>
5:18 pm - Sunday June 16, 5771

ቋሚ ሲኖዶስ አስቸኳይ ውሳኔዎችን አሳለፈ! (አደባባይ ሚዲያ)

ቋሚ ሲኖዶስ አስቸኳይ ውሳኔዎችን አሳለፈ!

 

አደባባይ ሚዲያ 
 

የቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ!

 ♦ ቅዱስ ፓትርያርኩ እራሳቸውን ለልዩ ሱባኤ ይለያሉ 
♦ ምዕመናን በየቤታቸው በፀሎት  እንዲቆዩ 
• ከወትሮው አነስ ባለ ቁጥር ካህናት ይቀደሱ
• ምዕመናን ከቤት ሆነው ይጸልዩ
• መንፈሳዊ ኮሌጆችና ማሰልጠኛዎች ለማቆያ ይሁኑ…
ቅድስት ቤተክርስቲያን ለኮሮና በሽታ በሚደረገው  እርዳታ ለአዲስ አበባ መስተዳደር 3 ሚሊየን ብር ውጭ ሆኖ እንዲሰጥ ወስናለች።
 ሌላው ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ ካህናቱ እና ዲያቆናት  በየአግልግሎት ደብራቸው ተወሰነው  ከግቢ ሳይወጡ እንዲያገለግሉ የተቀሩት አገልጋዮች ደግሞ ለጊዜው በመኖሪያ ቤታቸው እንዲሆነ ተወስኗል።
 የካህናት ማሠልጠኛ እና የቴዎሎጂውን የመማሪያ ማስተማሪያ ቦታውን ለማቆያነትና ለአንዳንድ አገልግሎት እንዲውል ተወስኗዋል።
 ዛሬ በመንበረ ፓትርያርክ ቅፅረ ጊቢ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት  በቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ በብፅዕ አቡነ ዮሴፍ በተነበበው መግለጫ ተገልፆአል።
እግዚአብሔር አምላክ ዓለማችንንና አገራችን ኢትዮጵያን ይጠብቅልን። 
ለሕዝባችንም ምሕረትንና ፈውስን ይስጥልን !
አሜን !
Filed in: Amharic