እርሱ ባወቀ በቄሮኮሮና ላይ አድሮ የቻይና ኮሮና ገብቶ ጉድ ሳያደርጋቸው በፊት ወደ የሃገራቸው መለሰ። አሁን ከየ ዩኒቨርሲቲው የሚበተነውን እግዚአብሔር ይከልለው።
•••
በዚህ ሁሉ መሃል ግን ለንስሐ ያድርግለትና የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማን ሳላመሰግን ባልፍ አምላኬ ይቀየመኛል። ሃይማኖቴም አይፈቅድልኝም። ቦለጢቀኞች ለፎቶ ነው የሚያደርገው ቢሉም እሰይ እንኳን ደግ አደረገ። ነገር ግን እንደ ህዝብ መሪነቱ ከህዝብ መሃል ሆኖ በሽታውን ሳይሰጋ፣ ሳይፈራም ሌት ተቀን አየሯ በተበከለው ከተማ እየዞረ ለሚያደርገው ልፋት ጎንበስ ብዬ እጅ እነሳዋለሁ። ተባረክ። ዘር ይውጣልህ። እንዲህ ሆነህ ብትሞትም አይቆጭህ። ኮሮና መሃል ቆመህ ኮሮናን የምትዋጋ የቱለማ ኦሮሞው ልጅ አመሰገንኩህ።
•••
አልጨረስኩም ። እያየሁ እቀጥላለሁ። 
•••
ሻሎም !    ሰላም !   
መጋቢት 20/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic