>
5:16 pm - Thursday May 24, 9027

የሶማሌ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ! ( ሙክታሮቪች ኡስማኖቭ)

የሶማሌ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ!

ሙክታሮቪች ኡስማኖቭ
የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊው ሀገር በጭንቀት በተወጠረችበት ወቅት ችግር ፈጣሪ በመሆናቸው ተነስተዋል!
* የፕሮቶኮል ዋና ሀላፊውም ተቀይሯል!
* የፀጥታ ዘርፉን ይመራ የነበረው ግለሰብም በቤት ውስጥ እስር እንቅስቃሴው ተገድቧል
 ይህ ውሳኔ ሀገር ሀላፊነት የጫነችበት መሪን ህይወት ቅድሚያ መሰጠት ስላለበት የተወሰደ የጥንቃቄ እርምጃ ነው!!
 
የሶማሌ ክልል በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው። እንደማንኛውም የክልል ፖለቲካ በስራ አስፈፃሚ መካከል የፖለቲካ አለመግባባት እንደሚከሰተው ይህም የዚሁ ነፀብራቅ የሆነ ጉዳይ ነው። በግል ለማጣራት ያደረኩት ሙከራም የሚከተለውን መረጃዎች አግችቻለው።
ትናንትና ከሙስጠፋ ጋር ልዩነት የነበራቸው አንዳንድ አካላት ወደ የሴራ ፖለቲካ ገብተው በግምገማ ሰበብ ሙስጠፋን በአጣዳፊ ሁኔታ ለማንሳት ይጥራሉ። ሆኖም ሙስጠፋ ይህን አካሄድ በዚህ ሀገር ጭንቅ ውስጥ በገባችበት ወቅት የፖለቲካ አሻጥር ቀድሞ ስለነቃ የግምገማውን አካሄድ ሳይቀበለው ቀረ። ሴራውም ከሸፈ።
አሁን ክልሉ በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ በመግባቱ ሙሉበሙሉ ፊቱን ኮሮናን ወደ መታገል በመመለስ ከህዝቡ ጋር በጋራ የሀገርን የጋራ ጥረት ወደማገዝ ተሸጋግሯል። የፀጥታ ዘርፉን ይመራ የነበረው ግለሰብም ከፕሬዝዳንቱ ጋር በነበረው ልዩነት ለሀገር ደህንነት ሲባል በቤት ውስጥ እስር እንቅስቃሴው ተገድቧል። የፕሬዝዳንቱ የፕሮቶኮል ሀላፊም ተነስቷል። አሁን ባለው የሀገር ችግር ላይ ሌላ ችግር ላለመጨመር በፖለቲካ ልዩነት ቢኖርም የሀገር ጥቅም ስለሚቀድም እና ሀገር የወረርሺኝ አደጋ ስለተጋረጠባት በርካቶች የሙስጠፋን ጊዜያዊ እርምጃ ደግፈዋል። በጂግጂጋም እኔ የታዘብኩት ይህንን ነው።
አሁን ሁሉም ትኩረቱ በሽታው ላይ መልሷል። እዚህም እዚያም የሚወራ ያልተጣራ ወሬ ቢኖርም። በጂግጂጋ ፍፁም ሰላማዊ እንቅስቃሴ ነው ያለው። በርካታ የፈጠራ ወሬዎች ስለሚወሩ ለግጭት ነጋዴዎች ጆሮ መስጠት አያስፈልግም። ክልሉ ከጫፍ እስከ ጫፍ በአቶ ሙስጠፋ ኦማር አመራር ስር በሰላም እየኖረ ነው። ዋናው ስጋቱ የኮሮና ወረርሺኝ በመሆኑ የፖለቲካ ልዩነቱ የነበረ እና በዳበረ የሶማሌ ህዝብ ውስጣዊ ግጭትና ውጥረት የመፍቻ የሽምግልና መንገድ የሚፈታ ይሆናል። ይህ የክልሉን ህዝብ የሚያሳስብ አይደለም።
አንዱና ትልቁ ብልፅግና ፓርቲ ምቹ ያደረገው ነገር የፓርቲ አስተዳደርና ውስጣዊ መመሪያና ደንብ ስላለው ጉዳዩ በብልፅግና አጠቃላይ ልዩነትን በህጋዊ መንገድ መፍትሄ የመፈለግ ስታንዳርድ መሰረት የክልሉም ውስጣዊ ልዩነት በዚሁ መንገድ ይፈታል ብዬ እጠብቃለሁ።
እንደቀድሞ ኢህአዴግ አንዱን በአንዱ በማናከስ ክልሉን ባለስልጣናት በመፐወዝ ክልሉን ማቆርቆዝ አሁን አይታሰብም። ሁሉ ነገር በህግ እና በፓርቲ ውስጣዊ አሰራር የሚያልቅ ይሆናል። ይህን መረጃ የማስተላልፍላችሁ በወያኔ ካድሬዎች እየተነዛ ያለው በሬ ወለደ ወሬ ክልሉን ለማተራመስ ፍላጎት ስላለ ነው። የሶማሌ ህዝብ ተረጋግቶ በሰላም ኮሽታ ሳይሰማው እየኖረ ነው። ስጋቱ ኮሮና ነው። የብልፅግና ፓርቲን ለማዳከም፣ የሶማሌን ህዝብ እራሱን የማስተዳደር መብት በእውነተኛ ፌዴራሊዝም እየመራ ያለውን ሙስጠፋ ስም ለማጥፋት በርካታ ዘመቻዎች በዲጂታል ወያኔ የሚዘራውን ሀሰተኛ መረጃ መስማት የለብንም።
የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊው ሀገር በጭንቀት በተወጠረችበት ወቅት ኮሮናን ለመታገል ርዐሰ መስተዳድሩ በትኩረት እንዲሰሩ ሲባል ተነስተዋል። የፕሮቶኮል ዋና ሀላፊውም ተቀይሯል። ይህ ውሳኔ ሀገር ሀላፊነት የጫነችበት መሪን ህይወት ቅድሚያ መሰጠት ስላለበት የተወሰደ የጥንቃቄ እርምጃ ነው።
በተረፈ የክልሉ መንግስት መግለጫን መስማት ይሻላል። ይህ መረጃ ብዙ ሰዎች በውስጥ መስመር የተሳሳተ መረጃ እየተዘራ በመሆኑ የማውቀውን እንድነግራቸው በጠየቁኝ መሰረት፣ እኔ በግል ለማጣራት ሙከራ አድርጌ የደረስኩበት መረጃ እንጂ የክልሉ መንግስት ይፋዊ መግለጫ አይደለም። የሰማሁት እና ያጣራሁትን ነው ያጋራኋችሁ። የክልሉ መንግስት መግለጫ ሲሰጥ ተርጉሜ አቀርብላቹሀለው።
በመጨረሻም እየመጣብን ያለው የወረርሺኝ አደጋ ከፍተኛ በመሆኑ ሙሉ ትኩረታችንን በብሽታው ላይ እናድርግ ለማለት እወዳለሁ።
Filed in: Amharic