>

ኮሮና A-3 (ኢብሮ ሹመት)

ኮሮና A-3

ኢብሮ ሹመት
1,የኮሮና በሽተኞች በሶስት ወር ውስጥ በአለም ከአንድ ሚሊየን በላይ ሆነዋል ከ210ሺ በላይ ድነዋል 55 ሺ እሚሆኑት ደሞ ሞተዋል ።
የአውስትራሊያ ቺፍ ሜዲካል ኦፊሰር አለም ላይ አሁን  ካለው 10  እጥፍ በላይ በቫይረሱ ያሉ ሰዎች እንደሚሆን ተናግረዋል ማለትም ከአስር ሚሊየን በላይ ይሆናል ነው ያሉት!
2,አሜሪካ አሁን ላይ በሁለት ሳምንት ብቻ 10 ሚሊየን እሚሆን ስራ የፈታ እንዳለ ታውቁዋል ፣ ትራምፕ አሁንም እሚያወራው ስለ ነዳጅና ስለ ኢራን ላይ ለሚያደርገው ጦርነት ነው  ፣ታዋቂው የጃዝ ጊታሪስት ቡኪ ፒዛርሊ በ 94 አመቱ በቫይረሱ ሞትዋል ጊታሪስቱ የፕሬዝደንት መቀመጫ ዋይት ሀውስ ውስጥ ለብዙ ግዜ ይጫወት ነበር ፣ የመጀመርያ የአሜሪካ ፊሲሺያን ዶክተር እንዲሁ በቫይረሱ ሞትዋል፣ አንዲት የስድስት አመት መንትያዎች እናት በሚያሳዝን ሁኔታ ሞታለች ፣ እስካሁንም በምርመራ 250ሺ ገደማ ቫይረሱ ያለበት ሲኖር 6,100 እሚሆኑ ደሞ ሞተዋል ያገገሙት ደሞ 10,400 ብቻ ናቸው ከሌላው አንጻር የአሜሪካ የሚያዙት እጅግ ብዙ ሲሆን ሚድኑት ደሞ በጣም ትንሽ ናቸው ፣ የአሜሪካም መንግስት በአሁን ሰአት አዲስ ፖስፖርት ፕሪንት አያረግም
3, ቻይና ዉሀን – ዢ ጂፒንግ አፋቸውን ማስክ ለብሰው ቤጂንግ ላይ የተተከሉ ዛፎችን ውሀ ሲያጠጡ ነብር ቻይና ዉሀን ግዛት በበጎ ፍቃድ 108 ሰዎች ለክትባት ሙከራ የተወጉት ኢንጄክሽን 18 ሰዎች አስራ አራት ቀናቸውን ትላንት ጨርሰዋል የደማቸው የጤናቸው  ሁኔታም በጥሩ ሁኔታ እንዳለ ተገልጽዋል ፣ corona beer ፋብሪካ ምርት ማምረት አቁሟል ፣ 870 እሚሆኑ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ከውጭ መተውብኛል ብለውም እያለቃቀሱ ነበር
4, እስፔን ምን አልባት ክትባት መስጠት ትጀምራለች በዚህ ወር መጨረሻ የሳይንስ ሚኒስትሩ ፔድሮ ዱኬ ነው ሀሙስ ለት በቫይረሱ ጉዳይ  በተዘጋጀ ስብሰባ ላይ የተናገሩት ብዙ የእስፖኒሽ  የክትባት እሪሰርች ፉኩሊቲዎች አሉን እና እየታገልን ነው ብለው እተታጨደ ያለውን ህዝበ አዳም አጽናንተዋል ።
ዛሬ ብቻ 7,500 አዲስ በሽተኛ በአንድ ቀን አስመዝግባለች ጠቅላላውም 118,000 ሄኖላታል ትላንት አንድ ሺ ነበር የሞተባት ዛሬ 590 ሞቶባት ከትላንቱ ተሽላ ከአሜሪካ ቀጥላ እስፔን ሁለተኛ ሆናለች ።
5, የእንግሊዙ ጠቅላይ ቦሪስ ጆንሰን እራሱን በለይቶ ማቆያ አቆይቶ እንዳለ ነው በሪሞትም ስራዬን እየሰራው ነው እያለ ነው ፣ Adam Schlesinger እስታር በ52 አመቱ በቫይረሱ ሞትዋል ፣በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ አንዳንድ ሆስፒታሎች አፍሪካውያንን እና ጥቁሮችን እንደማይቀበሉ በሽተኞች ተማረዋል የተለያየ በሽታ እንኳን እያለባቸው መታከም አልቻሉም ፣ እንግሊዝ ዛሬ ብቻ ከ700 በላይ የሞተ ሲኖር ጠቅላላ ድምርም 3,610 የሞቱ እንዳሉ ተረጋግጡዋል እስካሁን በምርመራም 38,168 ቫይረሱ እንዳለበት ተረጋግጡዋል ግን ይሄ ቁጥር ትንሽ የሆነው ብዙ ያልተመረመረ እንዳለ ነው ይላሉ ባለሞያዎች ።
6, የጀርመንዋ መርክል  ዛሬ አርብ ከኳራንታይን ተመልሳለች ተመርምራም ነጻ ወታለች ወደ ቻንስለር ተመልሳለች ፣ ጀርመን ዛሬ ከቻይና በበሽተኛ ብዛት ብትበልጥም ብዙ ተስፋዎች ከሌሎች እየተሻለች ነው ከጎሮቤት ሀገሮችዋ ከነጣልያን እና እስፔን በእጅጉ ተሽላ እየታየች ነው በተለይ ህክምና ላይ ያላትን ጉልበት አሁን ላይ አሳይታለች 86,000 ቫይረሱ ያለባቸው አሉ ግን እስካሁን የሞተባት 1,122 ብቻ ነው 22,440 ሰዎች ድነዋል ይሄ ከሌሎች ሲነጻጸር የመርክል መንግስት እና የህክምና ሚኒስትሮችዋ ወጥረዋል ማለት ነው ።
7, የፈረንሳይ መንግስት በኮሮና ምክንያት ለተቸገሩ እና ቤት ለሌላቸውም የሆቴል እየከፈለ እንደሚያስቀምጥ ተናግሩዋል ትላንት ብቻ 1,355 ሰው በሀያ አራት ሰአት ውስጥ ሞትዋል ጠቅላላ ቫይረሱ ያለባቸው 60ሺ ደርሰዋል።
8,ግዙፉ የኤምሬት አየር መንገድ በ አፕሪል 6 ስራውን ይጀምራል አለም ላይ ላሉ ዜጎቹም ነጻ አገልግሎት እንደሚሰጥ የአየር መንገዱ ሀላፊ ተናግረዋል አንድ ሰው  የሶስት ወንበር ቦታ ይዞ እና  ኤርፖርቱም ሙሉ በሮቦት የሙቀት መለኪያ ማሽኖች እንደተገጠሙ ካረጋገጡ በሃላ ነው ይሄን ያሉት ከሜግሬሽን ጋር ጥብቅ ምርመራ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል ።
8, ኢትዮጵያ ትላንት አንድ አድና ዛሬ ግማሽ ደርዘን ገቢ አድርጋለች 35 ቫይረሱ ያለበት እንዳለም እርግጥ ሆንዋል 96% ከውጭ የገባ ነው ፣
9, ኬንያም ዛሬ ብቻ  12 አዲስ ሰዎችን ስታገኝ አንድ ደሞ ሞቶባታል 122 ሆነዋል ጠቅላላ ቫይረሱ ያለባቸው እስካሁን አራት ደሞ ሞተዋል ፣
Filed in: Amharic